“ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም” ዶ/ር አብርሃም በላይ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ

December 28, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/190535

ዶ/ር አብራሃም በላይ Awramba Times ላይ በሰጡት ቃለ-ምልልስ ኢንሳን ከመሰረቱት ሰዎች አንዱ መሆናቸውን በመጠቆም ወደ ኢንሳ የገቡት በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ባስመዘገበው ውጤት እና መልካም ስነ-ምግባራቸው መሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር አብራሃም ለውጡን ተከትሎ የኢንሳ መስራች አመራሮች (ጓደኞቻቸው) በተለያየ የስልጣን ቦታ እና የፖለቲካ አሰላለፍ ውስጥ ገብተው መለያየታቸው እና ሁሉም እንደበፊቱ ለአገራዊ ዓላማ በአንድነት መስራት አለመቻላቸው እንደሚያሳዝናቸው በመጠቆም ከጓደኞቻቸው አንድም ሰው እንዲታሰር እና የሌላ አጀንዳ አራጋቢ ሆኖ ማየት እንደማይፈልጉ ለአገር ልማት ብቻ መስራት እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

ዶ/ር አብረሃም በላይ ለትግራይ ጥቅም እንታገላለን በሚል ጄ/ል ተክለብርሃን ወ/አረጋይ እና ተከታዮቹን ሃሳብ እንደሚቃወሙት በዚህም መሰረት ለአገር መስራቱን እንደቀጠለ በመግለፅ የጄ/ል ተክለብርሃንን ሃሳብ አሁንም እንደማይቀበሉት እነሱ ግን በስጋት ወደ መቀሌ መሸሻቸውን ጠቁሞ ማንም ሰው ወንጀለኛ ከሆነ ደግሞ ትግራይ ስለሄደ ከመታሰር አይቀርለትም! የትግራይ ህዝብ ለውጥ ፈላጊ እንጂ የለውጥ አደናቃፊ አይደልም የትግራይ ህዝብ አሁን ፌዴራል መንግስት ጫና እየፈጠረብን ነው ተብሎ ስጋት ውስጥ እንዲኖር ሆን ተብሎ የተለጠጠ ወሬ እየተነዛበት ነው እንጂ ምንም ስጋት የለም ብለዋል የትግራይ ህዝብም የለውጡ አካል ሆኖ ሳለ የመጣውን ለውጥ የእኔ አይደለም ብሎ መሸሸ ልክ አይደለም።

ዶ/ር አብይ አህመድ እኛ ትግሬዎች ለትግራይ ህዝብ ያላደረግነውን ሲያደርግ የነበረ አሁንም ኣብዛኞቹ ጓደኞቹ የትግራይ ልጆች ናቸው መጀመሪያ አከባቢ የንግግር ግድፈቶች ነበሩ እሱን ደግሞ አንዳንድ ሰዎች ስለ ሌባ ሲናገር የትግራይ ህዝብን ሌባ ብሎ ሰድቧል በሚል እየለጠጡት ስለሆነ እንጂ ዶ/ር አብይ ለትግራይ ህዝብ ምንም ጥላቻ የለውም።

የኢትዮ-ኤርትራ እርቅ በራሱ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅም ነበር ነገር ግን እኛ የትግራይ ልጆች አላገዝነውም ቅንነት ይጎድለናል ስለዚህ የትግራይ ህዝብን ጭንቅ ውስጥ ለማስገባት ስለሚፈልጉ ነው እንጂ የትግራይ ህዝብ እና መንግስት እልክ ውስጥ መግባት ሳይሆን የተገኘውን አጋጣሚ ተጠቅመው ነገሩን ወደ መልካም መቀየር ይችል ነበር።

በአጠቃላይ የትግራይ ህዝብን ሆን ብለው ስጋት ውስጥ ማስገባት አግባብ አይደለም ሰው የራሱን አቋም እንዲይዝ ቢደረግ የትግራይ ህዝብ በሰላም ከሌሎች ጋር እንዲኖር ማድረግ ይቻል ነበር ግን ሆን ተብሎ ማጨናነቅ እና ስጋት ውስጥ እንዲኖር የተለየ ሃሳብ የሚያቀርብ ባንዳ ብሎ መሰየም ይሄ የትም አያደርስም ለትግራይ አይጠቅምም የትግራይ ህዝብ መቼም ጠባብ ሆኖ አያውቅም ዛሬም ወደፊትም ኢትዮጵያዊ ነው ከጊዝያዊ ጥቅም በዘለለ አርቆ ማሰብ የሚችል ህዝብ ነው ስለዚህ ይህንን ህዝብ የሚጎዳ ስራ የሚሰራ መንግስት አይደለም ዶ/ር አብይ።

አውሮፕላን እና መብራት ከትግራይ ህዝብ ይቋረጣል ተብሎ የተወራው ሃሰት ነው ሆን ተብሎ ህዝቡን ለማስጋት ዶ/ር አብይ ጠላትህ ነው ለማለት የሚፈልጉ አካላት ናቸው ይህንን ወሬ እያናፈሱ የራሳቸውን ጥቅም የሚያካብቱት እንጂ ከህዝብ ጋር ጥላቻ ያለው መንግስት የለም ችግሩ የፖለቲከኞች ፈጠራ ጥላቻ ነው።

የመብራት እና የአየር መንገድ አገልግሎት ይቋረጣል የሚል የውሸት አጀንዳ በሰዎች የሚወራ እንጂ ጠቅላይ ሚንስትሩ የትግራይ ህዝብ ጥላቻ የለበትም መንግስት ሆኖ የህዝብ ሰርቪስ የሚያቋርጥ መንግስት የለም ይህንን ሰርቪስ ከሚያቋርጥ እና ከህዝብ ጋር ከሚጣላ መንግስት ቢሆን ኖሮ እኔም ልቀጥል አልችልም ነበር! ትግራይ ውስጥ እንገነጠላለን ብለው የሚንቀሳቀሱ አካላት አሉ ነገር ግን የትግራይ ህዝብ የኢትዮዽያ መስራች ህዝብ ነው ይህንን የመገንጠል አጀንዳ የሚያራግቡት እንደ ሜ/ጄ ተክለብርሃን አይነት የግል ጥቅማቸው የተቋረጠባቸው ሰዎች የሚያራግቡት ጉዳይ ነው::

እነዚህ ሰዎች በፊት አዲስ አበባ እያሉ ሌሎች ለትግራይ ብለው ሲንቀሳቀሱ ለነበሩ አካላት እናንተ ጠባቦች ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ አማራጭ የውድቀትና የጥፋት አማራጭ ነው ሲሉ የነበሩ ዛሬ በአንድ አመት ውስጥ አጀንዳ ቀይረው እንገንጠል የሚል አጀንዳ ሲያመጡ በጣም የሚያሳፍር ነገር ነው ፤ የትግራይ ህዝብ ጠላቱ ድህነት ነው ከዚህ የሚያወጣው ፖሊሲ እና አማራጭ ሀሳብ ነው የሚያስፈልገው እነዚህ ሰዎች ግን ከእነሱ ውጭ ሌላ የትግራይን ህዝብ ሊመራ የሚችል ተተኪ አመራር ያለ የማይመስላቸው ናቸው፤ለዚያም የሃሳብ ልዩነት እና የሃሳብ የበላይነት የማያምኑ ናቸው ከድሮም ጀምሮ ልዩነቶች ይከሰታሉ የተሻለ ሃሳብ ያመጣውን ተቀብለህ ከዚያ ሃሳብ ትምህርት ወስደህ ለህዝብ የሚጠቅም ስራ መስራት ሽንፈት አይደለም ትክክለኛ መንገድ እና ዲሞክራስያዊ አካሄድ ይህ ነው!

የፖለቲካ ልዩነት ማለት ጠላት መሆን ማለት አይደለም ለውጡን ተቀብሎ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የሚቀላቀል የትግራይ ተወላጅ ይኖራል ሌላው ደግሞ እስካሁን የተኅዝነው የህወሃት ጉዞ ነው የሚያዋጣኝ ብሎ በነበረው መንገድ ሊቀጥል ይችላል ከዚያ ውጭ ግን ወደ ጥላቻ እና ጦርነት ለማምራት ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው ! የፓለቲካ ልዩነት እያለህ በአገር ልማት ጉዳይ አብሮ መስራት ይቻላል! የሚያዋጣውም እሱ ነው ወደ ሌላ ህገ-ወጥ እና ሀላ ቀር መንገድ ህዝቡን ለማስገባት መንቀሳቀስ ተቀባይነት የለውም ከጊዜው ጋርም አይሄድም ሀላፊነት የጎደለው አካሄድም ነው :: ፅንፈኛ ሁነህ ወደ ጥላቻ ህዝብን መምራት ውጤቱ ኪሳራ ነው ተገቢም አይደለም!!

በአጠቃላይ እኔ የማምነው የትግራይ ህዝብ የሚያዋጣው ከለውጡ ጋር በማበር እንደ ሁሉም ዜጋ የለውጡ ተጠቃሚ የሚሆንበት አማራጭ ማየት ነው:: አሁን የታየ ያለው ሀላ ቀር አስተሳሰብ ይዘው እኛ እናውቅልሃለን የሚሉ አካላት ሊታቀቡ ይገባል ይበቃል ልንላቸውም ይገባል:: ሌላው ነገር ማወቅ ያለብን የእኛ ሰዎች 27 ዓመት ሙሉ እኛ የምንፈልገውን ነገር ብቻ ስንተገብር በዚያ ተግባራችን ደስተኛ ያልሆነ እና ሂደቱ ያልተቀበለ ሰው ስላልነበረ አይደለም ህዝቡ በመቻቻል ስሜት አልፎን እና የሂደቱ አካል በመሆን በዲሞክራስያዊ አማራጭ ለውጥ ማምጣት ይቻላል በማለት ነው። ስለዚህ የትግራይ ህዝብን ሆን ተብሎ ስጋት ውስጥ ከማስገባት እና ነገሮችን እየለጠጥን ከማባባስ ከታቀብን አሁን በአገራችን የጨለማ ጊዜ ሳይሆን የብርሃን ጊዜ መኖሩን ይገለጽልናል።

ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅመው ይሄው ነው! አሁን ያለውን የብርሃን ዘመን እያጣጣምን ክፍተቶችን እየደፈን ከለውጡ ጋር አብረን መጓዝ ከቻልን ለትግራይም ለአገራችንም ልማት እና እድገት የሚጠቅመን እሱ ነው! ደካማ ጎን እና ክፍተት ብቻ እየቆጠርን ከሄድን መለወጥ አንችልም ስለዚህ በጎ አስተሳሰብ እና ቅንነት ካለን አሁን ያለው መንግስት የትግራይ ህዝብ ጠላት ነው የሚለውን የተሳሳተ ህዝብን የማደናገር አጀንዳ ትተን እንደ ዜጋ ከመንግስት ጋር ተባብረን ከሰራን ለውጥ ማምጣት እንችላለን!

ላለፉት አምሳ እና አርባ አመታት የተከተልነው አካሄድና አስተሳሰብ ብቻ ነው ትክክል ብለው ለሚያስቡት የድሮ አመራሮች ለዚህ ትውልድ ያላቸው ንቀት ነው የሚያሳየውና የአሁን ትውልድ እነሱ ከሚያስቡት በተሻለ የሚያስብ እንሱ ካመጡት ለውጥ የተሻለ ለውጥ ማምጣት የሚችል ብልህ ትውልድ ያለ መሆኑን አምነው ለወጣቱ ትውልድ ሀላፊነትማስረከብ አለባቸው::
አመሰግናለሁ!!