December 30, 2019

Posted by: ዘ-ሐበሻ

የኦሮሞ ፖለቲካ ሂደት፡ አሁን ሁሉም ለይቶለታል ተጠቃሎ አንድ ጎራ ገብቷል፡፡ እንዲህ ጥርት ብሎ እስከሚታየን ማመን ተስኖን ነበር፡፡ ምን አልባት ከኦሮሞ ፖለቲከኛ የተረፈ በሚል አሁንም ጥቂት ተስፋ እናደርግ ይሆናል፡፡ የምናየው እውነት ግን ብዙ የታመነባቸው ሳይቀር እያደር ያቺ መለስ ድሮ የተናገራት አንድ በአንድ እየሆነች ነው፡፡ ኦሮሞ ሲፋቅ ያላትን ነው፡፡ እኔ እንኳን ከበፊትም እውነቱን አውቀው ነበር፡፡ ግን በአንዳንድ ሰዎች እኔም ተሸውጃለሁ፡፡ በተረፈ ግን የኦሮሞ ፖለቲክስ ምንም ጥላቻና ዘረኝነት ዋና መሠረቱ ስለሆነ ለዘመናት ሕዝቡንም በዚሁ አስተሳሰብ ስለበከሉት አሁን ከሌሎች ጋር አብሮነትን የሚሰብክ ፖለቲከኛ ፋይዳ እንደሌለው ግልጽ ነበር ለኔ፡፡ ለዛም አደል ዛሬ ስልጣን ላይ ያሉት በኢትዮጵያ ምለናል ብለው በማግስቱ እዛው የኖሩበት የጥላቻና ዘረኝነት ሱሳቸው የሚመለሱት፡፡ ሱስ ይልሀል ይሄ ነው፡፡ መጀመሪያ በውዴታ ጥላቻንና ዘረኝነት ተቀብለው ስለተጠመቁ ከዚህ በኋላ ደህና እንሁን ቢባል እንኳን የሚለቅ ሱስ አይሆንም፡፡ በዋቃ ጉራቻ (የጥቁር አምላክ) አምልኮት ስነስርዓት (ኢሬቻ) ላይ ባልገደሉት ግዳይ ሲያስፎክራቸው የነበረውን አስታውሱ፡፡ ችግር አለ፡፡ ቄስ ቶሎሳ እንዳሉት ነው ነገሩ፡፡ እንግዲህ የማይገባውን ታደርግ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ ከተሰጠህ በኋላ ለማሰብ እሞክራለሁ ብትል እንኳን አይቻልህም፡፡ ለነገሩ የእነሱ ልክፍት ወደሌላው ተጋብቷል መሰለኝ ማስተዋል ጠፍቷል፡፡ እስር ቤት አስገብቶ ሲያማቅቀው የነበረውን ቡድን ሊሳለም በቀለ መቀሌ ድርስ የሄደ እለት ጤነኛ የሆነ ሁሉ በገባው ነበር፡፡

የሆነ ሆኖ አሁን መረራ በሱሱ ተጠልፏል፡፡ እንደተናገረውም ቆይቻለሁ ይላል፡፡ አሁን ብሶብኝ ነው እንጂ አይነት ይመስላል፡፡ ኢትዮጵያ ሱሴ ያለን ሰውዬ እኔ ቀንደኛ ደጋፊው ነበርኩ፡፡ ይችን ነገር እሱም ያቃታል፡፡ በእውነት ተሸውጄ እንጂ እንደሌሎች ነገሮችን ላለማጋነን በሚል ኦሮሞ ኢትዮጵያ ማለት ሲጀምር የምጨፍር ሆኜ አደለም፡፡ እኔ ኢትዮጵያ በቀደምት የኦሮሞ አባቶች እንደተገነባቸው አውቃለሁ፡፡ ዛሬ ግን አፍራለሁ! እኔ ሱሴ ያለውን ሰውዬ እስኪ ወዶ ላይሆን ይችላል ከሚል ትንሽ ጠብቄው ነበር፡፡ እንደውም እዛ ቤተመንግስት መናፈሻ ከሚሰራው በላይ አምነው ነበር፡፡ እንግዲህ ሁሉም ከኦሮሞ ፖለቲከኛ ኢትዮጵያዊነት ይመጣል ብሎ የሚያስብ ከአለ እየተሸወደ ነው፡፡ ምን አልባት በወያኔ ያልተጠመቀ ሌላ ቦታ የቆየ ካልሆነ፡፡ በነገራችን ላይ የኦሮሞን ፖለካን ንድፍ ያወጣችው ወያኔ ነች፡፡ያ ከአርሲ አሰላ ሲንጋፖር ከዛም አሜሪካ በወያኔ እየተደገፈ ዛሬ ደግሞ በግልጽ በአሸባሪነት ሥራ የተሰማረው ግለሰብ ወያኔ እንደቀጠረቸው እንዴት ሕዝብ ማስተዋል እንዳልቻለ ሳሰብ አዝናለሁ፡፡ የለንደኑንና የአትላንታውን ጉባዔ አስታውሱ፡፡ ወያኔ አደጋ ላይ በነበረች ጊዜ ነበር እነዛ ጉባዔያት የሕዝብን ትግል ለመበታተን ሆን ተብለው ወያኔን ለመታደግ የተደረጉት፡፡ መረራ ድሮም ላያዋጣው ብቻውን ለፋ፡፡ በስተርጅና መሆኑ ከፋ እንጂ፡፡

የኦሮሞ እስላማዊ አንቅስቃሴ፡- በኦሮሞ ፖለቲካ ከድሮ ጀምሮ የኦሮሞ እስላማዊ እንቅስቀሴ አጋጣሚ በአገኘ ቁጥር ኢትዮጵያንና ክርስትናን ለማጥፋት ሲሸምቅ ነበር፡፡ ደርግ አከርካሪው ሰብሮት የነበረው የኦሮሞ እስላማው እንቅስቃሴ በአሸባሪነት ቀደምት ነበር፡፡ እነ አላቃኢዳ ገና ሳይወለዱ ማለት ነው፡፡ ደርግ እንዴት እንደመታው ያውቃል፡፡ በባሌና ሀረር በዚያደባሬ ወረራ ጊዜ የነበረው እውነት ይሄ ነበር፡፡ ይሄን እውነት ብዙዎች አይረዱትም፡፡ ዛሬ በኦሮሞነት ተጠፈልፎ የገዛ ቤተሰቡን ለአራጆች እያስማማ ያለው በአርሲ፣ ባሌና ሐረር የተወለደ ክርስቲያን ኦሮሞ ይሄን እውነት አሳምሮ ያውቃል፡፡ እርግማን ውስት ስለገባ ግን ይክዳል፡፡ በቅርቡ በጥቅምት ወር በነበረው የአረመኔያዊ የሽብር ጥቃት ሰለባ ከሆኑት አብዛኛውም እንደተባለው ኦሮሞ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡ የሚገርመው አንድ አርሲ የሆነ ግን የሽብር ቡድኑ ዋና የሆነው የወያኔው ቅጥር ቀንደኛ ደጋፊ የሆነ አሜሪካ የሚኖር የጴንጤ ሰባኪ አባቱን በአረመኔዎች ማጣቱ ሳይገርም በኋላ ሰዎች ለአሜሪካ መንግስት ለምስክርነት ቢጠይቁት ጌታ ያለው ሆነ በሚል እምቢ ብሏል፡፡ ለሌሎች በአለው የጥላቻ ልክ ሲጨፍርለት የነበረው ቡድን በገዛ አባቱ እንኳን መጥቶ ሊሰማው አልቻለም፡፡ እንዲህ ነው የምትሆነው!

ሰሞኑን የሞጣ መስኪድ መቃጠል የሚገርም ትዕይንት እያሳየን ነው፡፡ በነገራችን ለዚህ መስኪድ መቃጠል ምክነያት (ወይም በቀጥታም ገና እያጣራን ነው) ከሌላ ቦታ የተላኩ ሙስሊሞች ናቸው የሚል መረጃ ደርሶኛል፡፡ አስገራሚው ነገር ይሄው ቁማር ከበፊቱ የሙስሊም እምነት መከፋፈል ጋር መገናኘቱ ነው፡፡ አህመዲን ጀበል የተጋለው ግለሰብ በግልጽ ከኦሮሞ እስልምና አሸባሪዎች ጋር እየሰራ እንደሆነ መሪጃዎች እየወጡ ነው፡፡ በቤተክርስቲያኑ ላይ ሙከራ ከመደረጉና ከመስኪዱ መቃጠል በፊት አስቀድሞ መረጃው የደረሳቸው የአካባቢው ሙስሊሞች ለክልሉም ለአካባቢውም አስተዳደር ጥበቃ እንዲደረግ አሳሰብው እንደነበር መረጃዎች ይናገራሉ፡፡ አንድስ ቢሆን ለምን ተቃጠለ? የተቃጠለውም መስኪድ አንድ ብቻ እንደሆነ ነው ከቦታው የገኘኋቸው መረጃዎች የሚናገሩት፡፡ ስለዚህ ዝርዝር አልገባም ሲጣራ እንሰማለን፡፡ ሌላ ሚስጢር ስላለ፡፡ የሆነ ሆኖ የኦሮሞ እስላማዊ አክራሪ ቡድላን አጋጣሚውን ተጠቀሞ ብዙ ትዕይንት አሳይቶናል፡፡ ትልልቅ ጉዶችን እያወጣም ነው! የድምጻችን ይሰማ በሚል ብዙ ክርስቲያን ሳይቀር ሲደግፈው የነበረ ቡድን አንዳንድ አባላት አሁን እያሠሩ ያለውን ላስተዋል በፊትም በትልቅ ሴራ ውስጥ እንደነበሩ የሚጠቁም ነው፡፡ የሆነውን በቀጥታ ከቦታው ላይ በራሳችሁ ለማወቅ ሞክሩ፡፡ እንዲህ ይላል አንዱ የአህመዲን ጀበል ፌስቡክ ላይ የለጠፈውን ያወናበረው፡፡ አንዷ ክርስቲያን በአንዲት ሙስሊም እናት ቤት ተከራይታ ስትኖር ከቀን በፊት እናንተ ተዘጋጅቶላችኋላ ብላቸው ቤት ትለቃለች ከዛ አሁን ይሄ ከሆነ ኋላ እዛው መጥታ እኚህ እናት ምነው ሳትነግሪኝ ይሏታል…. የሴትዮዋም፣ የልጅቱም ምስልም ድምጽም የለም፡፡ ይሄን ቪዲዮ ስትመለከቱት ቦታው ላይ ቀረጽኩ የሚለው ግለሰብ ራሱ በሚፈልገው ያወራል፡፡ ግለሰቡ እሱ እንደሚፈልገው ሰዎቹን ቢጠይቅም ሰዎቹ ባብዛኛው የሚያወሩት እሱ ከሚለው የተለየ ነው፡፡

ለዚህ ሁሉ ተጠያቄው ማን ነው ነው? የሚከተሉትን ጉዳዮች አስተውለሉ

  1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የአገሪቱ ትልልቅ የገንዘብ ተቋማት እየተመሩ ያለት በማን ነው? የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኢኮኖሚያዊ ክስረት ስጋት ይልቅ የደህንነት ስጋት እንደሚሆን ከዚህ በፊት ጠቁሜ ነበር፡፡ ሥራ አስኪያጁ ከአዋሽ ባንክ ምክትሉ ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ  ነው የመጡት፡፡ ይህ ባንክ በተደጋጋሚ በዘረፋ ስም ለአሸባሪዎች ገንዘብ ሲያስተላለፍ ነበር፡፡ አሁንም በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አናውቅም፡፡ ሆኖም አሁን ይህ ባን ለአሸባሪዎች የገንዘብ ዝውውር እየዋለ እንደሆነ እናስባለን፡፡
  2. በየቦታው በሠላማዊ ሠልፍ እየተባለ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፡ ይሄን ጉዳይ አስተውሉ፡፡ ሠላማዊ የሚባለው በቆንጨራና ገጀራ የሚዝቱ ናቸው፡፡ ሰሞኑን በዚሁ የኦሮሞ አሸባሪዎች በሚንቀሳቀሱበት ክልል አንድ ሌላ አስቂኝ ትዕይንት ተመልክተናል፡፡ ግማሹ ሰላማዊ ሰልፍ በሚል መንግድ ላይ ወጥቶ ሌላው እጅ ለእጅ ተያይዞ የቤተክርስቲያን ጠባቂ ለመምሰል ሲሞክር አይተናል፡፡ ሲጀምር ሰላማዊ ከሆነ ቤተክርስቲያኑን መጠበቅ ለምን አስፈለገ፡፡ ሊያቃጥሉ ያሰቡ አሉ ለማለት ነው? በጠራራ ጸሐይ ነው፡፡ የእስላማዊ አክራሪው ቁማር ግን እንዲህ አደለም፡፡ ዶዶላ ላይ እኮ ግልጽ አይተናል፡፡ ቤተክርስቲያን ማቃጠል ስለሚያሳጣ ክርስቲያኖቹን ከገደልንና ከጨረስን ቤተክርስቲያኑ ባዶ ስለሚሆን ቤተክርስቲያን በማቃጠል ለምን የፖለቲካ ኪሳራ እንከስራልን ነው ቀመሩ የእነ አህመዲን ጀበር ስልት ነው፡፡
  3. ማንም እንደፈለገው ሕዝብን ሰብስቦ ለዓመጽ ማስነሳት፡- ይሄን ጉዳይ ከጅምሩ ተናግሬ ነበር፡፡ የሚገርመው ከአመት በፊት አደገኛ የሆነ የሀይማኖት ግጭት ሊነሳ እንደሚችል ጠቁሜ ነበር፡፡ በግልጽ የኦሮሞ መንግስት ለአሸባሪዎች በጀት መድቦ በየቦታው እየሄዱ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ነበር፡፡ ይሄን ዛሬ ቤተመንግስት ያለው ሰውዬ አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ሲጀምር እሱ ራሱ ነው ዛሬ ለእነዚህ አሸባሪዎች የገንዘብ ዝውውር በሚመች ሁኔታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክንም ሰዎች የሰየመው፡፡

ኢትዮጵያውያን እነዚህን መጥፎ አጋጣሚዎች ወደጥሩ ለመቀየር ዋሳኝ ጊዜያቸው ነው፡፡ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ዋናው ቁማር ከበፊት የቀጠለ ነው፡፡  በተለይ በእምነት ምክነያት እየተቆመረ ያለውን ቁማር በትኩረት እዩ፡፡ ሕዝቡን በምን እንደሚያጋጩት ብዙ ሞክረዋል፡፡ አሁን ቤተክርስቲያንና መስኪድ በማቃጠል የሀይማኖት ብጥብጥ እንዲነሳ ትልቅ ሴራ እየተሰራ ነው፡፡ የሙስሊም ድምጻችን ይሰማ ጊዜ ብዙ ክርስቲያኖች ከሙስሊሙ ጉን ቆመው ነበር፡፡ ያ ድምጻችን ይሰማ የሚለው ቡድን ዛሬ ምን ያህል በትክክልም ለፍትህ እንደቆመ አላውቅም፡፡ ከዛ ከድምጻችን ይሰማ ትልቅ እውቅና በሕዝብ ዘንድ ያገኙ አንዳንዶች የተደበቀ ሴራቸውን አሁን በከፍተኛ ፍጥነት እያስኬዱት ነው፡፡ አህመዲን ጀበል የተባለው ግለሰብ በግልጽ አካሄዱ ማን እንደሆነ እያሳየ ነው፡፡ የሞጣው ቅንብር ብዚሁ ግለሰብ በሚመራ ቡድን የተቀነባበረ ነው (መረጃው ሙሉ በሙሉ ሲደርሰኝ እነግራችኋለሁ) ፡፡ ይሄን ግለሰብና አጋሮቹን እየሰማችሁ የምትጦዙ ሙስሊሞች ተጠንቀቁ፡፡ ዛሬ በሞጣ አንድ መስኪድ ተቃጠለ፡፡ ከዛ በፊት በእሰቴና አካባቢ ተመሳሳይ ችግር ነበር፡፡ ያኔም ሙከራው የነበራው የሙስሊሙንና ክርስቲያኑ ለማናከስ ነበር፡፡ በጎንደር ሙስሊሙንና ክርስቲያኑ አንድ ስለሆነባቸው አልተመቸም፡፡ ጎንድር ከማንም በላይ በጥንቃቄ የሚሄድ ሕዝብ ነው፡፡ ወያኔን ወገቡን ሰብሮ የጣለው ጎንደር እንደሆነ ወያኔና አጋሮቿ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ በዛው ልክ ብዙ ሴራ ቢሸርቡም አልቻሉትም፡፡ ከጎንደሮች ብዙ መማር ይቻላል! በጥቅምት ወርና ከዛም በፊት በብዙ ቦታዎች ቤተክርስቲያን ተቃጠለ፡፡ ለሁለቱም ጥፋት ምንጩ ግን አንድ ነው፡፡ በተለይ ከኦሮሞ ውጭ ያላችሁ ሌሎች ሙስሊሞች በማታውቁት ሴራ በሙስሊምነት ብቻ አትጠመዱ፡፡ አሁን የማየው የመስኪዱ መቃጥል ሳይሆን ነገሮችን ለማጦዝ ነው፡፡ ጉዳዩ ምርመራ ላይ ነው፡፡ በክርስትናው እንደልባቸው እየዘወሩት ብዙዎች መኖሪያ ማድረጋቸው ሳያንስ አሁን በሰፊው ሌላ ቁማር ጀምረዋል፡፡ የእምነት ጉዳይ በመግለጫና ሠላማዊ ስለፍ በሚል አደባባይ እየወጡ መደንፋትን አይጠይቅም፡፡ የሚያምን ቢኖር፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ወደዘር ከዘር ደግሞ አሁን ወደ ሀይማኖት ገብቷል፡፡ ሁሉም ይንቃ!

ቅዱስ እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አገራችንን ይታደግ! አሜን!

ሰርፀ ደስታ