December 31, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/191990
ኢዜማ አዳማ/ናዝሬት ምርጫ ወረዳ ሁለት ጽ/ቤት የኢዜማ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት መርቀው መክፈታቸው ይታወቃል ።
ይሁን እንጂ የአዳማ ከተማ ኦዳ ቀበሌ ጽ/ቤት ሊቀመንበር በክፍለከተማ ተዝዤ ነው በማለት ጽ/ቤቱን እንዲንዘጋ፣ በጽፈት ቤት ውስጥ የለጠፍናቸውን የድርጅቱ ሎጎዎችን ፣ ባንዲራችን እና ማንኛውንም ምልክት እንድታጠፉ በማለት አዘውናል ።
“በኔ ጥላ ስር ናቹሁ” ብለውም በህግ ጥላ ስር መኖራችንንም ረስተው ዝተውብናል።
በመሆኑም ይህ ጉዳይ ይመለከተናል የሚል አካል በአስቸኳይ እልባት የማይሰጥበት ከሆነ በአንድ የቀበሌ አመራር ምክንያት የፓለቲካ ምህዳሩ ሙሉ በሙሉ መዘጋቱን ለአለም ህዝብ አሰውቀን እንቅስቃሴ ለማቆም እንገደዳለን።
Source – አዳማ -የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ