December 31, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/191996
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/CE38D46E_2_dwdownload.mp3
ከተወሰነ የኮንፈረንሱ ክፍል ውጪ ጉባኤው ለጋዜጠኞች ዝግ ነበረ፡፡
DW : ቅዳሜና እሁድ መቀሌ ውስጥ የተካሄደው የህወሀት ጉባኤ ተሳታፊዎች የኢህአዴግ መፍረስ ሕገወጥ አካሄድ ነው ሲሉ አወገዙ። ድርጅቱ በተለያዩ ፖለቲካዊ አጀንዳዎች ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ ከፓርቲው አባላትና አባል ያልሆኑ የተለያዩ የማሕበረሰብ ክፍል ተወካዮች የመከሩበት የዚህ ህዝባዊ ጉባኤ ተሳታፊዎች ውሁድን ፓርቲ ብልፅግናንም እንታገለዋለንም ብለዋል፡፡ የህወሓት ሊቀ መንበር ዶክተር ደብረፅዮን በጉባኤው ላይ ባሰሙት ንግግር የትግራይን ሰላምና የህዝቡን አንድነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የውስጥ ኃይሎች ያሏቸው መኖራቸውን ጠቅሰው እርምጃ ይወሰድባቸዋል ብለዋል፡፡
► መረጃ ፎረም – JOIN US