

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
አበበ አይነኩሉ ማን ነው??
በወያኔ ታፍነው ደብዛቸው የጠፋው ኢሕአፓዎች ከብዙ በጥቂቱ!!
1. ፀጋዬ ግ/ መድህን (ደብተራው)
2. ስጦታው ሁሴን
3. በለጠ አምሃ
4. አበራሽ በርታ
5. ለማ መኮንን
6. ይስሃቅ ደብረ ፅዮን
7. ወንዱ ሲራክ ደስታ
8. ኢንጂነር አበበ አይነኩሉ( የሰራተኛ መሃበር)
9. ሃጎስ በዛብህ
10. ብርሃኑ እጂጉ ( ጆርናሊስት)
11. ከበደ ተስፋዬ
12. ሌውተናንት አዱኛ
13. ታምራት ግዛቸው
14. ደሳለኝ አምሳሉ
15. እዮብ ተካበ
16.ደምሴ ተስፋዬ
17. ጌታቸው አበበ
ሌሎችም በርካታዎች…….
አበበ አይነኩሉ በጠንካራ ሃይማኖትና ኢትዮጵያዊ መሰረት ላይ ከታነፀ ቤተሰብ ከአባቱ ከአለቃ አይነኩሉ መርሻ ተወልዶ፤ ለህዝብና ለሀገር ሉአላዊነት ዘብ በመቆም ፤ በኢሕአፓ ስር ተደራጅቶ ሲታገል፤ በዘረኛውና አፓርታይዳዊው ወያኔ ታፍኖ በመወሰድ ደብዛው የጠፋ እንቁ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው።
በሙያው ኢንጅነር የነበረው አበበ አይነኩሉ፤ የባሓር ዳር ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ምክትል ስራ አስኪያጅና የሠራተኞች ማሃበር አባል በመሆን ፤ በወያኔ ታፍኖ እስከተወሰደበት ድረስ የሠራተኛውን መብት ለማስከበር ሲታገል፤ የወያኔን ደባ ሲያጋልጥና ሲታገል ቆይቷል።
በህዳር 24 ቀን 1986 ዓ.ም ወንዱ ሲራክ ደስታን ጨምሮ ከሌላ 3 ጓዶች ጋር ከብሃር ዳር ታፍነው ተወስደው እስከዛሬ የገቡበት ሳይታወቅ ደብዛቸው ጠፍቷል።
ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!
ለህግ የበላይነት፤ ለሰላም ለዴሞክራሲና ለ እኩልነት..
ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!