እረፍ! ተመለስ! ተጠቀንቀቅ! በሉት!!!

ወገኖቸ እጅግ አርሬያለሁ ተቃጥያለሁ!!!

እስክንድር ነጋ ከአብን ጋር የቅንጅት ፓርቲ ለመመሥረት እንደጨረሰ መረጃ ደርሶኛል፡፡ የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል!” አሉ አበው፡፡ እስክንድር ይሄንን ሊያደርግ እንደሚችል በእጅጉ ስፈራ ነበር!!!

እንደምታስታውሱት እነ እስክንድር ባለአደራ ምክርቤቱን ወደ ፓርቲ ሊያሳድጉት ወይም አዲስ አበባ ላይ አተኩሮ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ ሊመሠርቱ እንደሆነ እንዳስታወቁ እንዲህ ማሰባቸው በጣም ጥሩና አስፈላጊ መሆኑን ገልጨ ነገር ግን ፓርቲውን በአዲስ አበባ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ የፖለቲካን ስሌት አለማወቅ መሆኑንና አዲስ አበባን ማሸነፍ ቢቻል የተቀረው የሀገሪቱ ክፍል በአገዛዙና በቅጥረኞቹ እስከተያዘ ጊዜ ድረስ ሊመጣ የሚችል ለውጥ አለመኖሩን በማስገንዘብ ፓርቲው ከተመሠረተ ሀገር አቀፍ መሆን እንዳለበት፣ ሥያሜያቸውንም ኢትዮጵያዊነት!” ቢሉት ተስማሚ መሆኑን ገልጨ በዚሁ በሶሻል ሚዲያ አሳስቤ ነበር!!!

ከዚያም እስክንድር ይሄንን ሐሳብ በመጋራት ሚዲያ ላይ ወጥቶ የሚመሠርቱት ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ ብቻ አተኩሮ እንዲንቀሳቀስ ቢመሠረት ከአዲስ አበባ ውጭ የሚኖረው ሁኔታ የተለየ የሚሆን ከሆነ ለውጥ የማይመጣ መሆኑን ገልጾ ፓርቲው ሀገር አቀፍ ፓርቲ እንደሚሆን ተናግሮ ነበር!!!

አሁን ደግሞ እንደገና ወደኋላ ተመልሶ ፓርቲው በአዲስ አበባ ላይ ብቻ የሚወዳደር መሆኑን እየገለጸ ነው፡፡ እስክንድር ወደኋላ የተመልሰበት ምክንያትም ቅጥረኛው አብን እስክንድርን የእናንተ ማኅበራዊ መሠረት (constituency) እና የአብን ማኅበራዊ መሠረት አንድ በመሆኑ ላለመደራረብ (over lap) ላለማድረግና አቅምና ዕድልን ላለማባከን የቅንጅት ፓርቲ መሥርተን የእናንተን ፓርቲ አዲስ አበባ ላይ እንዲወዳደር በማድረግ፣ አብንን ደግሞ ከአዲስ አበባ ውጭ ባለው እንዲወዳደር በማድረግ፣ ሌሎች አካባቢዎችንም ተቀራራቢ አቋም አመለካከት ያላቸውን ፓርቲዎችን እንዲቀናጁንና በኮንስቲቱዌንሲያቸው እንዲወዳደሩ በማድረግ መንግሥት መመሥረት የሚያስችለንን የወንበር ቁጥር በማግኘት መንግሥት እንመሠርታለን!” ብለው ስላጃጃሉት እንደሆነ ሰምቻለሁ!!!

እስክንድር አብንን የሚያስበው ትክክለኛ ለአማራና ኢትዮጵያን ለሚል የኢትዮጵያ ሕዝብ የቆመ ድርጅት አድርጎ ነው፡፡ ሸፍጠኛው ሴረኛው የወያኔ ባሪያ ፀረ አማራው ብአዴን ለሸፍጠኛ ተልእኮው ወይም ለዓላማው ካድሬዎቹን አደራጅቶ የመሠረተው ድርጅቱ መሆኑን አያውቅም!!!

ብአዴን እንዴት አድርጎ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕልም በእንጭጩ እንደቀጨው አያቹህ አይደል??? ማንም መገመት እንደሚችለው ይሄ የእነ እስክንድር ፓርቲ በምሁራን የተሞላ ሆኖ ቢመሠረትና በሀገር አቀፍ ደረጃም የሚወዳደር ቢሆን ብቸኛው በኢትዮጵያ ሕዝብ ወይም silent majority ተብሎ በሚጠራው ድምፁ በማይሰማውና ከነአካቴውም ያለ በማይመስለው ነገር ግን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛውን ቁጥር በሚይዘው የኢትዮጵያ ህልውናና አንድነት ፈጽሞ አደጋ ላይ እንዳይወድቅ በሚፈለገው ሕዝብ ታምኖና ተወዶ የሚመረጠው ብቸኛው ፓርቲ ይሄ የእነ እስክንድር ፓርቲ ነበር የሚሆነው!!!

አገዛዙ ይሄንን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ለዚህ ዓይነት ስውር ተልእኮ ያዘጋጀውን ቅጥረኛ ድርጅቱን አብንን ከላይ የገለጽኩላቹህን ነገር እንዲለውና እንዲጃጃል በማድረግ እስክንድር የሚመሠርተውን ፓርቲ በአዲስ አበባ ብቻ እንዲወሰንና የእነ እስክንድር ፓርቲ መንግሥት መሆን የሚችልበትን ዕድል እንዲያጣ አድርጎታል፡፡ ፓርቲያቸውንም ከሽንፈት መታደግ ችለዋል፡፡ አያሳዝንም??? ቅስም እንክት አያደርግም??? እስክንድር ግን ምን ነክቶት ነው??? ለብአዴን አስበልቶናል ስላቹህ!!! እባካቹህ ይሄንን ሰውየ ሳይመሽና ሳያስበላን በፊት ምከሩት አንቁት???

ይሄንን ስላቹህ ነጻ ተአማኒና ፍትሐዊ ምርጫ ይደረጋል!” እያልኩ አይደለም፡፡ የምንመርጠውና ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በንቃት የሚሳተፉት ነጻ ተአማኒና ፍትሐዊ ምርጫ ቢደረግ የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርጫ ምን ሊሆን እንደሚችል ለማሳየትና አገዛዙ ነጻ ተአማኒና ፍትሐዊ ምርጫ ፈጽሞ እንደማያደርግ እንዳላደረገም ለማጋለጥ ነው!!!

በዚህ አጋጣሚ እነ እስክንድር እየመሠረቱት ያሉትን ፓርቲ ባልደራስ ብለው እንደሠየሙት ስለሰማሁ በዚህም ጉዳይ ማለት የምፈልገው ነገር አለ፡፡ እናንተየ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ስለ ኢትዮጵያ እንሞታለን!” በሚሉትም ተገለለ ተጠላ ማለት ነው እንዴ???

ወይ ጉድ! “አፍ ሲያመልጥና ጸጉር ሲመለጥ አይታወቅም!” አሉ!!! እንግዲህ እነ እከሌ ይቀየማሉ!” እያልን ኢትዮጵያ ከሚል ስምና ኢትዮጵያዊ ከሆነ እሴት ሁሉ ስንርቅ ከማንነታችን ጋር ተረሳስተንም ልንቀር ነው ማለት ነው??? ከዚህ በላይስ ለፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ኃይሉ ድል አለ እንዴ???

የእነ እስክንድር የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክር ቤት!” በሚል የሚንቀሳቀሰው የአዲስ አበባና የሕዝቧ መብት ተሟጋች ማኅበር ባጭሩ ባልደራስ!” እየተባለ የሚጠራበት ምክንያት ማኅበሩ በተመሠረተበት ዕለት በባልደራስ የስብሰባ አዳራሽ በመሰብሰቡ እንደሆነ የምታውቁት ነው፡፡ ማኅበሩን የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት!” ብሎ ለመጥራት ረዝሞ የታያቸው ሰዎች ናቸው ባጭር ለመጥራት ሲሉ ባልደራስ ብለው በተሰበሰቡበት አዳራሽ ስም መጥራት የጀመሩት፡፡

ባልደራስ የሚለው ቃል ትርጉም የቤተመንግሥት ፈረሶችን የመንከባከብ ኃላፊነት የተሰጠው ተሿሚ ማለት ነው ሌላ ትርጉም የለውም፡፡ ያ አዳራሽ የባልደራስ አዳራሽ የተባለው ቀደም ባለው ታሪካችን ቦታው የቤተመንግሥት ፈረሶች ማረፊያና መንከባከቢያ ቦታ ስለነበር ነው፡፡

አሁን እንግዲህ ታዲያ የፓርቲን ስም ባልደራስ!” ብሎ መሠየም ምን ይሉታል እስኪ??? የቤተመንግሥት ፈረሶችን ተንከባካቢ ተሿሚዎች ፓርቲ ማለት አይሆንም ወይ??? ካልጠፋ ስምስ ለምን??? ከማንነታችን ጋር የተሳሰረ ስም ካስፈለገስ ስንት የከበረ ስም በሞላበት ሀገር ባልደራስ የሚል ስም ይመረጣል??? እውነት ባልደራስ የሚለው ስም ተስማሚና ተመራጭ ሆኖ ነው ወይስ የኢትዮጵያየሚል ስምን ሽሽት???

ይሄንን ስምም እንዲሁ እንዲያስተካክሉ ንገሯቸው፡፡ ቄሮና ኦነጋውያን እንደሆኑ እነ እስክንድር ፓርቲያቸውን ባልደራስ አይደለም ቄሮ ወይም ፊንፊኔ ቢሉላቸው እንኳ ሊመርጧቸው አይደለም ፈጽሞ ሊያዩዋቸው እንኳ እንደማይፈልጉ ግልጽ ነው፡፡ የልቅስ ባልደራስን ባልዲራስ እያሉ ማሾፊያ እንዳያደርጉት ነው የምፈራላቸው፡፡ ስለሆነም የፀረ ኢትዮጵያ ኃይሉን ላለማስከፋት በሚል ስሌት በየቦታውየተያዘው ከማንነታችንና ከሰንደቃችን የመሸሽ አባዜ ፍጹም የተሳሳተና በአስቸኳይም መታረም ያለበት መሆኑን አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com