January 7, 2020
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/100193
በግሎባል ፋየር ፓወርስ ጥናት መሠረት፣ በአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ ወታደራዊ ተቆም የገነቡ አምስት አገራቶች ውስጥ በአንደኛ ደረጃ ግብፅ ስትሆን፣ሁለተኛ አልጀሪያ፣ ሦስተኛ ሳውዝ አፍሪካ፣ አራተኛ ናይጀሪያ እንዲሁም አምስተኛ ደረጃ ኢትዮጵያ መሆናቸውን ግሎባል ፋየር ፓወርስ (Global Firepower’s 2019 Military Strength ranking) በ2019 እኤአ ወታደራዊ ጥንካሬና ደረጃ እንዳላቸው ገልፆል፡፡
ግሎባል ፋየር ፓወርስ ጥናት 50 ወታደራዊ መለኪያዎችና የብሔራዊ ኃይል መሥፈርቶች (Nation’s Power Index Score) ውስጥ ትኩረት ያደረገው በየአገሮቹ ያለ የመሳሪያ ክምችት ዓይነት፣ ጥራትና ዘመናዊነት፣ የሠለጠነ ወታደራዊ የሰው ኃይል፣ የሥነ መልክአ ምድር ስትራቴጂክ አቀማመጥ፣ ወታደራዊ ስንቅና ትጥቅ አቅርቦት እንዲሁም የተፈጥሮ ኃብት ወሳኝ መለኪያዎች ናቸው፡፡ አምስቱ የአፍሪካ ሃገራት ከፍተኛ ወታደራዊ ተቆም የገነቡ ሃራት ሲሆኑ በውትድርናው መስክ ሃገር በቀል ወታደራዊ መከላከያ ኢንዱስትሪ በመገንባት መሪነቱን ለመጨበጥ ችለዋል፡፡ ወታደራዊ መለኪያዎችና መሥፈርቶች ውስጥ ዋናዎቹ ተዋጊ የጦር አውሮፕላን፣ ተዋጊ ታንኮች፣ የባህር ኃይል፣ የመከላከያ ባጀት አንኮሮቹ ናቸው፡፡
በ2018 እኤአ ኢትዮጵያ በአፍሪካ የሦስተኛ ደረጃ የነበራት ሲሆን በ2019 እኤአ ወደ አምስተኛ ደረጃ ዝቅ ብላለች፡፡ በተመሳሳይ አመተምህረት ደቡብ አፍሪካ ከአምስተኛ ደረጃ ወደ ሦስተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች፡፡
ግሎባል ፋየር ፓወርስ ጥናት መሠረት፣ ወታደራዊ የኃይል አመዳደብ ደረጃ (Power Index Score is 0.0000) ሊደረስበት የማይችል መለኪያ ሲሆን ወደዚህ አሃዝ በደረሱና በተጠጉ ቁጥር የአገሮች መከላከያ ኃይል ጥንካሬን ያረጋግጣል፡፡
አምስቱ ኃያላን የአፍሪካ አህጉር ወታደራዊ ኃይል ተቆማት በ2019እኤአ
These are the 5 most powerful militaries in Africa in 2019
የውጭ አንበሣ የውስጥ እሬሳ!!! የህወሓትና ኦነግ ሽብርተኝነትና የፖለቲካ ሴራ
- ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ መንግሥት የ4 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የጦር አውሮፕላኖች፣ የውጊያ ሂሊኮፕተሮች፣ ሚሳኤሎችና የጦር መሳሪያ በብድር ለመግዛት ጠይቃለች፡፡
- የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት ጉዳዬች አማካሪ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ መግለጫ መሠረት፣ የኢትዮጵያ የባህር ኃይል የሚታጠቀው የጦር መሣሪያ ዓይነትና ተዋጊ የጦር መርከቦች ዲስትሮየር፣ ኬረር፣ ሜትሮ ሃይል ወይም ቀላል ሃይል ወይም አጃቢ ሃይል የሚለው ጉዳይ ገና በጥናት ላይ እንዳለና ባህር ኃይሉ መሠረቱን በጁቡቲ ወይም በኤርትራ ባህር ለመጣል አስቦ ከጁቡቲ ባህር መልህቁን ጥሎል ተብሎል፡፡ የቀ.ኃ.ሥና የደርግ መንግሥት ዘመን የነበረው የኢትዮጵያ ባህር ኃይል መርከቦችና የጦር ተዋጊ ጀልባዎች ወዘተ ህወሓት/ ኢህአዴግ የት እንደሸጣቸው መጠየቁ ቀረና ያለ ባህር ባህር ኃይል ይሉናል የድንጋይ ዳቦ ዘመን ፖለቲከኞች፡፡ የኢትዮጵያ የባህር ሀይል (ከ1955 እስከ 1990) ድረስ ነበረ፡፡ ኢምፔሪያል ኢትዮጵያን ኔቪ 81 መርከቦች ነበሩት እነሱም ፓትሮል ቦትስ፣ ቶርፒዶ ቦትስ፣ አነስተኛ ስብመርሲብል (ባህር ሰርጎጂ) ቦትስ፣ ተዋጊ መርከቦች በምፅዋ ወደብ ነበራት፡፡ የመርከቦቹ እጣ ፈንታ ምንሆነና ሌላ መርከብ ያለ ባህር በር እንዴት!!! በወርቃማው ዘመን ቀ.ኃ.ሥ ኮማንደር ኢን ቺፍ የነበሩ ሲሆን፣ ሪል አድሚራል እስክንድር ደስታ ምክትል ኮማንደር ኢን ቺፍ ነበሩ፡፡
- የኦሮሚያ ክልል መንግሥት 10 ሽህ ልዩ የፖሊስ ኃይል አሰልጥኖ አስመርቆል፡፡ በትግራይ ክልል ልዩ የፖሊስ ሃይል፣ ሚሊሽያና መከላከያ ሠራዊት የፌዴራል መንግሥቱን በመጋፋት ተገንጥሎ በሽብርና ፖለቲካ ሴራ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ በፌዴራል መንግስት፣ የአብዲ ኢሌ የሱማሌ ክልላዊ መንግሥት 40 ሽህ ልዩ ኃይል ከተመታ በሆላ የአማራ ክልል 5 ሽህ ልዩ የፖሊስ ኃይል አሰልጣኝና መሪ ጀነራል አሳምነው ፅጌ መደምሰስ በኃላ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት 10 ሽህ ልዩ የፖሊስ ኃይል አሰልጥኖ አስመርቆል፡፡ የሠራዊቱን አወቃቀር ከአንዱ ብሄር ወደ ሌላ ብሄር የማዘዋወር የተረኝነት ስሜት ካለፈው አለመማር መሆኑን መገንዘብ አልታደልንም፡፡ ‹‹አርበኞች ግንቦት 7›› በነካ እጃቸው የወያኔን የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች ስም ዝርዝር እንዳጋለጡ ዛሬም ያለውን የኦዴፓ/ ብልፅግና ፓርቲ የኦነግ የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች መረጃ እንዲያቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
- ኢትዮጵያ ከዓለም የገንዘብ ድርጅት አና ከዓለም ባንክና የልማት አጋሮች 8.9 ቢሊዮን ዶላር ብድርና እርዳታ ዕዳ እንደተሰፈረላት በኩራት የብልጥግና ፓርቲ ፕሬዜዳንት ሎሬት ዶክተር አብይ አህመድ በኩራት ለኢትዮጵያ ህዝብ አብስረዋል፡፡
- የኢትዮጵያ ዕዳ 52 ቢሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን ከአሁኑ 8.9 ቢሊዮን እና ከ4 ቢሊዮን ዶላር የጦር አይሮፕላን ግዢ ጋር ስንደመር 64.9 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ በጥናት አረጋግጠናል፡፡ የቻይና መንግሥት ከ 17 እስከ 20 ቢሊዮን ዶላር በማበደር የአንበሳ ድርሻውን በመቀራመት በአዲሱ ፕራይቬታይዜሽን ቅርምት የኢትዮጵያ ዓየር መንገድን፣ ኢትዮቴሌኮም፣ የንግድ መርከብ ድርጅትን፣ የባቡር ኮርፖሬሽን፣ ወዘተ መውስዱ ገሃድ ሃቅ ሆኖል እንላለን፡፡
ምንጭ፡-
- https://www.Global Firepower’s 2019 Military Strength ranking) በ2019
- https://en.wikipedia.org/wiki/Ethiopian_Navy