January 2, 2020
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
በአሁኑ ሰዓት ህወሐት እያስተዳደረው በሚገኘው በማይፀብሪ ወረዳ ካድሪዎች ከፍተኛ ጣልቃ ገብነት እየተፈፀመበት እንደሆነ ከሚነገርለት በዋልድባ አብንረንታት ቤተ ሚናስ ገዳም የሚገኙ መነኮሳት በአማራዊ ማንነታቸው እየተጠቁ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል።

ይኸውም ታህሳስ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ህወሐት ያሰማራቸው የማይፀብሪ ወረዳ የፀጥታ አካላት እማሆይ ወለተ መድህን፣መናኝ ገ/ማርያም እና አባ ገ/ማርያምና ሌሎችን ወደ ማይጋባ ቀበሌ አስረው መውሰዳቸው አይዘነጋም።
የመጀመሪያው የገዳም መጋቢ የነበሩትን አባ ገ/ማርያምን ብቻ ነጥለው ማይጋባ ላይ በማሰር ሌሎችን በሁለት ቀን ውስጥ ገዳሙን ለቀው እንዲወጡ አስፈርመዋቸዋል ሲሉ ያነጋገርናቸው አባት ተናግረው ነበር።

ይህን ተከትሎ በዛሬው እለት ታህሳስ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከወንዶች አባ ወልደ ሚካኤል፣አባ ወልደ ማርያም እና መናኝ አባ ገ/ማርያም፣ ከሴቶች ደግሞ እማሆይ ወለተ ማርያም፣ እማሆይ ወለተ መድህን፣እማሆይ አመተ ማርያም እና መናኝ ወለተ ማርያም ከአብረንታንት ገዳም እንዲወጡ መደረጉ ታውቋል።
መነኮሳት አማራ በመሆናቸው ብቻ የተከበሩ የገዳም መነኮሳትን “ሽፍታ ናቹህ፣ከፋኖ ጋር ትገናኛላችሁ፣ሰላይ ናቹህ” እየተባሉ ከህወሐት አመራሮች ጋር በመገናኘትና በማባረር የተወቀሱት አባ ገ/ህይወት መስፍን በቅፅል ስማቸው ሻምበል ገ/ህይወት፣አባ ሰላማ ገብሩ፣አባ ወልደ ህይወት እና የህፃኑ ማርያም ገበዝ አባ ወልደ ዮሀንስ ናቸው።
ተጨማሪ መረጃዎችን እንዳገኘን የምንመለስ ይሆናል።