16 ጃንዩወሪ 2020

በዩናይትድ ስቴትስ አደራዳሪነት ዋሽንግተን ላይ ሲካሄድ የቆው የኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት ፍሬያማ እንደነበር ተነግሯል።

ሦስቱ ሃገራት እንዲሁም አሜሪካ እና የዓለም ባንክ በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ እንዳመለከቱት በሕዳሴው ግድብ ሙሊት እና ሌሎች መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት በሚያደርሱ ነጥቦች ላይ ተግባብተዋል።

የአሜሪካው ገንዘብ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በድረገፁ ባወጣው መግለጫ ላይ የሃገራቱ ውሃ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት እንዲሁም ቀደም ብሎ በተደረጉ ውይይቶች ላይ ተመሥርቶ ከስምምነት ተደርሷል።

ሃገራቱ አደራዳሪዎች በተገኙበት በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ለመስማማትለቅድመ ስምምነት ደርሰዋል።

Twitter post by @seleshi_b_a: We have concluded discussion on #GERD.  The joint statement is attached here.  …. This result is after latest  4 rounds of Water Ministers meeting &  3 rounds of 6 ministers in the presence of US & the World Bank.

Image Copyright @seleshi_b_a

@SELESHI_B_A

ሚኒስትሮቹ፤ ሦስቱም ሃገራት ለአጭር ጊዜ ወይም ረዘም ላለ ጊዜ የሚቆይ ድርቅን በመቋቋም ረገድ የጋራ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተስማምተዋል።

ሚኒስትሮቹ ከጥር 19-20 ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ተገናኝተው በአባይ ግድብ ሙሊት ዙሪያ የተጠናከረ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተስማምተዋል። እስከዚያ ባለው ጊዜ ቴክኒካዊና ሕጋዊ ውይይቶች እንደሚከናወኑም ታውቋል።

የሦስቱ ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በድንበር ዘለል ትብብር አስፈላጊነት ዙሪያ ጠንከር ያለ አቋም አንፀባርቀው ስምምነቱ እንዲፀና የበኩላቸውን እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል ይላልየአሜሪካ ገንዘብ ሚኒስቴር ድረገፅ ላይ የወጣው መግለጫ።

የዋሽንግተኑ ስምምነት የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያና ግብፅ መካከል ያለውን ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ይጠበቃል።

5 ቢሊዮን ዶላር ያወጣል የተባለለት የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትሲጠናቀቅ በአፍሪቃ ትልቁ እንደሚሆን ይጠበቃል። 6 ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨትም ከግድቡ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

የሦስቱ አገራት የውሃ ሚንስትሮች በህዳሴው ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ጉዳይ ውይይት ሲያደርጉ ሕዳር ላይ በዋሽንግተን ካደረጉት ድርድር አንስቶ ይህ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።

በኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን የውሃ ሚንስትሮች በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ትናንት ታህሳስ 29 ቀን 2012 . ም በአዲስ አበባ ያካሄዱት የሦስትዮሽ ቴክኒካዊ ስብሰባ ያለስምምነት መጠናቀቁ ይታወቃል።