አገዛዙ ግብጽና ሱዳን በ1959እ.ኤ.አ የተፈራረሙትን ኢትዮጵያን ያገለለውን የዓባይን ውኃ በብቸኝነት የመጠቀም ውልን ሊፈርምልል ነው!!! እግዚኦ በሉ!!!
ከተደራዳሪዎቹ አንዱ የሆነው ደንቆሮና ከሀዲ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ትናንትና በኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ የዓባይ ወንዝ ዓመታዊ የውኃ መጠን ከ35-40 ቢ.ሜ.ኪ. መሆኑን ገልጾ አማካኙን ማለትም 37ቢ.ሜ.ኪ ውኃ በዓመት ለመልቀቅ መስማማታቸውን ገልጿዋል!!!
በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ለወደፊቱ በዚህ ታላቅ የተፈጥሮ ሀብቷ በዓባይ ወንዝ ላይ ለዓባይ ወንዝ የምታዋጣውን የውኃ መጠን ታሳቢ አድርጎ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን መሠረት ባደረገ መልኩ ለመስኖ ልማት የሚያገለግል ግድብ ገንብታ ወንዙን የድርሻዋን ያህል መጠቀም ፈጽሞ አትችልም ማለት ነው!!!
ይሄም ማለት ሌላ አንድና ሁለት ትርጉም የሌለው አገዛዙ በሀገርና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ ብሔራዊ ክህደት በመፈጸም ግብጽና ሱዳን በ1959እ.ኤ.አ. የተፈራረሙትን ኢትዮጵያን ያገለለ የዓባይን ውኃ በብቸኝነት የመጠቀም ውልን ፈረመ ማለት ነው!!!
ይሄው ደንቆሮ ሰውየ ይሄንን የክህደት ስምምነት ከተስማማ በኋላ ቅንጣት እንኳ ሳያፍር እዚያው ላይ ጨምሮ እንደገለጸው “ስምምነቱ ሌሎች ግድቦችን በዓባይ ወንዝ ላይ እንዳንገነባ የሚከለክል አይደለም!” ብሏል፡፡ ምን ዓይነት ግድብ ብላቹህ ጠይቁት፡፡ መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኘ እነግራቹሃለሁ ለኃይል ማመንጫ ይላቹህ ይሆናል እንጅ ፈጽሞ ለመስኖ ልማት የሚያገለግል ግድብ ሊላቹህ አይችልም!!! ምክንያቱም የዓባይ ወንዝ የሚሰበስበውን ዓመታዊ የውኃ መጠን እንዳለ ለመላክ ተስማምተው ፈርመዋልና ነው!!!
በመሆኑም ዓባይን የሚያህል ታላቅ ወንዝ እና በመስኖ ሊለማ የሚችል አራት ሚሊዮን ሔክታር ለም መሬት ይዛ በረሀብ የምትቆላዋ አሳዛኟ ሀገር ኢትዮጵያ ከእንግዲህ በኋላ ለመቸውም ጊዜ ቢሆን የዓባይን ውኃ ለመስኖ ልማት ላትጠቀም ተስማምታለች፡፡ መስማማቷንም ከሀዲዎቹ ከሳምንት በኋላ በሚፈርሙት ፊርማ ታረጋግጣለች!!!
ይሄ ክህደ ከማሳዝንም አልፎ አያሳብድም ወይ ወገን??? እነኝህ ከሐዲዎች ከቶ ምን ቢሰጧቸው ወይም ደግሞ ይሄንን ሕዝብና ይህችን ሀገር እንዴት ቢጠሉ ነው የወደፊት የመልማት ተስፋውን ሳይቀር እንዲህ ሊያጨልሙበት የቻሉት???
የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄ የተፈጸመብህ ከፍተኛ ብሔራዊ ክህደት ቁጣህን ካልቀሰቀሰውና ብሔራዊ ጥቅምህን አሳልፎ የሰጠውን ይሄንን የክህደት ውል እንዳይፈረም ካላደረክ በቁምህ ሞተህ መቀበርህን ዕወቀው!!!
ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ድርጅቶችና ማኅበራት እውነት እንደምታወሩት ለሀገርና ለሕዝብ የቆማቹህ ከሆናቹህ ሕዝብን ለተቃውሞ በማስተባበር ይሄንን በሀገሪቱ የወደፊት የመልማት ተስፋዋ ላይ የተቆመረውን የክህደት ውል እንዳይፈረም ታደርጉ ዘንድ አጥብቄ ማሳሰብ እወዳለሁ!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው