አገዛዙ ኦሮሚያ በሚለው የሀገራችን ክፍል ቤተክርስቲያን የቃል ኪዳን ምልክቷን (ዘፍ. 98-17) እንዳትጠቀም መከላከሉ ሲገርመን እራሱን በአዲስ አበባ ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ስም ያደራጀው የአሸባሪው አገዛዝ አሸባሪ ጭፍራ የቤተክርስቲያኗን ያለማንም ጣልቃገብነት የአምልኮ ሥርዓትን በነጻነት የመፈጸም ሕገመንግሥታዊ መብቷን በመጣስና በመግፈፍ የቃልኪዳን ምልክቷን እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ለበዓሉ በጥምቀተ ባሕሮች፣ በአብያተክርስቲያናትና በጎዳናዎች ላይ ከተሰቀለበት ሲያወርድና በኃይል ሲያስወርድ ውሏል!!!

ሲጀመር የኦሮሚያ ፖሊስ የሚባለው ኃይል የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌዴራል ፖሊስ እያሉ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ ምን አግብቶት ነው ገብቶ የሽብር ተግባር የሚፈጽመው???

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ልብ በል የኦሮሚያ ፖሊስ የሚሉት የጥፋት ኃይል በማያገባው ገብቶ አዲስ አበባ ውስጥ ይሄንን የሽብር ተግባር የሚፈጽመው አገዛዙ አዲስ አበባን በስርቆሽ በር በኩል ኦሮሚያ ክልል ወደሚሉት መጠቅለላቸውን ለሕዝብ ለማሳወቅ ነውና ይሄንን ነገር ታግሰህ ከተቀበልክ አዲስ አበባን አሳልፈህ እንደሰጠህ ዕወቀው!!! ከዚያ የሚከተልህን ታየዋለህ!!!

ይህ የምታዩት ፎቶ አሸባሪው የአዲስ አበባ ፖሊስ የቅጽረ ቤተክርስቲያንን በማንም ኃይል ያለመደፈር መብት እና የሃይማኖት ሥርዓትን በነጻነት የመፈጸም ሕገመንግሥታዊ መብት በመጣስና በመግፈፍ አራት ኪሎ ከሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ለበዓሉ የተሰቀለውን ትእምርተ ኪዳን ወይም የቃልኪዳን ምልክት አውርዱ!” ብሎ ሲያወርድና ሲያስወርድ ነው የምትመለከቱት!!!

ለቤተክርስቲያን ከዚህ በላይ መደፈር፣ ከዚህ በላይ መዋረድ፣ ከዚህ በላይ የመብት እረገጣ ምን አለ??? አገዛዙ ለውጥ ብሎ ማጭበርበሩን ትቶ ወደቀደመው አንባገነን ፈላጭ ቆራጭነቱ ተመልሶ የቤተክርስቲያንን መብት ክብርና ጥቅም ሲደፍር፣ ሲገፍና ሲነጥቅ ከዚህም በላይ ሲሰብርና ሲያጠፋ ወደነበረበት ጊዜ መመለሱን ካረጋገጠ የቆየ ቢሆንም ይሄም ተጨማሪ ማሳያ ነው!!!

በተጋዳላይ አቦይ ማትያስና ጭፍሮቻቸው የሚዘወረው ሲኖዶስ ተብየው የአገዛዙ ጉዳይ አስፈጻሚ የዚህ የአሸባሪዎች ግፍ ተባባሪ በመሆኑ ነው ቤተክርስቲያን የቃልኪዳን ምልክቷን በተለያየ ጊዜ በተለያየ ቦታ በመጠቀም መብቷ ላይ ጥሰትና ገፈፋ ሲፈጸም ሌላው ቀርቶ መግለጫ በማውጣትና ድርጊቱን በማውገዝ ቤተክርስቲያን የመብት ጥሰት ገፈፋና እረገጣ እንደተፈጸመባት እና ቤተክርስቲያኗ የአምልኮ ሥርዓቷን በነጻ የመፈጸም ሕገመንግሥታዊ መብት እንዲከበር ጠይቆ የማያውቀው!!!

ጭራሽ እንዲያውም እነ ተጋዳላይ አቦይ ማትያስ ከላይ ያስቀመጥኩላቹህ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እያለና የቤተክርስቲያኗ ትውፊትም በሚገባ እያረጋገጠ እኛ ይሄንን ሰንደቅ ዓላማ በቃል ኪዳን ምልክትነቱና በንዋዬ ቅድሳትነቱ አናውቀውም!” በማለት ሸምጥጠው በመካድ የቃል ኪዳን ምልክቱ እንዲጠፋ ከአገዛዙ ጋር በማሴር ተባብሮ ነበር፡፡ በአንዳንድ ብርቱ አባቶች ብርታት ነው በመረጃ ተረትተው ፍላጎታቸው ሳይሳካ የቀረው!!!

ምእመናን ሆይ! ፈተናው በምታዩት መልኩ ከጥፋት ኃይሎች አፍጥጦ መጥቷል እምቢ ለሃይማኖቴ!” ብለህ መከራ በመቀበል ሃይማኖታዊ ግዴታህን የምትወጣ ክርስቲያን ብትኖር በቤተክርስቲያን ራስ በክርስቶስ ፊት ክብርና ጸጋ ታገኝበታለህና በርታ ጽና!!!

ለሆድህና ለጥቅምህ አድልተህ የዚህ ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ አባሪ ተባባሪ በመሆን አፍህን በዝምታ የሸበብክና በዝምታህ የተባበርክ እንዲሁም ፈርተህ ቤተክርስቲያን በዚህ መልኩ መብቷ ሲገፈፍ፣ ሲጣስ፣ ስትደፈርና ስትዋረድ አፍህን የሸበብክና እራስህን ጥግ ያሲያዝክ ግን ወዮ ላንተ!!!

ድል ለቤተክርስቲያን!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው