This image has an empty alt attribute; its file name is 110600428_.jpg

…በርካታ የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የጉዞ እገዳ ይጣልባቸዋል የተባሉ አገራት ዝርዝርን ተመልክተናል ያሉ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ፤ የጉዞ እገዳው ሰለባ ይሆናሉ የተባሉት የአፍሪካ አገራት ኤርትራ፣ ናይጄሪያ፣ ሱዳን እና ታንዛኒያ መሆናቸውን ዘግበዋል።

በስዊትዘርላንድ ዳቮስ እየተካሄደ ባለው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ ላይ ከዎል ስተሪት ጆርናልጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አራት የአፍሪካ አገራት ላይ የጉዞ እገዳ ለመጣል ማቀዳቸውን አረጋግጠው፤ የአገራቱን ዝርዝር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

ዘ ፖለቲኮ በበኩሉ የአገራቱ ዝርዝር የመጨረሻ ውሳኔ አለመሆኑን እና ለውጥ ሊደረግባቸው እንደሚችል አስነብቧል። ዘ ፖለቲኮ ከአራቱ የአፍሪካ አገራት በተጨማሪ ቤላሩስ፣ ምያንማር (በርማ) እና ክሪጊስታን የጉዞ እገዳ ሊጣልባቸው የሚችሉ አገራት መሆናቸውን ዘግቧል።

ፕሬዝደንቱ ሊያጸድቁት እንደሚችሉ የተገመተው እና በረቂቅ ላይ የሚገኘው ሕግ፤ እገዳ የተጣለባቸውን አገራት ዜጎች ሙሉ በሙሉ ከጉዞ የሚገድብ እንዳልሆነ እና በተወሰኑ የቪዛ አይነቶች እና የመንግሥት ባለስልጣናት ላይ ብቻ ገደብ እንደሚጥል ተነግሯል።

የአሜሪካ መንግሥት የጉዞ እግዱን በየትኞቹ አገራት ላይ እና ምን አይነት እገዳ እንደጣለ በቀጣይ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

እነዚህ አገራት በምን መስፈርት ተመርጠው የጉዞ እገዳው እንደተጣለባቸው ግልጽ ባይደረግም፤ የአሜሪካ የስነ ሕዝብ እና ጤና ዳሰሳ ጥናት አሃዞች እንደሚያሳዩት የእነዚህ አገራት ዜጎች አሜሪካ ከደረሱ በኋላ ከተፈቀደላቸው ቀን በላይ ይቆያሉ።

... 2018 ለጉብኝት ወይም ለሥራ ወደ አሜሪካ ከተጓዙ ኤርትራውያን መካከል 24 በመቶ የሚሆኑት በቪዛቸው ላይ ከተፈቀደላቸው ቀናት በላይ በአሜሪካ ቆይተዋል። 5 በመቶ የሚሆኑት ናይጄሪያውን እና 12 በመቶ የሚሆኑት ሱዳናውያን በተመሳሳይ መልኩ ከተፈቀደላቸው ቀናት በላይ በአሜሪካ ቆይተዋል።

በአጠቃላይ ወደ አሜሪካ ለሥራ ወይም ለጉብኝት ተጉዘው ከተፈቀደላቸው በላይ የሚቆዩት 1.9 በመቶ የሚያህሉት መሆናቸውን አሃዞች ይጠቁማሉ።

Presentational grey line

... 2017 ፕሬዝዳንት ትራምፕ አብዛኞቹ የሙስሊም አገራት ከሆኑት፤ ኢራን፣ ሶማሊያ፣ ሶሪያና የየመን ዜጎች ወደ አሜሪካ የሚያደርጉት ጉዞ ላይ እግድ መጣላቸው ይታወሳል።

እገዳው በፍርድ ቤት ክርክር ተደርጎበት የነበር ቢሆንም፤ ሰኔ 2018 የአሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን አጽንቶታል።

ዲቪ ሎተሪ

በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ፕሮግራምተሳታፊ ከሆኑ ሃገራት መካከል የተወሰኑት ሃገራት በፕሮግራሙ እንዳይሳተፉ ሊደረግ እንደሚችል ጭምር ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

በዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ ፕሮግራምበአሜሪካ ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ሃገራት ዜጎች፤ በእጣ አማካኝነት ወደ አሜሪካ መጥተው ግሪን ካርድ (የመኖሪያ ፍቃድ) የሚያሰጥ ፕሮግራም ነው።

ይህ ፕሮግራም አሜሪካን የተለያዩ የዓለማችን ሃገራት ሰዎች የሚኖሩባት ልዩነቶቸን በውስጧ የያዘች ሃገር ያደርጋታል ተብሎ ሲተገበር ቆይቷል።

ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን ይህ ፕሮግራም የማይፈለጉአይነት ሰዎችን ወደ አሜሪካ እያመጣ ስለሆነ መቅረት አለበት በማለት፤ በዲቪ ፕሮግራም ፈንታ ክህሎት ያላቸውን ሰዎች ለይቶ በተለየ ቪዛ ወደ አሜሪካ የማምጣት ፕሮግራም ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ይላሉ።