እስከ ዘር ማጥፋት ጥቃት የደረሰ አረመኔያዊ የግፍ ጥቃት፣ ገደብ የለሽ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ በ21ኛው መ... ፈጽሞ የማይጠበቅ የሕግ ሽፋን የተሰጠው የኢፍትሐዊ አሥተዳደር በደል ብሶት፣ ያፈጠጠ የሀገር መፍረስ ሥጋት ወዘተረፈ. የወለደው የአማራ ብሔርተኝነት ትግል ተወልዶ የነበረው የአማራ ብሔርተኝነት ትግል ተወለደ ወዲያውም ሞተ!” የመባልን ያህል አጭር የሕይዎት ታሪክ ነው ያለው!!!

በስንት መከራ ስንት ዋጋ ከፍለንበት ተቀስቅሶ የነበረው ይሄ የአማራ ብሔርተኝነት መቀስቀሱ ከፍተኛ ሥጋት ላይ የጣላቸው ወያኔ/ኢሕአዴግና ቢጤዎቹ የጥፋት ኃይሎች ተጋግሎ እየተቀጣጠለ የነበረውን የአማራ ትግል ለመጥለፍ አሰቡና ካድሬዎቻቸውን አደራጅተው አብን!” የሚባል ድርጅት መሠረቱና ይሄንን ያሠጋቸውን የአማራ ትግል በአብን ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አደረጉት!!!

አብንም ከአገዛዙ ጋር ተናቦ አገዛዙ በሚወስደው እርምጃ በመታገዝ የአማራን ትግል ግለቱን ቀስ እያደረገ እንዲበርድና እንዲቀዘቅዝ በማድረግና ማጅራቱን ተመትቶ እንዲጠቀለል ለዚ የማጅራት መች ምት በማመቻቸት የተሰጠውን ተልእኮ በተሳካ ሁኔታ አጠናቆ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተሾመ ዕለት አክራሪ የአማራ ብሔርተኛን ሁሉ ታች ድረስ ወርደን መንጥረን እናጠፋዋለን!” እንዳለው ሁሉ ዘመቱበትና ሊያጠፉት ቻሉ!!!

ይህ የአማራ ብሔርተኝነት ትግል መቀስቀስ የሀገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ የጣለውን የጎሳ ፖለቲካ የሚጠላውና ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዘው the silent majority በመባል የሚጠራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀገሪቱን ካንዣበበባት የመፍረስ አደጋ የሚታደጋት ይሄ የአማራ ብሔርተኝነት ነው!” ብሎ በማሰብ የአማራን ብሔርተኝነት ትግል በታላቅ ጉጉትና ተስፋ ሲጠብቅ ነበር!!! ድጋፉንም በሚታይና በማይታይ መልኩ በተለያየ መንገድ ይገልጽ ነበር!!!

የት ይደርሳል የተባለ ጥጃ ሉካንዳ ቤት ተገኘ!” እንዲሉ አገዛዙ በሥነ ሥርዓቱ ቁጭ ብሎ ስትራቴጂ ነድፎ በመነሣት በተለያየ አቅጣጫ በአቃፊው የአማራ የብሔርተኝነት ትግል ላይ በመዝመቱ አሁን ላይ በምታዩት ደረጃ እንኳንና ለሀገር ለራሱ እንኳ ሳይሆን ቀርቶ እጅግ በሚያሳዝን አኳኋን አከርካሪውን ተሰብሮ በመውደቁ አማራ ይቅርና ትናንሽ ጎሳዎች እንኳ ፈጽሞ የማይታገሷቸው አማራን እንደማኅበረሰብ ቅስሙንና ክብርሩን ክፉኛ በሚነካና በሚያዋርድ ደረጃ፣ በከፍተኛም ንቀት እዚህም እዚያም አጸያፊና ነውረኛ ጥቃቶች እየተፈጸሙበት እንኳ ትንፍሽ ሳይል የገዛ ሐዘኑን የገዛ ሕመሙን የገዛ ውርደቱን ዓይቶ እንዳላየ ሰምቶ እንዳልሰማ ሆኖ እያሳለፈ ይገኛል!!!

ይሄ ሁሉ ሲሆን ለአማራ ሕልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብት፣ ጥቅም እንታገላለን!” የሚሉ ድርጅቶች ፊት ለፊት ወጥተው መክፈል ያለባቸውን ዋጋ በመክፈል ሕዝቡን አነቃንቀው አማራ ሌላው ሁሉ ቢቀር የአናሳ ጎሳዎችን ያህል እንኳ በሰውነቱና በዜግነቱ ታፍሮና ተከብሮ መኖር እንዲችል ማድረግ ለምን ያልቻሉና ያልፈለጉም ይመስላቹሀል???

ከሰሞኑ ድርጊት እንኳ ብንነሣ ምንም እንኳ ይሄንን መሰል ግፍ መፈጸም ከጀመረ የቆየ ቢሆንም አሁን አማራ ልጆቹን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማስተማር በማይችልበት ደረጃ ደርሶ እንኳ፣ የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ!” እንዲሉ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የጥቃት ኢላማው የአማራ ተማሪ በሆነበት ሁኔታ አጠፉ!” እየተባሉ የዲሲፕሊን እርምጃ እየተወሰደባቸው ከየዩንቨርስቲው እንዲባረሩ የሚደረጉት የአማራ ተማሪዎች በሆኑበት ሁኔታ፣ በየስፍራው በኖረበት ቀየ ነፍሱ የትንኝ ያህል እንኳ ዋጋ አጥታ በማንነቱ የትም በግፍ እየተገደለ ባለበት ሁኔታ፣ በጥፋት ኃይሎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ዘወትር በግፍ ላይ እንደገና ሌላ ግፍ እየተደራረበ የሚፈጸምበት በየዕለቱ አዳዲስ መርዶ የሚጎበኘው አማራ ብቻ በሆነበት ሁኔታ አማራ ግን ይሄ ሁሉ ግፍ ሲፈጸምበት ቅስቅስም ሳይል ምንም ማድረግ ሳይችል ላንቀሳቅስህ!” የሚለው ለአማራ እታገላለሁ!” የሚል አንድም ድርጅት ሳይኖር ውርደቱን ውጦ ምንም እንዳልተፈጠረ አርፎ የሚቀመጥ ሆኖ ቁጭ ብሏል!!!

ነገሩን እጅግ አሳዛኝ የሚያደርገው ደግሞ እንደ ኦሮሞ እንዲሁም እንደ ትግሬ ያሉ እና አናሳ ጎሳዎችም ሳይቀሩ ተመሳሳይ አስቀያሚ ማንነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ቢፈጸምባቸው ፈጽሞ የማይታገሱና ቢቃጣባቸው እንኳ ከአክቲቪስቶቻቸው እስከ ፖለቲከኞቻቸው ድረስ ያሉት ሀገሩን ቀውጢ አድርገው ሕዝባቸው በቁጣ እንዲነሣ በማድረግ ክብራቸውን የሚያስጠብቁ በሆኑበት ሁኔታ አማራ ግን እራሱን ከእነኝህ ጋር በማነጻጸር በቁጭት ለመነሣሣት ሳይሞክር ከእነኝህ አንሶ ለራሱ እንኳ ሳይሆን አንገት አስደፊ ውርደቱን፣ አሳፋሪ አዋራጅና ቅስም ሰባሪ ውርደቱን ዋጥ እያደረገ አርፎ መቀመጡ ነው!!!

እስኪ እየሆነ ያለውን መለስ በሉና አስቡ??? በዚህች ሀገር ውስጥ ተጠቂው አማራ ብቻ እንዳይመስልና በአማራ ላይ የሚፈጽሙት የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ጥቃት እንዳይታወቅ ለማድረግ ለሽፋንና ለፖለቲካ ሴራቸው ሲሉ ከሦስት ዓመት ወዲህ ኦሮሞ ከሶማሌ እንዲፈናቀል፣ ደቡቦችንም ከቡራዩና ከተለያዩ ቦታዎች ወዘተረፈ. እንዲፈናቀሉ ከማድረጋቸው ውጭ በመላ ሀገሪቱ ያለማቋረጥ ለ29 ዓመታት ሙሉ በብቸኝነት ከአማራ ውጭ ጥቃት ሲፈጸምበት የኖረ አንድ ሌላ ብሔረሰብ ልትጠቅሱልኝ ትችላላቹህ??? ለዚህን ያህል ዓመት በአማራ ላይ ሲፈጸም የኖረው ያ ሁሉ መንግሥታዊ የሽብር ጥቃትስ አማራን በምን ያህል በቁጥር እንደቀነሰው፣ ምንያህል እንዳደኸየውና እንደሰበረውስ አስባቹህና ገምታቹህ ታውቃላቹህ???

እጅግ የሚገርመውና የሚያሳዝነው ነገር አገዛዙ ለውጥ!” ብሎ እየተወነ ባለበት ዘመን እንኳ ዘመኑ ለአማራ ከእንቅቡ ወደ ምጣዱ እንዲሆንበት ማድረጉ ነው፡፡ የአማራ መከራ ተባብሶ መቀጠሉ ብቻ ሳይሆን አማራ በዚሁ ለውጥ!” በተባለው ድራማ ምክንያት በተፈጠረው ክፍተት ተጠቃሚ ሆኖ እራሱን አደራጅቶ ለእራሱ እንዳይቆምና ህልውናውን፣ ደኅንነቱን፣ ነጻነቱን፣ መብቱንና ጥቅሙን እንዳያስጠብቅ ለማድረግና በስውርና በግልጽ በሚፈጽሙበት ጥቃት አማራን የማጥፋት ሰይጣናዊ እቅዳቸው እስኪፈጸም ድረስ ደፍቆ ለማስቀረት በአማራ ላይ የሚሠራው የፖለቲካ ሴራና ደባ አብንን የመሰሉ ቅጥረኛ ድርጅቶችን ከመመሥረት ጀምሮ ቀድሞ ለአማራ ይታገሉ የነበሩትንና ብዙ ዋጋ የከፈሉትን አማሮችን በገንዘብና በተለያዩ መንገዶች በመደለል በድብቅ ለአገዛዙ እንዲሠሩ እስከማድረግ ይረስ እየረቀቀና እየጠነከረ መምጣቱ ነው!!!

አብኖች አገዛዙ ሰኔ 15 ላይ ጀግኖቻችንን እነ አሳምነው ጽጌን በሐሰተኛ ክስ ወንጅሎ በግፍ በገደለ ጊዜ ካድሬዎቻቸውን አሰማርተውና አመራሮችም መግለጫ እያወጡና በሚዲያም እየቀረቡ አማራ አጸፋዊ እርምጃ በመውሰድ ትግሉንና ጀግኖቹን ከመመታት እንዳይታደግ፣ ፀረ አማራው አገዛዝም በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዳይጋለጥ ሕዝቡን ተረጋጉ፣ አማራ ታጋሽ ነው ታገሱ፣ ከመንግሥት ጋር ተባበሩ፣ ጸጉረ ልውጥ ስታገኙ ለጸጥታ አካላት አሳልፋቹህ ስጡ…..!” ወዘተረፈ. እያሉ የቅጥረኝነታቸውን አስበልተውን በነፍስ በሥጋችን ተጫውተውብን ሲያበቁ ይባስ አሉና ደግሞ ከጥቃቱ ማግስት ጀምረው የአማራ ትግል ለቅሶ ይበዛዋል፣ የአማራ ኤሊት አማራ የህልውና አደጋ ላይ ያለና በጠላት የተከበበ አድርጎ የሌለ ነገር በማሰብና በማውራት የተጠመደ ነው!” ወዘተረፈ. በማለት አማራን ምንም ኮሽታ በሌለበት በራሱ ላይ የሚያሟርት ቃዣታም አስመስለው በማውራት እግጅ በሚያሳዝንና ልብ በሚሰብር አንጀት በሚያደማ መልኩ ተሳለቁብን ቀለዱብን!!!

አብኖች እንዲህ ክፉኛ ሊሳለቁብንና በቁስላችን ላይ እንጨት ሰደው ክፉኛ ሊያደሙን ሊመሠረቱ ሰሞንና በተመሠረቱም ጊዜ ግን ስሜት ኮርኩረው የሕዝብ ድጋፍ ለመሰብሰብ በማሰብ አማራ ህልውናህ አደጋ ላይ ነው ተነሥ፣ እስከአሁን ያስበላህ አለመደራጀትህ ነው ተደራጅ፣ አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ፣ ከአሁን በኋላ አማራን ማንም የትም የሚገድለው አይሆንም፣ አማራነት የሰውነት ውኃ ልክ ነው…..!” ወዘተረፈ. የሚሉና ሌሎችም ኢትዮጵያዊነትን ያኮሰሱና አማራነትን ያገነኑ ለመድገም የሚከብዱ መፈክሮችን እያስተጋቡ ነበር በሚገባ በተጠና መንገድ በተለይ ወጣቱን የስሜት ስካር ውስጥ በመክተት ለረጅም ዘመናት ስንት ደክመንና ስንት ዋጋ ከፍለን የአማራን ብሔርተኝነት ትግል ለዚያ አድርሰነው ከነበርነው እጅ በመንጠቅ መዳፋቸው ስር እንዲገባ ማድረግ የቻሉት የነበረው!!!

የሆነው ሁሉ ሆኖ አሁንስ ቢሆን አማራ የሆነበትን ሁሉ መለስ ብሎ ተመልክቶ፣ የተሠራበትን ደባና ሸፍጥ አጢኖ ለመንቃትና በቁጭት ለመነሣት ችሏል ወይ?” ብለን ብንጠይቅ አብዛኛው አማራ እንኳንና ሊነቃ ገና የሆነበትን ነገር የተሠራበትን ሸፍጥና ሴራ እንኳ በቅጡ እንዳልተረዳ የምናየው እውነት ነው፡፡ እንኳንና ሕዝቡ ልኂቃኑ እንኳ ገና ሙሉ ለሙሉ አልነቃም፡፡ ሙሉ ለሙሉ እስኪነቃ ድረስም ገና ብዙ የሚከፍለው ከባባድ ዋጋ አለ!!!

ለዚህ አማራ ለደረሰበት የትግል መጠለፍና እጅግ አሳዛኝ ኪሳራ ሁሉ ዋነኛ ተጠያቂዎቹ አብንን የመሠረቱት በሙሉ አብንን ከመመሥረታቸው በፊት ከ90% በላይ የሚሆኑት በብአዴን ተመድበው ከካድሬነት የመጡ ወይም የወያኔ አህዮች ሆነው በየተሰማሩበት አማራን አሳሩን ሲያበሉትና ለወያኔ የዘር ማጥፋት ጥቃት ሲያስበሉት የኖሩ የብዙ ንጹሐን አማራ ደም በእጃቸው ያለባቸው የሆኑ፡፡ የተቀሩት ደግሞ አማራ የሚባል ብሔረሰብ ወይም ነገድ የለም!” እያሉ በተለያዩ ፓርቲዎች ውስጥ ሆነው ለአማራ ጥፋት ሲሠሩ የነበሩና በአማራ ብሔርተኝነት ትግል አንዳቸውም እንኳ የማይታወቁና ያልተሳተፉ ሆነው እያለ ድንገት ተነሥተው የአማራ ብሔርተኛ በመምሰል የአማራን ትግል እንመራለን!” ብለው ሲነሡ የየአንዳቸውን የጀርባ ታሪክና ሰብእና ወደኋላ መለስ ብለን እናጢን እንመርምር!” ሳይሉና ሳይመረምሩ በእውር ድንብስና በግልብ ስሜት ብቻ በመነዳት ሕዝባችን በብአዴን ጠላፊ ወጥመዶች ማለትም በአብንና በዐሥራት እንዲጠለፍ እንዲታለልና ለዚህ ውድቀትና ስብራት የዳረጉት ዘገምተኛ ሊኂቃኖቻችን ናቸው!!!

ይሄ ሁሉ ሲሆን በእያንዳንዱ ሁነት በአመክንዮና በመረጃ እየሞገትኩና እየተነተንኩ ተው እነኝህ ሰዎች ቅጥረኞችና የአማራን ትግል ጠላፊዎች ናቸው ተጠንቀቁ!” እያልኩ አብዝቸ የጮህኩና ያስጠነቀኩ ብሆንም ከጥቂት አስተዋዮች በስተቀር የሰማኝ አልነበረም፡፡ እንግዲህ በቅጥረኞች፣ በባንዶችና በፀረ አማራ የጥፋት ኃይሎች አህያ ብአዴን የተረሸነውን የአማራን ብሔርተኝነት ትግል ነፍስ ይማር!!!” ከማለትና ለትንሣኤ ያብቃው!” ከማለት ውጭ ሌላ ምን ማለት ይቻላል???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው