ከእነዚህም መካከል አንዱ ለ9 ዓመታት በኢቢሲ ከሪፖርተርነት እስከ ዜና ክፍል ምክትል ዋና አዘጋጅነት ያገለገለው ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ ይገኝበታል።

ጋዜጠኛው ቢላል በዚህ ሳምንት ሰኞ የተካሄደውን የዩኬአፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ለመዘገብ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከሚመራ ልዑክ ጋር ወደ ለንደን የተጓዘ ሲሆን ጥገኝነት መጠየቁን ለቢቢሲ አረጋግጧል።

• የኢቢሲ የትግርኛ ክፍል ሠራተኞች በተቋሙ አስተዳደር ጫና ይደርስብናል አሉ

ከቢላል በተጨማሪ ሌሎች ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የኢቢሲ ነባር ጋዜጠኞች በተለያዩ አጋጣሚዎች በሄዱባቸው ምዕራባውያን ሃገራት ጥገኝነት ለመጠየቅ የተገደዱት ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በሚደርሱባቸው ጫናዎች እንደሆነ ተናግረዋል።

Presentational grey line

ጋዜጠኞች የኤዲቶሪያል ነጻነት የላቸውም

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት እና በውጪ አገራት የሚገኙት የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ለቢቢሲ በላኩት የጽሑፍ መልዕክት በጋዜጠኝነት ሥራቸው የኤዲቶሪያ ነጻነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

ጉዳዮች እየተመረጡ ነው የሚዘገቡትያሉት ጋዜጠኞቹ እንደምሳሌ፤ በጅግጅጋ አብያት ክርስቲያናት ሲቀጣሉ በፍጥነት ሳይዘገብ መቆየቱን፣ የሃይማኖት ተቋማት መግለጫዎች ለምሳሌ ሲኖዶሱ የኦሮሚያ ቤተክነት መቋቋምን አወግዛለሁ ማለቱ አለመዘገቡ፣ በሞጣ የተፈፀመው ጥቃት ሰፊ ሽፋን ሳይሰጠው እንደቀረ፣ የትግራይ ክልል እና የህውሃት መግለጫዎች አለመዘገባቸው፣ የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጉዳይ የተዘገበበት መንገድ እና ሌሎችን ጉዳዮችን በመጥቀስ የዜና ሽፋን የሚሰጣቸው ጉዳዮች የተመረጡት ብቻ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁም፤ ኢቢሲ እንደ ከዚህ ቀደሙ እኔን ብቻ አገልግሉ የሚልና ሌላውን ሰምቶ እንዳልሰማ የሚሆን መገናኛ ብዙኃን በመሆኑ የድርጅቱ አገልጋይ ሆኖ ላለመቀጠል ወስኛለሁብሏል።

ገዥውን ፓርቲ ማገልገል ብቻ አላማቸው ያደረጉና ከዚያ ውጭ የሕዝብም ሆነ የትኛውም ፓርቲ ፍላጎት የማይነሱበት፤ ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችን ለመዘገብ የሚያስችል ሁኔታዎች የሉም ሲል ያክላል።

እርሱ እንደሚለው አሁን ላይ ተባብሰው የመጡት የብሔርና እምነት ጉዳዮች በሙያው ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ ችግሮች ናቸው። እነዚህ ችግሮች በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ባልደረቦቹም ላይ የሚያጋጥሙ እንደሆኑ ይናገራል።

ጋዜጠኞችም በሚያነሱት ጉዳዮች በማንነታቸውና ኃይማኖታቸው የሚፈረጁበት አጋጣሚዎችም በርካታ መሆናቸውን ያነሳል።

ከዚህም ባሻገር ኢቢሲ የሚዘገቡ ጉዳዮችን ከመምረጡም ባሻገር ጋዜጠኞች በጉዳዮቹ ላይ ዘገባ ለመስራት ሲጠይቁ ይሁንታ እንደማይሰጣቸው ይናገራል።

የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ አብዱልጀሊል ሃሚድ ግን በተቋሙ የኢዲቶሪያል ነጻነት የለም የሚሉ ክሶችን ሙሉ በሙሉ ያጣጥላሉ።

• የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝመሐመድ አደሞ

• ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ?

የራሳችን ኤዲቶሪያል ፖሊሲ አለን። በዛ መሠረት ነው በነጻነት የሚሰሩት። ምንም የተቀየረ ነገር የለም። ማንም ጣልቃ አይገባም። ሁሉም ነገር የሚሰራው በጋዜጠኝነት ሥነምግባር ነው። አቶ ቢላል በራሱ ፍቃድ ለኑሮ ይሻለኛል ብሎ ነው የቀረው እንጂ የኤዲቶሪያል ነጻነት የለም የሚለው አያስኬድምበማለት ጉዳዩን ለማብራራት ይሞክራሉ።

ጋዜጠኞቹ እንደምሳሌ የጠቀሱትን በማንሳት ዜናዎች እየተመረጡ ነው የሚሰሩት ለሚለው ቅሬታ ምላሽ የተጠየቁት አቶ አብዱልጀሊል፤ እኛ አገርን በማይንድ ፣ ሕዝብን በማያራርቅ መልኩ ነው ዜናዎችን የምንመርጠው። እንደውም የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ጉዳይ ቀድመን የዘገብነው እኛ ነንይላሉ።

የጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ፕሬስ ሴክረታሪያት በኢቢሲ ቀርበው ስለታገቱት ተማሪዎች ከሰጡት መግለጫ ውጪ ኢቢሲ ተከታታይ ዘገባ አለመስራቱን እና ጋዜጠኞች በጉዳዩ ዝርዝር ዘገባዎችን ለመስራት ጠይቀው መከልከላቸውን የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ይናገራሉ።

አቶ አብዱልጀሊል ግን፤ ይሄ ዘበት ነው። ዛሬ ጠዋት በነበረው ስብሰባ ላይ እንኳን ተከታታይ ዘገባዎች ለምን አይሰሩም ብለን ጥያቄ አቅርበን ነበር። አቶ ቢላልም እራሱ ቡድን መሪ ስለሆነ ይህን ሃሳብ አቅርቦ በኤዲቶሪያሉ ጸድቆለት ነበር። እሱ የቤቱን ስም ለማጠልሸት ካልሆነ በቀር ከዚህ ጋር የተገናኘ ነገር የለምይላሉ።

Image copyright

ጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ

BILAL WORKUጋዜጠኛ ቢላል ወርቁ

ተቋሙ ብቃት በሌላቸው ሰዎች ነው የሚመራው

ጋዜጠኛ ቢላል ተቋሙን የሚመሩት ምንም ዓይነት የሚዲያ ልምድ እና በቂ የትምህርት ዝግጅት የሌላቸው እንደ ፌደሬሽን ምክር ቤት በብሔር ውክልና የተቀመጡ ናቸው፤ ሃሳቦችም ሲነሱ በብሔር ነው የሚቃኙትይላል።

ለቢቢሲ በጽሁፍ ሃሳባቸውን የላኩ ጋዜጠኞችም በተመሳሳይ መልኩ ከአርታኢዎቻቸው መካከል ጥቂት የማይባሉት በቂ ልምድ እና የትምህርት ዝግጅት እንደሌላቸው ጠቁመዋል።

አቶ አብዱልጀሊል በበኩላቸው ኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች አገር ነች። ይሄ ሚዲያም የሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ነው ብለን ነው የምናምነው። እየተሰራ ያለውም በዚሁ መልክ ነው። ሰዎቹ አቅም የላቸውም ለሚባለው፤ አቅሙን ማነው የሚወስነው? ዩኒቨርሲቲዎች አስተምረው ሰርተፊኬት ስጥተዋል። እስከ ሁለት ማስተርስ ዲግሪ ያላቸው ጋዜጠኞች አሉሲሉ መልሰዋል።

• የድኅረ ዐብይ ሚዲያ በምሁራኑ ዕይታ

የቀድሞ የኢቢሲ ጋዜጠኞች ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች መካከል የጋዜጠኝነት ሙያን እና ልምድን በሚጠይቁ የኤዲቶሪያል ስብሰባዎች ላይ እንደ ጠቅላላ አገልግሎት እና የሹፌሮች ስምሪት ኃላፊዎች ያሉ በኤዲቶሪያል ስብሰባዎች ላይ ተገኝተው በዜናዎች አዘጋጋብ እና ይዘት ዙሪያ አስተያየት ይሰጣሉ ይህም በሥራችን ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል የሚለው ይገኝበታል።

አቶ አብዱልጀሊል ለዚህ ምላሽ ሲሰጡ፤ በኤዲቶሪያል ፖሊሲያችን ላይ የኤዲቶሪያል አባላት እነማናቸው ተብሎ ተጽፎ ተቀምጧል። የሹፌሮች ስምሪት ኃላፊዎችም ሆኑ ጠቅላላ አገልግሎት እንዲሳተፉ የሚደረገው ከሎጂስቲኩ በተጨማሪ በሚዲያው ላይ ብዙ ዓመት ስለቆዩ በዜናዎች ላይ ሃሳብ ይሰጣሉ፤ ሃሳባቸው ተቀባይነት ካገኘ ይወሰዳል

Presentational grey line

የመንግሥት ባለሥልጣናት ጣልቃ ገብነት

በጋዜጠኝነት ሥራችን ላይ የመንግሥት ኃላፊዎች እና መሥሪያ ቤቶች ጣልቃ ገብነት ሥራችንን በገለልተኛነት እንዳናከናውን ጫና ያሳድራል የሚለው ሌላው የጋዜጠኞቹ ቅሬታ ነው።

የኢቢሲ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የቴሌቪዥን ዘርፍ ኃላፊው ለዚህ ቅሬታ ምላሽ ሲሰጡ፤ ጫና የሚያሳድሩ የሉም ማለት ባይቻልም ይህ ገፍቶ የመጣ ጉዳይ አይደለምይላሉ። አቶ አብዱልጀሊል እንደሚሉት ከሆነ ከዚህ ቀደም አንዳንድ ዜናዎች እና ፕሮግራሞች አይተላለፉእያሉ የሚደውሉ ኃላፊዎች አሉ። እሳቸው እንደሚሉት ግን የተቋሙ ኤዲቶሪያ ፖሊሲ ላይ በመመርኮዝ የውጪ ጫና በተቋሙ ሥራዎች እና በጋዜጠኞች ላይ እንዳይደረግ ያደርጋሉ።

Presentational grey line

አሁን ለምን?

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ፤ በርካታ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ከእስር ተለቀዋል። እግድ ተጥሎባቸው የነበሩ መገናኛ ብዙኃን ወደ ሃገር ገብተዋል። በኢትዮጵያም የተሻለ የመናገር ነጻነት ሰፍኗል ተብሏል።

ይህ አዎንታዊ ለውጥ አለ በሚባልበት ወቅት ጋዜጠኞቹ ለምን በሄዱባቸው አገራት መቅረትን መረጡ?

ለዚህ ጥያቄ ምላሽ የሰጠን ጋዜጠኛ ቢላል፤ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለውጡ ሲመጣ ትልቅ ተስፋ እንደነበረው እና ደስተኛ እንደነበር ይናገራል።

ቢላል ከዚህ ቀደም ወደ ምዕራብ አፍሪካ እና መካካለኛው ምስራቅ አገራት ለዘገባ መጓዙን በማስታወስ በለውጡ ትልቅ ተስፋ ስለነበረው ከዚህ በፊት ባደረጋቸው ጉዞዎች በዚያው ለመቅረት እንዳላሰበ ይናገራል።

አሁን ላይ ግን እኛ ያልንህን ብቻ ሥራ። ባዘዝንህ መልኩ አገልግል።የሚለውን እንደ ጋዜጠኛ መሸከም ስላልቻልኩ ለመወሰን ተገድጃለሁይላል።

ቢላል በነበርኩበት የሥራ ኃላፊነት ከመንግሥት ባለሥልጣናትና ሚኒስትሮችም በስልክ ማስፈራሪያዎች ይደርሱብኝ ነበርይላል። ዝርዝር ሁኔታውን የጠየቅነው ጋዜጠኛው፤ ለቤተሰቦቹ ደህንነት ስለሚሰጋ ለጊዜው መናገር እንደማይፈልግ ገልፆልናል።

በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ከ4 ያላነሱ ነባር ጋዜጠኞች ባለፉት ጥቂት ወራት በተለያዩ አጋጣሚዎች ባቀኑባቸው አገራት ጥገኝነት ጠይቀዋል።