እናንተየ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሀገርና ለሕዝብ የቆመ የፖለቲካ ድርጅት፣ የሲቪክና የእምነት ተቋማት እንዲሁም ምሁራን አሉ ወይ???
ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በሚያደርጉት የዓባይ ግድብ ድርድር አሜሪካ በእጅጉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም እስከወዲያኛው የሚያስቀርና የሚጎዳ የማግባቢያ ሰነድ ላይ እንደተስማሙ መግለጻቸውን ተከትሎ ለፖለቲካ ድርጅቶች፣ ለሲቪክና የእምነት ተቋማት፣ እንዲሁም ለምሁራን ያቀረብኩት አስቸኳይ ጥሪ ነበር!!!
ይሄንን አደገኛ የክህደት ውል አገዛዙ ከማንም በላይ ጉዳዩ ለሚመለከተውና እንዲህ ባሉ በሀገሪቱ ጥቅሞች ጉዳይ ላይ ሉዓላዊ ሥልጣን ላለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ በዝርዝር ሳያሳውቅና ሳያስረዳ ሕዝቡ መስማማት አለመስማማቱንም ሳያረጋግጥ በሀገር ክህደት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ የሚሰጠውን አሳሪ ውል ወይም ስምምነት ሊፈርም መሆኑን ከብዙኃን መገናኛዎች ተሰምቶ እያለ ከጠቀስኳቸው አካላት ከምሁራንና ባጠቃላይ ከሕዝቡ ምንም ዓይነት ምላሽ አለመታየቱ እንደዜጋ በእጅጉ አሳስቦኛል!!!
ዋናው የውሉ አደገኛ አንቀጽ የዓባይ ውኃ ዓመታዊ የውኃ ፍሰት ከ35-40 ቢ.ሜ.ኪ. ነው በሚል ግምት ሀገራችን በየዓመቱ አማካኙን 37 ቢ.ሜ.ኪ. ውኃ ለመልቀቅ አገዛዙ መስማማቱ ነው!!! ለመስማማታቸው በሰጡት መግለጫ ላይ ሊንኩን ከፍቶ በመመልከት ማረጋገጥ ይቻላላ፦
https://youtu.be/pYW0hyTQne4
ይሄም ማለት ሀገራችን ወደፊት አቅም ሲኖራት በዓባይ ወንዝ ላይ ለመስኖ ልማት የሚያገለግል ግድብ ገድባ በመስኖ መልማት የሚችለውንና የዓለምን ገበያ በግብርና ምርት የማጥለቅለቅ አቅም ያለውን አራት ሚሊዮን በመስኖ መልማት የሚችል ሔክታር ለም መሬት የዓባይን ውኃ በመጠቀም ፈጽሞ ማልማት አትችልም ማለት ነው!!! ይሄ ታዲያ የኢትዮጵያን የወደፊት የመልማት ተስፋ ማጨለምና ማጨናገፍ እንደሆነ የሚጠፋው ሰው አለ ወይ??? ታዲያ ዝምታው ምንድን ነው???
በዚህ አደገኛ ውል የተነሣ ይሄንን ያህል አደጋ ተጋርጦብን እያለ እንደምታዩዋቸው “ለሀገርና ለሕዝብ ቆመናል!” የሚሉ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክና የእምነት ተቋማት እንዲሁም ምሁራን ምንም እንዳልተፈጠረ ጸጥ ብለዋል!!!
ሌላው ቀርቶ ውሉን በተመለከተ አገዛዙን ለሕዝቡ እና ለራሳቸውም “ማብራሪያ ይሰጠን!” ብለው እንኳ አልጠየቁም!!! አሁን ታዲያ እነዚህ ናቸው ለሀገርና ለሕዝብ የሚታገሉት፣ የሚሠሩትና የሚያገለግሉት??? ለዚህ ያልጮሁ ለሌላ ለምን ሊጮሁ ነው ታዲያ???
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! አገዛዙ የስምምነቱን ዝርዝር አንቀጾች ግልጽ አድርጎ ሳያሳውቅህና ሳትስማማ የሚፈራረም ከሆነ ይሄ ስምምነት ያንተ ፈቃድና ስምምነት ያልተሰጠውና ያንተ ውክልና በሌለው አንባገነን አገዛዝ በሀገር ክህደት የተፈጸመ መሆኑን አደባባይ ወጥተህ ተቃውሞህን ካላሰማህ ስምምነቱ ያንተ ይሁንታና ፈቃድ እንዳለው ተቆጥሮ መቸውንም ቢሆን የማይጣስ ሆኖ ይጸድቃልና ወደፊት ውሉን ልጣስና ሀገሬን ላልማ ብለህ ብታስብ እንኳ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ “የተስማማቹህበትን ሕግ መጣስ አትችሉም!” ብሎ ከግብጽ ጋር ቆሞ የሚወጋህ በመሆኑ “ግድ የለም ወደፊት ጉልበት ያለው መንግሥት ሲኖረን እንሽረዋለን ችግር የለውም!” የማይባል ነውና ለወደፊቱ ኢትዮጵያዊ መንግሥት ይሄንን የሀገራችንን መብትና ጥቅም ያላከበረ ስምምነት “የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቃውሞት የነበረና የሕዝቡ ውክልና በሌለው አንባገነን አገዛዝ በሀገር ክህደት የተፈጸመ ስምምነት ነው!” ብሎ ውሉን ለመሻር እንዲመቸውና ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው ለማስቻል ግልብጥ ብለህ ወጥተህ ተቃውሞህን በያለህበት የማሰማት ታሪካዊ ግዴታ አለብህ ይሄንን ሳታደርግ እንዳትቀር!!!
እባካቹህ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክና የእምነት ተቋማት፣ ምሁራንና የብዙኃን መገናኛዎች እባካቹህ ሕዝቡ እንዲህ እንዲያደርግና ተቃውሞውን ለታሪክ እንዲያስመዘግብ ያለ የሌለ ኃይላቹህን አሰባስባቹህ ተንቀሳቀሱ???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው