
ህም! ከደቂቃዎች በፊት አቶ ልደቱ ከዐሥራት ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ክፍል ሁለት ስመለከት ነበር፡፡ እንደተለመደው ቅጥፈትና ሸፍጥ ያዘለ ነበር!!!
አቶ ልደቱ ከሁለት ዓመት በፊት የጀቲቪ እንግዳ ሆኖ “እኔ አማራ ሲባል የማውቀው ክርስቲያን ለማለት መሆኑን ነው እንጂ በብሔረሰብ መጠሪያነቱ አላውቀውም!” እንዳላለ ሁሉ ለዚህ ክህደቱ አማራን ይቅርታ ሳይጠይቅ ዛሬ ደግሞ ፈራ ተባ እያለ በነገር መሀል “አማራ ነኝ!” ብሎ ቁጭ አለ!!!
የልደቱ ሰብእና ማለት ይሄ ነው እንግዲህ፡፡ ጊዜውን መስሎ የማደር ርካሽና ወራዳ ሰብእና!!!
“ሰው ምን ይለኛል!” ማለት የለ፣ “ሰው ይታዘበኛል!” ማለት የለ፣ “ተሳስቸ ነበር ይቅርታ!” ማለት የለ በፈለገው ጊዜ እንደ እስስት እየተለዋወጠ የቀጣሪውን የወያኔን ጥቅም ማስጠበቅና አስመስሎ ማደር ብቻ!!! ቱ ባይፈጠር በተሻለው ይሄ ቆሻሻ!!!
አቶ ልደቱ ስለ አማራ ብሔርተኝነት ሲጠየቅም “የብሔርተኝነት ደኅና የለውም፡፡ ብሔርተኝነትና ዲሞክራሲ ጨርሶ አይገናኙም፡፡ ብሔርተኝነት ለሀገር ጠንቅ ነው…!” ብሎ እርፍ አለ!!!
ጋዜጠኛው ከፍተኛ የአቅም ውስንነት ስላለበት ሊሞግተው አልቻለም እንጅ የአማራ ብሔርተኝነት እንደሌሎቹ ብሔረሰቦች የብሔርተኝነት ንቅናቄዎች ሀገር ለማፍረስና ለመገንጠል ሳይሆን ሀገርን ከጥፋት ለመታደግ በመሆኑ፣ እንደሌሎቹ የራሱን ብሔረሰብ ከሌሎች ነጥሎ ለይቶ ለመጥቀም የሚደረግ ሳይሆን በዘር ማጥፋት ዘመቻ ጥቃትና ከፍተኛ የመጥፋት ሥጋት ስር ያለውን የራሱን ህልውና ከጥፋት ለመታደግና በአገዛዙ የሰብአዊ መብት ረገጣ ስር ላሉ ሌሎች ዜጎች ሁሉ የቆመ በመሆኑ የአማራን ብሔርተኝነት ከሌሎቹ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ሕዝብ ከሆኑ የባዕዳን ቅጥረኛ የብሔርተኝነት እንቅስቃሴዎች ጋር ደብሎ ማውገዙና ማንቋሸሹ አቶ ልደቱ አሁንም ፀረ አማራ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ከወያኔ የቅጥረኝነት ተልእኮ እንዳለው ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ነው!!!
እውነቴን ነው የምላቹህ አቶ ልደቱ አማራነት የሚሰማው፣ ለአማራ ቀና ስሜት ያለው፣ ከዘር ማጥፋት ጥቃት እስከ የሰብአዊ መብት ገፈፋ ድረስ አማራ በአገዛዙ ለ29 ዓመታት ያለማቋረጥ የተፈጸመበት አረመኔያዊ ግፍና ሰቆቃ የሚሰማው፣ የሚከነክነው፣ የሚያሳስበው ቢሆን የአማራ ብሔርተኝነት ትግል በበቂና አሳማኝ ምክንያትና ዓላማ ያውም እጅግ ዘግይቶ የተቀሰቀሰና የተመሠረተ መሆኑን አፉን ሞልቶ ደረቱን ነፍቶ ይመሰክርና ይደግፍም ነበር እንጅ ፈጽሞ ከጠባብ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ሕዝብ የጥፋት ኃይሎች ጋር ደምሮ ሊያወግዘውና ሊኮንነው አይችልም ነበር!!!
በነገራችን ላይ አቶ ልደቱ “ወያኔ በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት ፈጽሟል!” ብሎ እንደማያምን ታውቃላቹህ??? ከዓመት በፊት አገዛዙ ኦሮሚያ ብሎ በሚጠራው የሀገራችን ክፍል በአማሮች ላይ የመፈናቀልና የግድያ ጥቃት ተፈጽሞ ከጥቃቱ ጀርባ ስላለው አካል ማንነት ከሁለት እንግዶች ጋር በአሜሪካ ድምፅ ቀርቦ “መንግሥት ከዚህ ጥቃት ጀርባ አለ ብላቹህ ታስባላቹህ ወይ?” ተብለው ሲጠየቁ ልደቱ “እኔ ፈጽሞ መንግሥት ለምንም ዓላማ ቢሆን ሆን ብሎ በገዛ ሕዝቡ ላይ እንዲህ ዓይነት ጥቃት ይፈጽማል ብየ አላምንም!” ብሎ ነበር የመለሰው!!!
አሁንም ብትጠይቁት እርግጠኛ ነኝ “አዎ ሕወሓት በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት አልፈጸመም!” ይላቹሃል፡፡ አቶ ልደቱ ወያኔ ከበረሃ ጀምሮ አማራን የማጥፋት ማኒፌስቶ ቀርጾ መጥቶ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት ጥቃት በመላ ሀገሪቱ ሲፈጽምና ሲያስፈጽም እንደኖረ ስለማያውቅ ይመስላቹሃል “ፈጽሞ አላምንም፣ አልፈጸመም!” የሚለው???
በሉ እንግዲህ ይሄ ጉደኛ ባንዳ ከዚህም በኋላ ገና ብዙ ጉድ ይሠራናልና ጉድ ለመሠራት ተዘጋጁና ጠብቁት እሽ እነ ዘገምተኞ???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው