አቶ ማሙሸት ከብአዴኑ ሚዲያ ከዐሥራት ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ክፍል አንድ ተመለከትኩት፡፡ አየ አቶ ማሙሸትiii ኦነግ ሠራዊቱን ይዞ ገብቶ ሀገር እያወከ፣ እንደትናንቱ ሁሉ አማራን የትም በግፍ እየገደለ፣ ባንክ እየዘረፈ፣ ምድረገኝ ላይ ካምፕ ገንብቶ እያሸበረና ወሎን ሰሜን ኦሮሚያ!” እያለ ጥቅሙን በኃይል እያስከበረስና ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ ሀገር ውስጥ ገብቶ በሰላማዊ ትግል እንዲወዳደር ያበቃነው እኛ ነን!” ብሎ እርፍ!!!

አየ የኛ በሳሉ ፖለቲከኛ!!! እየሆነ ያለውን ጉድ ሁሉ አይሰማም ዓያይም እንዴ ይሄ ሰውየ??? ዝንጉ ሰው እንኳ ቢሆን ቢያንስ እንኳ ሰሞናዊውን ግፍ እንዴት ይረሳዋል???

እኔ የዚህ ሰውየ ነገር የበቃኝ አገዛዙ ሴራ አሲሮና በሐሰት ወንጅሎ ሰኔ 15 ላይ ጀግኖቻችንን እነ ጄኔራል አሳምነው ጽጌን በግፍ የገደለ ጊዜ በኢቴቪ ቀርቦ እነ አሳምነውን እያወገዘ እኛ ከኢሕአዴግ ጎን ነን!” ያለ ቀን ነው!!! ያን ዕለት ወዲያውኑ ነበር ስልክ ደውየ ምን ለማለት ፈልጎ እንዲህ እንዳለ የጠየኩት፡፡ ሊሰጠኝ የቻለው አንድም መልስ ግን አልነበረውም፡፡ በጣም ወቀስኩት ንዴቴን መቋቋም አልቻልኩም ነበረ፡፡ ጆሮየ ላይ ነበር ስልኩን የዘጋው!!!

ይታያቹህ ይሰማቹህ በአማራ ትግል ላይ ተዘምቶ የአማራ ትግል እየተመታ፣ ጀግኖቻችን እየተጨፈጨፉ ከመችው ከጨፍጫፊው ግፈኛ አገዛዝ ጎን ነን!” ሊል የሚችል የአማራ ታጋይ ምን ዓይነት የአማራ ታጋይ ነው???

ማሙሸት ብዙ ዋጋ የከፈለለትን ወገንና ትግል ከድቶ አዲስ ማንነት እንደተላበሰ የገባኝ ያኔ ነበር፡፡ ከዛ መለስ ብየ ነገሮችን ማሰላሰልና መመርመር፣ ቀደም ሲል የተናገራቸውን ነገሮች ማጤን ያዝኩኝ፡፡ ነገርየው ወደሌላ አቅጣጫ መራኝ፡፡

እንደምታውቁት ወያኔ እንደ ቅንጅት ሁሉ ዓይን ባወጣና ባፈጠጠ የውንብድና ተግባር አንድነትንና መኢአድን ማርኮ የራሱ አድርጓቸው ቆይቷል፡፡ እነ ተስፋሁን ያኔ ነበር ድርጅታቸውን ሕገወጥ በሆነ በውንብድና ተግባር ሲነጠቁ የሰላማዊ ትግል በር ተጠርቅሞ እንደተዘጋ ስለገባቸው የትጥቅ ትግል ለማኪያሔድ ወደ ኤርትራ ሔደው አዴኃንን ለመመሥረት የበቁት፡፡ ወያኔ አንድነትንና መኢአድን መዚያ መልኩ ከተቆጣጠረና ቅጥረኞቹን ካስቀመጠ በኋላ እንዴት ሲጠቀምባቸው እንደኖረ የምታውቁት ነው!!!

መጨረሻም ወያኔ/ኢሕአዴግ ለውጥ የሚል የማጃጃያ ድራማ አመጣና የፖለቲካ እስረኞችን ሲፈታ እነ ማሙሸትም ተፈቱ ጥቂት ቆይቶም ማሙሸት በአገዛዙ ቁጥጥር ስር ያለውንና የአገዛዙን የፖለቲካ ጥቅም ሲያስጠብቅ የቆየውን መኢአድን እንዲመራ በሊቀመንበርነት ተሠይሞ ቁጭ አለ!!!

በሰዓቱ ይሄ ነገር ሲሆን ለእኔ የደረሰኝ ዜና እነ ማሙሸትና መኢአድን ይዘውት የቆዩት የወያኔ አገልጋዮች ተነጋግረው እርቅ በመፍጠራቸው ማሙሸት በሊቀመንበርነት ተሾመ!” የሚል ስለነበር ነገሩን ሳልመረምረው በየዋህነት ተነጋግረው ችግራቸውን ከፈቱማ ብየ ደስታየን በመግለጥ ፌስቡክ ላይ ሕዝቡ ከመኢአድ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ አሁንም ብትገቡ ታገኙታላቹህ፡፡ ለካ ነገሩ ሌላ ኖሯል!!!

እነ ማሙሸት አማረ ያሉበትን የእንቁጣጣሽ ወይም የመስቀል የዐሥራት ቴሌቪዥንን የበዓል ዝግጅት ማለትም ማሙሸት አማረ የታደመበትን ተመልከቱት፡፡ እዚያ ላይ ማሙሸት ታይቶኝ ስለነበረ!” ይልና ስለ የፖለቲካ እስረኞች መፈታት ገና ወሬው እንኳ ባልተሰማበት ጊዜ እስረኞች ሊፈቱ መሆኑን ለእስረኞቹ መናገሩን ይናገራል፡፡ እውን ሆኖ እስረኞቹ በተፈቱ ጊዜ እንዴት አውቆ ያኔ እንፈታለን!” ብሎ እንደነገራቸው እስረኞቹ እንደጠየቁትም ይናገራል፡፡ ያኔ አስቀድሞ በመናገሩና የተናገረውም በመፈጸሙ የጠረጠሩት ሰዎች ጥቂት አይደሉም!!!

ነገሩ እንዴት መሰላቹህ ወያኔ/ኢሕአዴግ የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት እንደወሰነ ከዋና ዋናዎቹ የፖለቲካ እስረኞች ጋር በለውጡ ኃይል ስም ተደራድሮ ነበር፡፡ የለውጥ ኃይል!” በሚል የገጸባሕርይ ስም የሚተውነው የወያኔ ቅጥረኛ ቡድን ከእነኝህ ዋና ዋና እስረኞች ጋር ሲደራደር ወያኔ እንደወደቀና ሥልጣኑን የለውጥ ኃይል እንደተረከበ፡፡ ይሄ የለውጥ ኃይልም ከእነሱ ጋር መሥራት እንደሚፈልግና እንደሚፈታቸው በመንገር ነበር አታሎ የተደራደራቸው!!!

ያለኝ መረጃ የሚያሳየው ሁሉም የተደራደራቸው እስረኞች እንደተስማሙ ነው፡፡ ይሄ መረጃ ትክክለኛ ነው!” ብየ መቶ በመቶ እንዳልቀበለው ያደረገኝ ብቸኛው ሰው እስክንድር ነጋ ነው፡፡ እስክንድር መጀመሪያ ላይ ለውጥ የሚባለውን ድራማ ያደንቅና ይቀበል ስለነበረ ጠርጥሬው ነበር፡፡ በኋላ ግን እነ ስንታየሁ ቸኮል ባልደራስን ጠነሰሱና ወደ ባልደራስ ከተውት ለውጥ ከሚባለው ድራማ ጋር ሲጣላ ቆይ እስኪ!” አልኩኝ፡፡ ይሄው እስከአሁንም ቆይ እስኪ!” እንዳልኩ ነው!!!

መሀል ላይም ባልደራስ ባለፈው መስከረም ላይ ሰላማዊ ሰልፍ የጠራ ጊዜ የአዲስ አበባ ሕዝብ ከትንሽ እስከ ትልቅ በዚሁ ሰልፍ ላይ ለመሳተፍ አሰፍስፎ እየጠበቀና ወጣቱ ቀኑ አልደርስ ብሎት በየመንደሩ እየጨፈረ እየተነቃቃ ውስጥ ውስጡን ተጋግሞ ሰልፉ ሳይታሰብ ከ1997ቱ ሰልፍ የላቀ ቀውጢ ሰልፍ ሊሆን እንደሚችል ተገምቶ ሰዓቱ እየተጠበቀ እያለ ከፍተኛ ሥጋት ላይ የወደቀው አገዛዙ መጨረሻ ሰዓት ላይ ሰልፉ ፈቃድ አልተሰጠውም!” ብሎ ኢሕገመንግሥታዊ በሆነ ምክንያት ሰልፉን ሲከለክል እስክንድር ይሄንን ኢሕገመንግሥታዊ ምክንያት በመቀበልና ለኢሕገመንግሥታዊው አሠራር ዕውቅናና አክብሮት ሰጥቶ ፈቃድ አልተሰጠውም ከተባለ ሕጉን አክብረን ሰልፉን እንሰርዘዋለን!” ብሎ ሰልፉን ሰርዞ አገዛዙን ከጉድ ሲያወጣው “I got you bitch!” ብየው ነበር፡፡ ለማንኛውም የእስክንድርን ጉዳይ በቅርቡ የምናረጋግጥ ይመስለኛል፡፡ የመሠረተውን ፓርቲ ከነ አብንና ከነ ልደቱ ጋር ካጣመረው ላያችን ላይ ሲተውንብን እንደቆየ ያረጋግጥልናልና ያ መረጃ መቶ በመቶ ትክክል እንደሆነ አረጋግጣለሁ!!!

ሌሎቹ የተቀሩት ሁሉ ግን በየጊዜው ከፈጸሟቸው ክህደቶች መረጃው ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጫለሁ፡፡ ለምሳሌም እነ ጄኔራል አሳምነው በተገደሉ ጊዜ እነ አሳምነውን በአገዛዙ ሚዲያ ቀርቦ ከሀዲዎችንና ፀረ ሕዝብ ናቸው!” ያለው ከሀዲው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንና ማሙሸት አማረን መጥቀስ ይቻላል፡፡ አገዛዙ እነ ጄኔራል አሳምነውን በእነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና መሰሎቹ ሲሰልል ነው የቆየው፡፡ አገዛዙ እነ አሳምነውን መግደል እንዳለበት የወሰነው ከነ ኮሎኔል ደመቀ በሚያገኘው መረጃ ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡ እነ ጄኔራል አሳምነው ኮሎኔል ደመቀን ፈጽሞ ስለማይጠረጥረው የልቡን ማለትም ዓላማውንና እቅዱን ሁሉ ለደመቀ ይነግረው፣ ያማክረውና ያዋየው ነበር!!! ሌሎቹን ከሀዲዎችን ግን ብዙዎቻቹህ ስለማታውቋቸው እተዋቸዋለሁ!!!

እንግዲህ ማሙሸት እስረኛው እንደሚፈታ የተናገረው ነቢይ መይም ጠንቋይ ሆኖ ሳይሆን የለውጥ ኃይል መስሎ ከሚተውነው አካል ጋር ሲደራደር ካገኘው መረጃ ተነሥቶ ነበር አላስችል ብሎት የፖለቲካ እስረኛውን እንደሚፈቱ የተናገረው፡፡ እሱ ግን ታይቶኝ ስለነበረ ነው!” ነው ያላቸው፡፡ በሕልሜ ዓይቸ ነው፡፡ ሕልሜም ስለማይስትና ክሱት ስለሆነ ነው እርግጠኛ ሆኘ የነገርኳቹህ!” ቢል እንኳ የተሻለና የሚመስል በሆነ ነበር ታይቶኝ ስለነበረ ነው!” ከሚል ይልቅ!!!

እናም ማሙሸት በወያኔ ቁጥጥር ስር ባለው መኢአድ ላይ በሊቀመንበርነት የተሾመው በድርድራቸው መሠረት ነው ማለቴ ነው፡፡ ከአገዛዙ ጋር በተስማማው መሠረትም ለአገዛዙ ተቀጥሮ አገዛዙን ለማገልገል ስለተሾመም ነው በሰኔ 15ቱ የፀረ አማራ ትግል ዘመቻና የግፍ ግድያ ወቅት አርበኞቻችንን እነ አሳምነውን እያወገዘ ከኢሕአዴግ ጎን ነን!” ሲል ሊናገር የቻለው!!!

አንድ ሌላ ጠቋሚ ነገር ልጨምርላቹህ፡፡ አሁን ላይ ማሰብ ማሰላሰል ማገናዘብ ለማይችል ዘገምተኛ ካልሆነ በስተቀር ዐሥራት ቴሌቪዥን የብአዴን እንደሆነና ሲቋቋምም ብአዴን ከጀርባ ሆኖ ዐሥራት ቴሌቪዥን የሕዝብ አመኔታ እንዲያገኝ በአማራ ትግል ሕዝብ የሚያውቃቸውን ወገኖች ከፊትለፊት በማሰለፍና ሕዝብን በማታለል የሕዝብ ሚዲያ አስመስሎ ከጀርባ ሆኖ እንደመሠረተው ቢያንስ አሁን ላይ ግልጽ ይመስለኛል!!!

ዐሥራትን በመመሥረት ሒደት ብአዴን ከፊት አሰልፎ ሕዝብን ካታለለባቸው ግለሰቦች አንዱ ደግሞ ማሙሸት አማረ መሆኑን ታስታውሳላቹህ፡፡ ሌሎቹ ኮሎኔል ደመቀና ኢንሳ በተባለው በወያኔ የስለላ ድርጅት ሰላይ ሆኖ ሲሠራ የነበረውና ተቃዋሚዎችን እንዲሰልል ስለተፈለገ ከተቋሙ የተባረረ መስሎ እንዲወጣ ተደርጎ ተቃዋሚዎችን ከቢሮ እስከ እስርቤት ሲሰልል የቆየው ጌታቸው ሽፈራውና ሌሎቹም በሒደት ማንነታቸው የታወቁ ግለሰቦች መሆናቸውን ታውቃላቹህ፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ዐሥራትን በመመሥረት ሒደት ላይ ፊት ተሰላፊ የሆኑት በአጋጣሚ ሳይሆን በብአዴን ተመድበው ነበር ሲንቀሳቀሱ የነበሩት፡፡ እንግዲህ ነጠብጣቦችን ገጣጥማቹህ ስትመለከተቱ የምታገኙት የማሙሸት አማረና የመሰሎቹ ሥዕል ይሄ ነው!!!

ከዚህ ምን ትረዳላቹህ ወገኖቸ??? አማራ ጠላቶቹ ካስቀመጡበት እስር ቤቱ ሰብሮ እንዳይወጣና አንዱን አጥር ሰብሮ ቢወጣ እንኳ በሌላው አጥር እንዲያዝ ይሄንንም ሰብሮ ቢያልፍ ደሞ በሌላው እንዲያዝ ዙሪያውን በበርካታ አጥሮች በታጠረበት እስር ቤት ውስጥ ያለ ሆኖ አይሰማቹህም??? እኔን እንደዚያ ነው የተሰማኝ፡፡ የእኛ ሕዝብ ይሄንን ሁሉ ጉዱን አያውቅም ስንነግረውም አይሰማም አይቀበልም፡፡ ጭራሽ እንዲያውም አስቀድሞ በአማራ ትግል ጨርሶ የማይታወቁ ምድረ የወያኔ/ኢሕአዴግ ካድሬ በግልጽ አብን ብሎ ተደራጅቶ መጥቶ ድርጅትህ ነኝ!” ሲለው አምኖ የሚቀበልና የሚጃጃል የመጨረሻ የዋህ ሕዝብ ነው፡፡ የዚህን ያህል ጅል ሕዝብ ነው!!!

ጠላቶቻችን ግን የገዛ ወገኖቻችንን ያውም ብዙ ዋጋ የከፈሉልን የነበሩትን ሳይቀር በገንዘብና በጥቅም ገዝተው በእኛ ላይ ሰላይና ጠባቂ አድርገው እስከማስቀመጥ ድረስ እጅግ ረቀው ዙሪያችንን በርካታ አጥሮችን አጥረውብናል!!! ወገን ሆይ ማወቅ ያለብህ ነገር ቢኖር ጠላቶቻችን እኛ እንደተቀበርን እንድንቀር ለማድረግ የማይከፍሉት ዋጋ፣ የማይወጡት ዳገት፣ የማይወርዱት ቁልቁለት የሌለ መሆኑን ነው!!! ወገን እንግዲህ ምን ያህል ንቁ፣ ጠንቃቃና ጠንካራ ሆነህ አማራጭ የሌለውን የህልውና ትግላችንን ቆርጠን ጨክነን መታገል እንዳለብን እንረዳ!!! ካልሆነ ነገራችን ሁሉ ሁልጊዜ የእንቧይ ካብ ነው የሚሆነው!!!

እኔ ደጋግሜ ነግሬያቹሃለሁ ወያኔ/ኢሕአዴግ ስሙን እየቀየረም ይሁን የተከፈለ እየመሰለ በቁም እስካለ ጊዜ ድረስ የአማራ ማንንትሴ እያለ ቅጥረኞቹን እያደራጀ እየሰጠህ ሲያጃጅልህ ይኖራል እንጅ በምንም ተአምር ቢሆን አማራ በነጻነት ተደራጅቶ ለራሱ እንዲሆን ይፈቅዱልናል ብላቹህ ካሰባቹህ በአማራ ላይ ምን ሲሠራ እንደኖረና ጠላቶቹ አማራን በተመለከተ ምን ዓላማና እቅድ እንዳላቸው ጨርሶ ምንም የማታውቁ፣ ነገር ምንም የማይገባቹህ መሆናቹህን ዕወቁ!!!

እንቅጩን ልንገራቹህ ወገኖቸ??? ከበፊት ጀምሬ ደጋግሜ ነግሬያቹሀለሁ አሁንም እነግራቹሃለሁ በምንም ተአምር ቢሆን የአማራ ጥያቄ በዚህ አገዛዝ ዘመን ፈጽሞ አይመለስም!!!

በዚህ አገዛዝ ስር የሚደረግ ምርጫም በምንም ተአምር ቢሆን ነጻ፣ ፍትሐዊና ተአማኒ አይሆንም!!! ነጻ ፍትሐዊና ተአማኒ ምርጫ ሳይደረግም አማራ እሱን በሚወክሉ ታማኝ ልጆቹ ተወክሎ እራሱ በመረጠውና ጥያቄዎቹን በሚመልስለት አካል ሊመራ ሊተዳደር አይችልም!!!

ያለህ ምርጫ ለመራር ትግል መራር ዋጋ ለመክፈል ቆርጠህና ጨክነህ ተነሥተህ በታማኝ ልጆችህ ተናበው የሚሠሩ የኅቡዕ ወይም የስውር እና የግልጽ ድርጅቶችን መሥርተህ የቆረጠ ዐመፅ መር ትግል ማድረግ ብቻ ነው!!!

ስለ ነገ አያሳስብህ እነዚህ እስካሉ ጊዜ ድረስ ያንተ ነገ የለምና፡፡ እንደምታየው ቀኑ ለአማራ የባሰ መከራና ግፍ እንጅ የተሻለ ቀን ይዞ አይመጣምና ነገን ተስፋ በማድረግ ከምንም ነገር የምትቆጠበውን ነገር እርግፍ አድርገህ ትተህ ቆርጠህና ጨክነህ ተነሥ!!!

ምርጫንም ሆነ ምን ተስፋ በማድረግ በከንቱ የምታባክናት እያንዳንዷ ቀን ለጠላቶችህ ይበልጥ ተጠናክረው የሚመጡበትን ዕድል ሲሰጣቸው ላንተ ደግሞ መከራህ ይበልጥ እንዲከብድና እንዲመር ዕድል የሚሰጥ ነውና እያንዳንዷን ቀን በከንቱ ስታባክናት ይሄንን አስብ!!!

ድል ለአሳረኛው አማራ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው