አማራ አንድ ነገር ባሰበ ቁጥር እየጠለፈ የመውሰድ ግቡን እንዳይመታ የሚያደርገው ቀንደኛ ጠላታችን የወያኔ አህያ ብአዴን ነገ የሚደረገውን ሰልፍ ከጀርባ ተቆጣጥሮት ሰልፎቹ ሕዝቡ ቁጣውንና ስሜቱን የሚገልጥባቸው እንዳይሆኑና እራሱ ያዘጋጃቸው መፈክሮች ብቻ ተሰምቶባቸው የሚበተኑ አልጫ ሰልፎች እንዲሆኑ ለማድረግ ካድሬዎቹንና ቅጥረኞቹን አሠማርቷል!!!

ወገን ሆይ! ፀረ አማራው ብአዴን ሰልፎችን የረባ የሕዝብ ድምፅ እንዳይሰማባቸው አድርጎ እንዲበተኑ ለማድረግ ቢጥርም እኛ ግን በዚህ ሰልፍ በ1. ደረጃ የምናወግዘውና ተጠያቂ የምናደርገው አካል ቢኖር እራሱን ቀንደኛ ጠላታችንን ብአዴንን መሆን አለበት!!!

በቁ. 1 ደረጃ ብአዴን ተጠያቂ የሚሆንበት ምክንያት፦

1. በየዓመቱ ተማሪዎቻችን በየዩኒቨርሲቲው ችግር ሲፈጠርና ተረጋግተው መማር የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሮ ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ችግራቸውን የአማራ መንግሥት ነኝ!” ለሚለው ብአዴን ለማቅረብና መፍትሔ ለማግኘት ተሰባስበው ባሕርዳር በመገኘት ባመለከቱ ቁጥር በልዩ ኃይል እያስቀጠቀጠ ከማስበተን ውጭ እንደ የአገዛዙ አካልነቱ ጥያቄዎቻቸውን በተገቢው መንገድ ተቀብሎ ተገቢውን የመፍትሔ እርምጃ እንዲወሰድ አድርጎ ስለማያውቅና ተማሪዎቻችንን ለዚህ አረመኔያዊ ጥቃት ያጋለጣቸው ዋነኛው አካል እሱ እራሱ በመሆኑ!!!

2. የተማሪዎቻችን መጠለፍ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ለችግሩ ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ ተጠላፊዎቹን ለማስመለስ ፈጽሞ ባለመሞከሩ!!!

3. ልጆቻቸው በአሸባሪ ኃይል መጠለፋቸውንና የልጆቻቸው ሕይዎት አደጋ ላይ መሆኑን በማመልከት የሕግ አካል እንዲደርስላቸው ለማመልከት የአማራ መንግሥት ነኝ!” ለሚለው ለማመልከት የሔዱ የቤተሰቦቻቸውን አባላት እያሸማቀቀና እያዋረደ በቁስላቸው ላይ እንጨት በመስደድ በግፍ ላይ ግፍ በመፈጸሙ!!!

4. በአቶ ንጉሡ ጥላሁን በኩል ሆን ብሎ ሐሰተኛ መረጃ በመልቀቅ በተማሪዎቹ፣ በቤተሰቦቻቸውና በአማራ ላይ በማላገጥ የሥነልቡና ጥቃት በማድረሱ!!!

5. ብአዴን ተማሪዎቻችንን ያስጠለፋቸው አገዛዝ አካል በመሆኑና በተማሪዎቹ ላይ በደረሰው ችግር ሁሉ የእሱም እጅ ያለበት በመሆኑ!!!

በእነዚህና በሌሎችም ምክንያቶች ሕዝቡ ነገ በሚያደርገው ሰልፍ ቁ. 1 ጠላቱን ብአዴንን አምርሮ ማውገዝና ተጠያቂ ማድረግ ይኖርበታል!!!

በሰልፉ ላይ ማቅረብ የሚኖርበት ጥያቄዎች ደግሞ፦

1. ብአዴን በአማራ ሕዝብ የተመሠረተ ባለመሆኑና የአማራን ሕዝብ ጥቅም ለአንድም ቀን ቢሆን አስጠብቆ የማያውቅ ይልቁንም የፀረ አማራ የጥፋት ኃይሎች ወኪል በመሆኑና ሕዝባችንን ሲያስበላ የኖረና እያስበላም ያለ ቁ. 1 የአማራ ጠላት በመሆኑ በዚህም ምክንያት የአማራን ሕዝብ የማሥተዳደር ሕጋዊም ሆነ ሞራላዊ መብትና መሠረት ስለሌለው ሥልጣሉን ለሕዝብ እንዲያስረክብ!!!

2. ለዘመናት እንደ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ላይ እና በአማራ ተማሪዎች ላይ ሲፈጸም የኖረው ሆን ተብሎ በእቅድና በዝግጅትየሚፈጸሙ የአሸባሪ ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ!!!

3. የታገቱ ተማሪዎቻችን በአስቸኳይ እንዲያስለቅቁ!!!

4. አማራን ማኅበራዊ እረፍት ለመንሳት፣ የአማራ ተማሪዎች ተረጋግተው ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉና በውጤታቸው እንዲደክሙ ወይም ተፎካካሪ እንዳይሆኑ ለማድረግ፣ በዚህም ችግር ምክንያት አማራ የተማረ ሰው እንዳይወጣበትና በተማረ ሰው እጦት ሁለንተናዊ ችግር ላይ እንዲወድቅ ወይም እንዲደርስበት ለማድረግ በማሰብ በየዓመቱ በተመሳሳይ ፀረ አማራ ሰቃይ የአማራ ተማሪዎችን የመግደል በተቀሩት ላይም የአካልና ሥነልቡናዊ ጥቃቶችን ያለማሰለስ በመፈጸም ከየዩንቨርስቲው ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለውና ትምህርታቸውን አቋርጠው እየወጡ ወድቀው የቀሩትን ጨምሮ ዘንድሮ ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉትን ከ35-50 ሽህ የሚደርሱ የአማራ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎና ሸዋ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ተመድበው ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ እንዲደረግ!!!

5. በአማራና በአማራ ተማሪዎች ላይ ግፍ የፈጸሙና ያስፈጸሙ የአሸባሪ ኃይል ጭፍሮች ለፍርድ እንዲቀርቡ!!!

6. የአማራ ተማሪዎች በተበደሉና የግፍ ጥቃት ሰለባ በሆኑ እንደገና ደግሞ ሆን ተብሎ በሚሠራ ሴራ ያጠፋቹህ እናንተ ናቹህ!” እየተባሉ ከትምህርት ገበታቸው እንዲባረሩ የተደረጉ የአማራ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ!!!

7. በፀረ አማራ አሸባሪ የጥፋት ኃይሎች ጥቃት ሕይዎታቸውን ላጡ የትምህርት ጊዜያቸው ለተስተጓጎለባቸውና ለተለያየ እንግልት ለተዳረጉ ተማሪዎች አስፈላጊውና ተገቢው የካሳ ክፍያ እንዲፈጸም!!!

ሌላም ካለ ጨምሩበትና እነኝህን ጉዳዮች በሰልፎቹ በሚገባ እናስተጋባቸው!!!

በዚህ አጋጣሚ ለአማራ ሕዝብና ባጠቃላይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ አጥብቄ ማሳሰብ የምፈልገው ጥብቅ ጉዳይ ቢኖር አገዛዙ ያስጠለፋቸውን የአማራ ተማሪዎች ጉዳይ እያደረገ ባለው መልኩ ትክክለኛ መረጃን ደብቆ ሆን ብሎ የተምታታና የተወናበደ መረጃዎችን ከተለያዩ አመራሮቹ እንዲለቀቁ በማድረግና ሕዝብን በማስጨነቅ ሕዝቡ ኢትዮጵያን አሳልፎ ለሸጠበት ወይም በቁሟ ለቀበረበትና በዚህ ሳምንት ከግብጽና ከሱዳን ጋር ሊፈርመው ለተዘጋጀበት የሀገር ክህደት ውል ትኩረት ሳይሰጥና ሕዝቡ ማድረግ የሚጠበቅበትን ተቃውሞ ሳያሰማ ተደፋፍኖ እንዲያልፍ ለማድረግ እየተጠቀመበት ነውና እንንቃ እንጠንቀቅ የክህደት ውሉ እንዳይፈረም እንቃወም!!!

ለተጠላፊ እኅት ወንድሞቻችን ስንጮህ ይሄ ከፍተኛ የሀገር ክህደት የተፈጸመበትን ውል ጉዳይም አንርሳ፡፡ ለሁለቱም ችግሮቻችን ዕኩል ትኩረት ሰጥተን እንንቀሳቀስ እባካቹህ???

ድል ለአማራ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው