አገዛዙ በዚህም በዚያም ብሎ ሰልፎቹን ለማክሸፍ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ እዚህ አዲስ አበባ ከትናንት አመሻሽ እስከ ዛሬ ዕኩለ ቀን ድረስ ኢንተርኔቱን አጥፍቶት ነበር፡፡ ሰልፍ በሚደረግባቸው አካባቢዎችም በተመሳሳይ ኢንተርኔቱን እንዳቋረጠው እገምታለሁ፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ቅጥረኞቹን አሰማርቶ ሰልፎቹን በመጥለፍ የታለመላቸውን ግብ ሳይመቱ እንዲቀሩ ለማድረግ ብዙ ጥሯል!!!
ትናንትና አመሻሹ ላይ “የባሕርዳሩን ሰልፍ አዘጋጅ የባሕርዳር ወጣቶች ማኅበር ነን” ያሉ ቅጥረኞች በብአዴኑ ቴሌቪዥን ዐሥራት ላይ ወጥተው “ከሰልፉ ዓላማ ውጭ በሆነ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ መፈክሮችን አናስተናግድም፣ ከእኛ ፈቃድ ውጭ መንቀሳቀስና እንቢተኝነትንና ቁጣን ያዘለ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም….!” እያሉ በርካታ ማስጠንቀቂያዎችን ለሕዝቡ አስተላልፈው ነበር!!!
ትናንትና በጻፍኩት ጽሑፍ “አማራ አንድ ነገር ባሰበ ቁጥር እየጠለፈ የመውሰድ ግቡን እንዳይመታ የሚያደርገው ቀንደኛ ጠላታችን የወያኔ አህያ ብአዴን ነገ የሚደረገውን ሰልፍ ከጀርባ ተቆጣጥሮት ሰልፎቹ ሕዝቡ ቁጣውንና ስሜቱን የሚገልጥባቸው እንዳይሆኑና እራሱ ያዘጋጃቸው መፈክሮች ብቻ ተሰምቶባቸው የሚበተኑ አልጫ ሰልፎች እንዲሆኑ ለማድረግ ካድሬዎቹንና ቅጥረኞቹን አሠማርቷል….!” ብየ ሕዝቡ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚገልጥ ጽሑፍ በለጠፍኩ ጊዜ አንዳንድ ቅጥረኞች ኡኡ ብለውብኝ ነበር፡፡ ቅጥረኞቹ ትናንት በዐሥራት ቴሌቪዥን ያስተላለፉትን ማስጠንቀቂያና ዛሬ ያደረጉትን ደግሞ ዓይታቹሃል፡፡ ከዚህ በላይ የሰልፍ መጠለፍ አለ ወይ???
“ከሰልፉ ዓላማ ውጭ በሆነ ጉዳይ ላይ ያተኮሩ መፈክሮችን አናስተናግድም፣ ከእኛ ፈቃድ ውጭ መንቀሳቀስና እንቢተኝነትና ቁጣ ያዘለ እንቅስቃሴ ማድረግ አይቻልም አይፈቀድም….!” ያሉ እነኝህ ቅጥረኞች ካስጠነቀቁት ውጭ የሆነ ሰው ቢያጋጥማቸው ምን የሚያደርጉ ይመስላቹሃል??? እዛው ላይ የጸጥታ አካል ጠርተው ያሳስሩታል፡፡ ያደረጉትም ይሄንን ነው፡፡ ከዚህ በላይ ቅጥረኝነት አለ ወይ???
ከዚህ ቀደም በየከተማው እየተመሠረተ ካለው የወጣት ማኅበራት ጀርባ ብአዴን መኖሩንና አደራጆችም ካድሬዎች መሆናቸውን ነግሬያቹህ ነበር፡፡ ይሄ የባሕርዳሩ ወጣት ማኅበር አስነዋሪና ወራዳ የቅጥረኛ እንቅስቃሴ ጥሩ ማረጋገጫ የሚሆናቹህ ይመስለኛል፡፡ የሚያሳዝነው እነዚህ ቅጥረኞች ይሄንን ሰልፍ ማኮላሸታቸው ብቻ አይደለም፡፡ ከዚህም በኋላ አማራ አንድ ጉዳይ ገጥሞት ሰልፍ ማድረግ በፈለገ ጊዜ ቁጥር “የሰልፍ አደራጅ ነን!” እያሉ እየጠሩ ሰልፍ እየጠለፉ የሚያኮላሹ መሆናቸውና መቸም ጊዜ ቢሆን አማራ ትክክለኛ ቅሬታውን፣ ስሜቱንና ቁጣውን የሚገልጥበት ሰልፍ መቸም የማይደረግ መሆኑ ነው እጅግ አሳዛኙ ነገር!!!
ብአዴን የሕዝብ አስመስሎ በካድሬዎቹ የወጣት ማኅበራትን ያደራጀበት ዋነኛ ዓላማና ምክንያት ይሄ ነው፡፡ በእነሱ በኩል ሰልፍ እየጠለፈ ለማኮላሸትና የስለላ ሥራ እንዲሠሩለት ለማድረግ፡፡ ይሄንን የባሕርዳር ወጣቶች ማኅበርን ሸፍጠኛ ተግባር የጎንደር ወጣት ማኅበርም በተደጋጋሚ አድርጎታል፡፡ ይሄው የባሕርዳር ወጣት ማኅበርም ከዚህ ቀደም ባሕርዳር በተደረገ ሰልፍ ላይ ስሜታቸውን በቁጣ ሲገልጡ የነበሩትንና ጠንከር ጠንከር ያለ መፈክር ሲያሰሙ የነበሩትን ወገኖችን ከመሀል እየለየ በማውጣት “ረብሻ ለመቀስቀስ ጥረት አድርገዋል!” እያለ እየያዘ ለጸጥታ አካላት በማስረከብ እንዳሳሰረ የምታስታውሱት ጉዳይ ነው!!!
እነኝህ የወጣት ማኅበራት ሕዝብ ሰልፍ የሚያስወጣ ጉዳይ ገጥሞት ገፍቶ ሰልፍ ለማድረግ ባሰበ ጊዜ ቁጥር ተሽቀዳድመው የሰልፍ አደራጅ ሆነው የሚቀርቡት ለዚህ ነው፡፡ ሰልፎቹ ከቁጥጥር ውጭ ሆነው ለአገዛዙ ችግር እንዳይፈጥሩ ለማድረግ፡፡ ሥራቸው ሰልፍ እየጠለፉ ማኮላሸትና ሰልፎቹ የታለመላቸውን ግብ እንዳይመቱ ማድረግ እንዲሁም የስለላ ሥራ መሥራት ነው!!!
አማራ ሆይ! ከዚህ በኋላ በምታደርገው ሰልፍ ሰልፉ የታለመለትን ግብ እንዲመታና በሰልፉ ላይ ማስተጋባት የምትፈልገውንና ያለብህን መፈክር ማሰማትና የሚፈጸምብህ ግፍ የፈጠረውን ቁጣና ስሜት በትክክል መግለጥ ከፈለክ ሰልፎችህ በእነኝህ ቅጥረኛ የወጣት ማኅበራት እንዳይጠለፍ ተጠንቀቅ፣ ከአጠገብህ እንዳይደርሱም ተከላከል!!!
እነዚህ ትናንት የባሕርዳሩን ሰልፍ ያዘጋጀን የባሕርዳር ወጣት ማኅበር ነን ብለው በዐሥራት ቴሌቪዥን የቀረቡ ሰልፍ ወይም ትግል ጠላፊ የብአዴን/ወያኔ ቅጥረኞች ማስጠንቀቂያዎቻቸውን ሲያዥጎደጉዱ የቅጥረኝነት ተግባራቸውን የጀመሩት ለሰልፉ ፈቃድ መጠየቃቸውንና ፈቃድ ማግኘታቸውን በመግለጥ ነበር!!!
እንዲህ ዓይነት ሕጋዊ አሠራር የለም!!! ይሄ አሠራር ኢሕገመንግሥታዊ የአፈና አሠራር ነው፡፡ ይሄንን ኢሕገመንግሥታዊ የአፈና አሠራር ሕጋዊ አስመስሎ ዕውቅና መስጠትና ሕዝብ አሠራሩን እንዲያከብርና እንዲከተል ለማድረግ መጣር ሌላኛው ቅጥረኝነታቸው ነው፡፡ ሕገመንግሥታቸው “አስታውቅ!” ነው እንጅ “አስፈቅድ!” የሚል ድንጋጌ የለውም፡፡ ማስፈቀድ የሚባል ነገር በዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌ “የአፈና ድንጋጌ ነው!” የሚል ብያኔ የተሰጠው አሠራር በመሆኑና በነጻ የመሰብሰብ፣ በነጻ ሰልፍ የማድረግ፣ በነጻ ሐሳብን የመግለጽ መብቶች ላይ ገደብ የሚያሳርፍ አንባገነናዊ አሠራርን ስለሚያመላክትና በሕዝብ ላይ እነኝህን ገደቦች ማሳረፍ ስለማይቻል ነው “ማስፈቀድ!” የሚል ቀርቶ ጸጥታ አስከባሪ አካላትን ለመመደብ እንዲያመችና ሰልፉ የሚደረግበት ስፍራ ሌላ አስቀድሞ ያስታወቀ ሰልፍ ወይም ሕዝባዊ ስብሰባ ያለ እንደሆነ መደራረብ እንዳይፈጠርና በአግባቡ ለማስተናገድ ዓላማ ብቻ “ማሳወቅ!” ግዴታ ሊሆን የቻለው፡፡ ምንም እንኳ አገዛዙ ለአንድም ቀን እንኳ ይሄንን የሕዝብ መብት ተግብሮትና አክብሮት ባያውቅም ቅሉ!!!
ምድረ ቅጥረኛ ሆይ! ለመሆኑ ለምንድን ነው እሱ አማራ ለዘመናት ሲፈጸምበት ስለቆየውና እየተፈጸመበት ስላለው ዘርፈ ብዙ ግፍና ሰቆቃ በደሎቹ በዚህ ሰልፍ እንዳይጮህና እንዳያሰማ የፈለጋቹህት???
እንዴትስ ነው ይሄ ሁሉ ግፍ ለ29 ዓመታት የተፈጸመበት አሳረኛ ሕዝብ “ከሰልፉ ዓላማ ውጭ የሆነ መፈክር ማሰማት አይቻልም፣ ከእኛ ፈቃድ ወተህ መንቀሳቀስ፣ ቁጣና እምቢተኝነትን ማንጸባረቅ አትችልም!” የሚባለው??? ለተፈጸመበት አረመኔያዊ ግፍ ቁጣውን ሊያሳይና ግፉን ለሚፈጽምበትና ለሚያስፈጽምበት የግፍ አገዛዙ እንቢተኝነቱን ሊገልጽ ካልሆነ ታዲያ ምን ሊያደርግ ነው ሰልፍ የሚወጣው እነ ቅጥረኞ???
አሁን እውነት አማራ ለተፈጸመበትና እየተፈጸመበት ላለው አረመኔያዊ ግፍ ሁሉ ቁጣና እንቢተኝነት ማሳየቱ በእጅጉ ሲያንሰው እንጅ ይበዛበታል ወይ እነ አህዮ??? ምድረ የወያኔ አህያ እናንተ ምናቹህ ተነክቶ ሆዳቹህን እንደሆነ ብአዴን/ወያኔ/ኦነግ ይሞላላቹሃል እንዴት ብሎ በወገን ላይ የሚፈጸም ግፍና ሰቆቃ ዘልቆ ይሰማቹህ ታዲያ??? ምድረ ቆሻሻ ባንዳ ሁላ!!!
ወገኖቸ መቸም ቅጥረኞቹ እንዲህ የሚያደርጉት ማንን ከምን ችግር ለመጠበቅ እንደሆነ ይጠፋቹሃል ብየ አላስብም፡፡ ይሄንን የሚያደርጉት በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው ፀረ አማራውን ብአዴንን ከሕዝብ ተቃውሞና ውግዘት ለመጠበቅ ለመከላከል ነው!!! አማራ ሆይ! ወዳጅ ጠላትህን እየለየህ ተንቀሳቀስ! ንቃ!!! ቅጥረኛን ፈጽሞ ከአጠገብህ አታድርስ!!!
አይገርማቹህም ግን??? በዚያ በኩል ቄሮ እንደፈለገ ያለ አንዳች ተጠያቂነት ዘግናኝ ዘግናኝ የአሸባሪ ጥቃት መፈጸም እስኪችል ድረስ ፍጹም ስድ ለቀው ያስፈጁናል አማራ ላይ ስትመጡ ግን በገዛ ራሱ ሰዎች፣ በገዛራሱ ልጆች እንዲህ ዓይነት የሴራና የሸፍጥ ትብትብ ተብትበው አስረው ፈጽሞ ነጻ ሆኖ ሌላው ቀርቶ ስሜቱን እንኳ እንዳይገልጽ አድርገው አፍነውታል!!! እኔ እነኝህን ሰዎች እንዴት አድርገው ጭንቅላታቸውን እንዲህ እንዳኮላሿቸውና የታዘዘውን ብቻ እንደሚያደርግና ማሰብ ግን እንደማይችል ሮቦት እራሳቸውን ማለትም አገዛዙን ብቻ በፍጹም ታማኝነት እንዲያገለግሉ ማድረግ እንደቻሉ ሳስበው እጅግ እጅግ እጅግ ይገርመኛል!!! አህያ እንኳ አንዳንዴም አሻፈረኝ ብላ ጭነት ትገለብጣለች፡፡ እነኝህ እኮ ምሳሌ የላቸውም፡፡ ምናልባት ሮቦት የሚለው ይገልጻቸው ይሆናል!!! አያሳዝንም ግን??? እግጅ አያሳፍርም??? በጣም አያሳርርም??? በጣም አያቃጥልም ይሄ ወገኖቸ??? እስከመቸ ድረስ ነው በአህያው ፀረ አማራ ብአዴንና አህያ ቅጥረኞቹ ታፍነህ ጩኸትህን እንኳ እንዳታሰማ ሆነህ የምታልቀው ወገን??? መቸ ነው እነኝህን ነቀርሳዎችህን ነቅለህ የምትጥለው??? ወገን ሆይ ቁ. 1 ቀንደኛ ጠላትህ ፀረ አማራው ብአዴንና ቅጥረኞቹ መሆናቸውን አውቀህ ቀድመህ እነሱን እስካላጠፋህ ጊዜ ድረስ መቸም ቢሆን በምንም ተአምር ነጻ ልትወጣና ህልውናህን ልትታደግ፣ መብትህን፣ ጥቅምህንና ደኅንነትህን ፈጽሞ ልታስጠብቅ እንደማትችል ጠንቅቀህ ዕወቅ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው