አገዛዙና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት የኢትዮጵያን ሕዝብ በኮኖና ቫይረስ ሊያስፈጁት አሲረዋል!!!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአገዛዙ በተሰጠው ትዕዛዝ ምክንያት ረጅም ዘመን የቆየ ነው!” የሚለውን የቻይናንና የኢትዮጵያን ግንኙነት በማሰብና ለቻይና የክፉቀን አጋር ለመሆን በመፈለግ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንደማያቆም በመግለጥ የአየር መንገዱ ማኔጅመንት እጅግ ደካማ የማሰብ፣ የማሰላሰልና አርቆ የማሰብ ብቃት ያለው መሆኑንና አሠራሩን በግምት ወይም ሳይንሳዊ ባልሆነ መንገድ የሚሠራ መሆኑን አረጋግጧል!!!

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በርካታ የዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ከማቆማቸውም ባለፈ በርካታ ሀገራት ከቻይና ለሚነሡ በረራዎች በራቸውን መዝጋታቸውን እየገለጹ ባሉበት ሁኔታ ነው እንግዲህ ደንቆሮው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት ወደ ቻይና የሚያደረገውን በረራ እንደማያቆም ዛሬ የገለጸው!!!

ደንቆሮው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በርካታ የዓለም አቀፍ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቆሙ፣ በርካታ ሀገራትም ከቻይና ለሚነሡ በረራዎች በራቸውን ዘጉ!” የሚለው ዜና ምን ማለት እንደሆነ ጨርሶ አልገባውም!!!

አየር መንገዱ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ የማያቆም ከሆነ ከቻይና ለሚነሡ በረራዎች በራቸውን የዘጉ ሀገራት ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ይዘጋሉ ወይም ማዕቀብ ይጥላሉ ማለት እንደሆነና በዚህም ምክንያት ሊያንሰራራ በማይችልበት ከፍተኛ ኪሳራ ላይ ሊወድቅ የሚችል መሆኑን በርካታ ተፎካካሪ አየር መንገዶች ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ ማቆማቸው አጋጣሚው በርካታ ዶላር ለመሥራት ያስችለኛል!” ብሎ የሚያስበው ደንቆሮው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማኔጅመንት ጨርሶ አልገባውም!!!

ከዚህ ቀደምም ምዕራብ አፍሪካ በኢቮላ ቫይረስ ችግር ላይ በወደቀ ጊዜ ሌሎቹ አየር መንገዶች በረራቸውን ሲያቋርጡ እሱ ግን ገቢን ብቻ በማሰብ አደጋን ባለማሰብ አደገኛ ሪስክ ወስዶ ወደ ምዕራብ አፍሪካ የሚያደርገውን በረራ ሳያቋርጥ ይሠራ እንደነበር ይታወሳል!!!

ይሄ በአቶ ተወልደ የሚመራው ደንቆሮ ማኔጅመንት የቻይናን በረራ ባለማቋረጡ ምክንያት ከሌሎች ሀገራት በሚጣልበት ማዕቀብ አየር መንገዱን ሊያንሠራራ በማይችልበት ኪሳራ ላይ ከመጣሉም በተጨማሪ በሌለን አቅም ቫይረሱን ወደ ሀገርቤት ይዞ በመምጣትና ሀገሪቱን በመበከል እሰበስበዋለሁ ብሎ ከሚያስበው ዶላር ገቢ ቢሊዮን ጊዜ እጥፍ በላይ ሀገሪቱንንና ሕዝቧን ለከፍተኛ ጉዳትና ኪሳራ ሊዳርጋት እንደሚችል ማሰብና መረዳት አልቻለም!!!

ግን ይሄንን ማሰብና መረዳት ስላልቻሉ ነው ብላቹህ ነው??? ሆን ብለው ሀገሪቱንና ሕዝቧን ለአደጋ ለመዳረግ አስበው ቢሆንስ??? እኛስ እንዲህ ያለ ያፈጠጠና ያገጠጠ አደጋ ጋርጠውብን እያየን ውሳኔው የእነሱ ነው!” ብለን ዝም ብለን ልናያቸው ይገባል ወይ???

ስለዚህ አተርፍ ባይ አጉዳይ!” አየር መንገዱ በድንቁርናም ይሁን በሸፍጥ ከዚህ መዓት ላይ ሳይጥለን በፊት ልናስቆመው ይገባልና ሳይረፍድ እንንቀሳቀስ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው