ይሄ ቅጥረኛ የጻፈውን መጽሐፍ በተመለከተ ከብአዴኑ ሚዲያ ዐሥራት ቴሌቪዥን ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ክፍል ሁለቱ ላይ ቃለመጠይቁ ሲቋጭ ስለ ሀገሪቱ ሲናገር ነው “መለያየት ከሆነ የተፈለገው መለያየት ያስፈልጋል፡፡ ስንለያይ ግን በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግረን መሆን አለበት!” ሲል የተናገረው!!!
ይሄ ባንዳ ይህችን ቃል ሲናገራት ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡ ምናልባት በሌላ ቦታም ተናግሮት ይሆናል፡፡ ቅርብ ጊዜ በዚሁ ሚዲያ ከኢኃኑ አቶ ይልቃል ጌትነትና ከአብኑ አቶ ጋሻው መርሻ ጋር ሆኖ ባደረጉት ውይይት ላይም ይሄንን ነገር ተናግሮት ነበር፡፡ ያኔ “ምን ለማለት ፈልጎ ነው?” ብየ አልፌው ነበር!!!
እንግዲህ ይታያቹህ ይሄ ሰውየ “ለኢትዮጵያ አንድነት እታገላለሁ!” የሚለው የመኢአድ (የመላው ኢትዮጵያ አንድንነት ድርጅት) ፕሬዘደንት ነኝ እያለ ነው “ኢትዮጵያን ተስማምተን እናፍርሳት!” እያለ ያለው!!!
ለነገሩ አገዛዙ ግልጽ ውንብድና ፈጽሞ አንድነትን እና መኢአድን ቀምቶ እንደ ቅንጅት ሁሉ የውሸት ፓርቲዎች አድርጎ ሲጠቀምባቸው መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነው ላይገርመን ይችላል፡፡ ይሁንና ግን ለሕዝባቸውና ለሀገራቸው የመጨረሻውን መሥዋዕትነት ከከፈሉት አርበኛ “ከእነ ፕሮ. ዐሥራት ጋር ሆኘ ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ በተለይም ለአማራ ብዙ ዋጋ ከፍያለሁ!” የሚል ሰው ይሄንን ነገር ሲያስብና ደጋግሞም በየስፍራው ሲናገረው ከመግረምም አልፎ በእጅጉ ግራ ማጋባቱ የሚቀር አይመስለኝም!!!
ይሄ የሰውየው አደገኛ የክህደት አነጋገርና የውሳኔ ሐሳብ (proposition) ባለፈው የተለያዩ መረጃዎችን ጠቅሸ “ማሙሸት ከአገዛዙ ጋር ተደራድሮ ሕዝቡንና ሀገሩን በመክዳት በቅጥረኝነት ለአገዛዙ እየሠራ ነው!” ያልኳቹህን ጉዳይ የሚያጠናክር ነው!!!
ማሙሸት ይሄንን ነገር በድንቁርና የተናገረው የሚመስለው የዋህ ሰው ይኖር ይሆናል፡፡ የጉዳዩን ክብደት በአንክሮ ለተመለከተውና የሰውየውን ኃላፊነት ለተገነዘበ ሰው ግን ማሙሸት የአገዛዙ ቅጥረኛ ስለሆነ እንጅ ከድንቁርና የተነሣ ይሄንን አደገኛ አነጋገር እንዳልተናገረ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል!!!
ለመሆኑ ይሄ ቅጥረኛ ርስታችንን፣ ሀገራችንን፣ መሬታችንን ለነማን አሳልፎ ሊሰጥ ፈልጎ ነው እንዲህ እያለ ያለው??? ለወራሪና ለስደተኛ አሳልፎ ሊሰጥልን ነው “ተስማምተን እንለያይ!” እያለ ያለው??? በኢትዮጵያ ህልውና ለመወሰንስ ማን ሥልጣን ሰጥቶት፣ ስንትስ ቢከፍሉት ነው “ተስማምተን እንለያይ!” እያለ የጥፋት ሐሳብ እያቀረበ ያለው??? እስኪ እባካቹህ ይሄንን ከሀዲ ቅጥረኛና ባንዳ ጠይቁልኝ???
ብቻ እጅግ በጣም ያሳዝናል!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው