በያሬድ ሃይለማሪያም

ቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ዩንቨርሲቲዎች መርዶ ነጋሪዎች ሆነዋል።

የሳይንሳዊ ምርምር ውጤት ዜናዎች ሳይሆን ከቅርብዩንቨርሲቲዎቹ እየተሰማ ያለው ለምርምርና ለትምህርት የሄዱ ተማሪዎች ከፎቅ እየተወረወሩ፣ በጩቤ እየተወጉ፣ በጅምላ እየተደበደቡ መገደላቸውን የሚገልጹ መርዶዎች ነው። ለትምህርት የወጤ ወጣቶች አስከሬናቸው ለቤተሰ እየተላከ ነው። ይህ እርምጃ ሆን ተብሎ ከአንድ ዩንቨርሲቲ ወደ ሌላ እየተዛመተ ተቋማቱ እንዲዘጉ እና የትምህርት ሂደቱም እንዲስተጓጎል በተቀናጀ መልኩ የሚሰራ ይመስላል።

ይህን ጉዳይ ማንም ከጀርባ ሆኖ ያስተባብረው ሁሉም ሰው በጋራ ሊያወግዘው የሚገባ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ለማህበረሰቡ ችግሮች በሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር መፍትሔ ያመጣሉ ተብሎ የሚጠበቁ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች መካከል ያለውን የሃሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶችን ለመፍታት አቅም እና መላ ማጣታቸው ተቋማቱ የደረሱበትን ዝቅጠት ያመላክታል።

ግዴታውንእየተወጣ አይመስልም። በአገሪቱ ውስጥ በስፋት የሚስተዋለው ሥርዓት አልበኝነት ከመንደሮች እና ከየመንገዱ አልፎ የትምህርት ተቋማት ውስጥም መንጸባረቁን በግልጽ እያየን ነው። በዚህ ሳምንት ብቻ ከድሬዳዋ እና ወልዲያ ዩንቨርሲቲዎች የተሰማው ዜና እጅግ የሚያሳዝን ነው። በሌሎች አንዳንድ የአገሪቱ ዩንቨርሲቲዎችም ተማሪዎች ለስጋት እና ለጥቃት መዳረጋቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። በቡሌ ሆራ ዩንቨርሲትም ውስጥ ተማሪዎች ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ከቀናቶች በፊት በመገናኛ ብዙሃን ሰምተናል።

የውይይት ባህል የራቃቸው ዩንቨርስቲዎች ተራጋጭ፣ እርስ በርሱ የሚገዳደል እና ተደባዳቢ ትውልድ ቢያፈሩ ምን ይገርማል? ውይይት ቁጣን ያበርዳል፤ አለመግባባትን ያጠባል፤ ግጭትን ይቀንሳል።

ለሞቱት ተማሪዎች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መስናናትን እመኛለሁ!