ፀረ አማራው የጥፋት ኃይል ብአዴን በለውጥ ስም አጃጅሎ እንዲደመሩ ያደረጋቸውን አሜሪካ የሚኖሩ ምሁራን ተብየ ዘገምተኞችን ከበፊቶቹ ጋር አቀናጅቶ አዲስ ሕዝባዊ የሆነ የዐሥራት ሚዲያ ቦርድ አቋቋምኩ!” ብሏል!!!

እንግዲህ ይታያቹህ በሀገር ውስጡ ስቱዲዮም ሆነ በዋሽንግተኑ ስቱዲዮ ካድሬ ጋዜጠኞቹ እንዳሉ ባሉበትና ጥቅሙን የሚያስጠብቅለት ሥራም በእነሱ በመሠራት እንዲቀጥል ባደረገበት ሁኔታ ነው እንግዲህ ዘገምተኛ ምሁራን ተብየዎችን ቦርዱ ውስጥ አካቶ ዐሥራት የአማራ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ ለአማራ ሕዝብ ነው!” እያለ ሊያጃጅል የሚሞክረው!!! ቀላል ይቀልዳል ባካቹህ!!!

እንደምታውቁት በፊት ኢሳት የአማራን ድምፅ እያፈነ ሲያስቸግረን በወገናችን ላይ የሚፈጸሙ የጥፋት ኃይሎች ግፍ ያለ አፈና እንደወረደ የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ ለማስቻልና የአማራን የህልውና ትቅል ለማቀጣጠል፣ ለማቀላጠፍ አማራ የራሱን ነጻ ሚዲያ ማቋቋም ከምንም ነገር በፊት ቅድሚያ ሰጥተን ልንረባረብበት የሚገባ መሆኑን አጥብቄ በማሳሰብ መጀመሪያ ላይ ይሄንን ሐሳብ በታላላቅ ድረገጾች ላይ ባቀረብኩት ጽሑፍ ወደ ሕዝብ ይዠ የቀረብኩት እኔ ነበርኩ!!!

ደጋግሜ ጮህኩ ጮህኩ ወደ ኋላ ላይ በአማራ ስም የተደራጁ ማኅበራት አጀንዳውን ያዙት፡፡ ለካ እነኝህ በአማራ ስም የተደራጁ ማኅበራት በውስጣቸው ካድሬ የተሰገሰገባቸው ኖረዋል ዐሥራት ሲመሠረት በካድሬ ቁጥጥር ስር ወድቆ ቁጭ አለ እነሱም የብአዴን አደረጉት!!!

እንደምታዩትም ዐሥራት ምድረ ካድሬ የተጠቀጠቀበት ሚዲያ በመሆኑ እንደታሰበው፣ እንደተጠበቀውና እንደሚፈለገው የአማራን ትግል የሚያቀጣጥል፣ አማራን ለትግል የሚያነሣሣ፣ ለ29 ዓመታት በአማራ ላይ የተፈጸሙ ሁሉን አቀፍ ግፎች፣ በደሎች፣ ጥፋቶች፣ አሻጥሮች፣ ሴራዎች በዶኩሜንተሪ ዘገባ ለሕዝብ የሚያሳውቅ፣ የሚያስገነዝብ፣ የሚያጋልጥ የትግል ሚዲያ ሊሆን ሳይችል ቀረ!!! አማራ ነጻ የሕዝብ ትግል ሚዲያ ያስፈለገው አማራ ያለበትን ይሄንን ክፍተት ወይም ጉድለት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሞላ ለማድረግ ነበርና!!!

ዐሥራት ሚዲያ ግን እንኳንና ይሄንን ክፍተት የሚሞላ የትግል ሚዲያ ሊሆን ይቅርና ሰኔ 15 ላይ እንደምታስታውሱት በእነ ጄኔራል አሳምነውና ቆራጥ ጓዶቹ ላይ የግፍ ግድያ በመፈጸም የአማራ ትግል ለማጥፋት ለተወሰደው የአገዛዙ የፀረ የአማራ ትግል ዘመቻ መሣሪያ ወይም መገልገያ በመሆን የቅጥረኛውን የአብን አመራሮችንና የብአዴን አመራሮች እያቀረበ ሕዝብ እየተወሰደ ከነበረው የፀረ አማራ ትግል ዘመቻ ጎን እንዲቆም መቀስቀሻ መሣሪያ ሆኖ ሊያገለግል ቻለ!!! ከዚያም በኋላ እየሠራና እያገለገለ ያለው ጠላትን ነው!!! የአማራ ትግል ሚዲያ መሆኑ ቀርቶ የጠላት ሚዲያ ሆኖ ቁጭ አለ ማለት ነው!!! እንዲህ ሊሆን የቻለውም ዐሥራት በፀረ አማራው ብአዴን ቁጥጥር ስር ያለ በመሆኑ ነው!!!

ጽድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነኑኝ!” እንዲሉ የትግል ሚዲያ መሆኑ ቀርቶ ብአዴን እንዲያው ሕዝብን ለመደለል ያህል እንኳ እንደ መደበኛ ሚዲያ ደረጃቸውን የጠበቁ ሥራዎችን ብቃት ባላቸው ጋዜጠኞች የሚሠራበት ሚዲያ እንኳ ሊያደርገው ሳይፈልግ ቀረና ዐሥራት ስም ብቻ ይዞ ሊቀር ቻለ!!!

ከዚህ ቀደም እንደነገርኳቹህ ከሁሉ ነገር የሚቆጨኝና የሚያንገበግበኝ ብአዴን የእኛ የነበሩትንና የወሰዳቸውን ቅጥረኞቹን እነ ኮሎኔል ደመቀን፣ እነ ማሙሸት አማረን፣ እነ ጌታቸው ሽፈራውን ወዘተረፈ. ከፊት አሰልፎ ሕዝብን በማታለል ዐሥራት ሚዲያ እኛ ባዋጣነው በገዛ ገንዘባችን ማቋቋሙ አይደለም፡፡ የጀግናችንን የፕሮ. ዐሥራትን ስም መጠቀሚያው ማድረጉ ብቻ ነው የሚያንገበግበኝ!!!

በዚህ አጋጣሚ ፀረ አማራውን ብአዴንን አምርረን እንጠላለን የሕዝብ ወገን ነን!” የምትሉ ምሁራን ዐሥራት የብአዴን መሆኑን ልባቹህ እያወቀ ዐሥራት የብአዴን መሆኑ በግልጽ እስካልታወቀ ድረስ ብቀርብ ምን ችግር አለው?” እያላቹህ ዐሥራት ላይ እንግዳ እየሆናቹህ የምትቀርቡ በተለይም በአማራ ተቆርቋሪነታቹህ የምትታወቁት ዐሥራት ላይ ስትቀርቡ ብአዴን እየተጠቀመባቹህ መሆኑን ዕወቁ፡፡ እንዴት ብትሉ የሚመለከታቹህ ሕዝብ ዐሥራት የብአዴን አለመሆኑን አረጋግጣቹህ የቀረባቹህ ስለሚመስለው ዐሥራት የአማራ ሕዝብ ነጻ ሚዲያ ነው!” ብላቹህ ማረጋገጫ እየሰጣቹህት እንደሆነ ነውና የሚቆጥረው ብአዴን በዚህ መልኩ እየተጠቀመባቹህ ስለሆነ ይሄንን ተገንዝባቹህ እባካቹህ ዐሥራት ላይ በመቅረብ መጠቀሚያ ከመሆን ታቀቡ!!!

አንዳንዱማ ጭራሽ ሕዝብ ዐሥራት ሚዲያ የብአዴን መሆኑን በቀላሉ የሚረዳበትን ስንት ነገር እያየና እየታዘበ ዐሥራት ነጻ የአማራ ሚዲያ ነው!” በማለት ሕዝብን ለማሳሳት የሚጥርም አለ፡፡ ለምሳሌ የሞረሽ ወገኔ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋኸኝ ትናንትና እንግዳ ሆኖ ቀርቦ ዐሥራት ነጻ የአማራ ሕዝብ ሚዲያ እንደሆነ ሲሰብክ ነበር፡፡ እንግዲህ ይሄ ሰውየ ብአዴን በለውጥ ስም አጃጅሎ እንዲደመሩለት ካደረጋቸው ዘገምተኛ ምሁራን አንዱ ነው ማለት ነው፡፡ ማወቃችን ጥሩ ነው!!!

የሚገርመው ይሄ ሰውየ በዚህ በብአዴን ሚዲያ ቀርቦና ሕዝብ ዐሥራት ሚዲያን የብአዴን ነው!” ብሎ እንዳይጠላ ዐሥራት የአማራ ነው!” እያለ እየሰበከ እዚያው ላይ ደግሞ ብአዴንን ለማውገዝ መሞከሩ ነው፡፡ እሱ ብቻ ሳይሆን ካድሬ የዲሲው ስቱዲዮ የዐሥራት ጋዜጠኞችም ይችን ብአዴንን በማውገዝ ፀረ ብአዴን የመምሰልን ፈሊጥ ተያይዘዋታል!!! ሕዝብ ጥሏቹህ የትናየት እንደሔደ ብታውቁ በዚህ ልታታልሉት ባልሞከራቹህ ነበረ!!! ምድረ ቅጥረኛ ሁላ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው