እስረኞች ካልተፈቱ፣ ሆን ተብሎ በአገዛዙ በአማራ ላይ በየስፍራው የሚፈጸሙ ግፍና ግድያ ካልቆመ…..!” በማለት ከነገወዲያ የካቲት 22, 2012.. እንደሚያደርጉት ሲናገሩት የቆዩትን አድማና ሰልፍ ሰርዘነዋል!” ብለዋል!!!

እነኝህን ቅጥረኞች አማራ በአገዛዙና በአጋሮቹ የጥፋት ኃይሎች በየስፍራው ሆን ተብሎ ታስቦና ታቅዶ በሚፈጸምበት ግፍ ፍዳና መከራ ላይ ያለና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ መሆኑ ፈጽሞ ዓይታያቸውም!!!

እነኝህ የፀረ አማራው ብአዴን ካድሬዎች ጥርቅም አማራን ለግል ጥቅማቸው መጠቀሚያ ያደርጉታል ወይም ይጠቀሙበታል እንጅ እራሳቸውን ለአማራ ጥቅም፣ መብት፣ ህልውና፣ ነጻነት፣ ደኅንነት ወዘተረፈ አሳልፈው ሰጥተው ለአማራ ዋጋ ለመክፈል ቅንጣት ታክል የማይፈልጉ በመሆናቸው ነው ታሰሩብን!” የሚሏቸው ጓዶቻቸው ጉዳይ እንታገልለታለን!” ከሚሉት መጠነ ሰፊ አሳር፣ ሰቆቃ፣ ፍዳና ግፍ በሰፊው እየተፈጸመበት ካለው አሳረኛው አማራ ጉዳይ በልጦባቸው ታሰሩብን!” የሚሏቸው ጓዶቻቸው የውሸት ለፖለቲካ አሻጥር እስርቤት ገብተው ከነበሩበት እንዲወጡ ስለተደረጉ አድማውን ትተነዋል!” የሚሉት!!!

ሌላው የገረመኝ ነገር እነኝህ ብናኞች አገዛዙ ከየካቲት 22 ጀምሮ እናደርገዋለን!” ያሉትን አድማና ሰልፍ ፈርቶ ጓዶቻቸውን የፈታላቸው የሚያስመስሉት ነገር ነው፡፡ ይሉሽን ባወቅሽ ገበያ ባልወጣሽ!” አሉ፡፡ አማራ ማንነታቸውን አብጠርጥሮ እንዳወቃቸው አላወቁም መሰለኝ፡፡ ታየኝ እኮ አማራ የእነኝህ አስመሳይ ቅጥረኞች የአድማ ተባባሪ ሲሆን፡፡ ቆይ እንጅ እነ ባንዶ አገዛዙ አድማቹህን ፈርቶ የሚፈታ ከሆነ ከዚህ ቀደም ደጋግማቹህ ስታስጠነቅቁ ምነው ታዲያ ያኔ አይፈታላቹህም ነበረ ታዲያ???

ወገን ሆይ! እውነቱ ግን ከዚህ ቀደም አብኖች በአስቸኳይ ካልተፈቱ እንዲህ እንዲህ እናደርጋለን!” እያሉ ባሉት መሠረት ያላደረጉትን ነገር እየተናገሩ ሲያስጠነቅቁ የነበሩት ለምን ዝም አሉ?” እንዳይባሉ ሲሆን አሁን በመጨረሻ ደግሞ የካቲት 22, 2012.. “እናደርጋለን!” ብለውት የነበረው አድማና ሰልፍ ሲቃረብ አገዛዙ ታሰሩብን!” ያሏቸውን የፈታበት ምክንያት ደግሞ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ በአስቸኳይ ካልተፈቱ እንዲህ እንዲህ እናደርጋለን!” እያሉ በተናገሩት መሠረት ያላደረጉትን ነገር እየተናገሩ ሲያስጠነቅቁ አገዛዙ ሳይፈታቸው ቀርቶ አማራ አፍሮባቸው ስለነበረና ይሄው ቁጥር ሁለት ብአዴን የሆነው የአገዛዙ አስመሳይ ፓርቲ አብን በአማራ ዘንድ ተአማኒነት፣ ክብርና ሞገስ ስለተለየው እንደገና ተአማኒነት፣ ክብርና ሞገስ እንዲያገኝ ለማድረግ ሲባል የካቲት 22 የሚል የአድማና ሰልፍ ቀጠሮ ሲናገር እንዲሰነብት ተደረገና ቀኑ ሲቃረብ አገዛዙ አድማቸውን ፈርቶ የፈታላቸው ለማስመሰል ለፖለቲካ አሻጥር ሆን ተብሎ እስርቤት እንዲቆዩ ተደርገው የነበሩት ካድሬዎቹ እነ ክርስቲያን ከእስርቤት እንዲወጡ ተደረገ!!! ዘገምተኛው መንጋ ግን አሻጥሩ አልገባውም!!!

የውሸት የታሰሩት ካድሬዎቹ ከእስር ቤት ካስወጧቸው በኋላ ደግሞ አማራ ለፖለቲካ አሻጥር የውሸት ከታሰሩት ከነ ክርስቲያን መታሰር ልጆቹን ተጠልፈው ተወስደው ደብዛቸውን ከማጥፋት ጀምሮ መጠነ ሰፊ የከፋ፣ የከበደ፣ የመረረ ስንት ፈተና፣ መከራ፣ ፍዳና ግፍ በየስፍራው እየተፈጸመበት ባለበት በዚህ ሰዓት የውሸት የታሰሩት ካድሬዎቹ እነ ክርስቲያን በመፈታታቸው የአማራ ችግር የተፈታ ይመስል እናደርጋለን!” ብለውት የነበረውን የየካቲት 22ቱን አድማና ሰልፍ ሰርዘነዋል!” ብለው መግለጫ አወጡና አረፉት!!!

እንግዲህ ይሄንን ከተመሠረተ ጀምሮ ለአማራ መከራ ለአንድ ጊዜ እንኳ ደርሶ የማያውቅ የካድሬ ቡድን፣ የጥፋት ኃይሎች የአማራን የህልውና ትግል ለማጥፋት ሰኔ 15 እና ከዚያ በኋላ በአማራ የህልውና ትግል ላይ ሲዘምቱ ከእነኝህ ከፀረ አማራ የጥፋት ኃይል ጎን ቆሞ አማራንና የአማራን ብሔርተኝነት የህልውና ትግል ያስበላውን የአገዛዙን ቅጥረኛ፣ አሻጥረኛ፣ ባንዳ ብአዴን ቁ.2 ቡድን ነው እንግዲህ ለአማራ ሕዝብ ጥቅም፣ መብት፣ ህልውና፣ ነጻነት፣ ደኅንነት ወዘተረፈ. እራሱን ለመሥዋዕትነት አሳልፎ ሰጥቶ የሚታገል ድርጅት ነው!” የምትሉት!!!

አየ እነ ዘገምተኞ!!! ስታሳዝኑ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው