አጋጥሟቹህ እንደሆነ አላውቅም የወያኔ/ኢሕአዴግ ቅጥረኞች በሶሻል ሚዲያው የሸዋ አማራ መስለውና አንዳንድ የሸዋ አማሮችንም አታለው የአማራን ትግል መምራት ያለበት ሸዋ ነው!” በሚል ዘመቻ ላይ አሠማርቷቸዋል!!!

የገረመኝ ፀረ አማራ የጥፋት ኃይሎቹ የሚሰማቸውና ተቀባይ አግኝተው አማራ በዚህም ጉዳይ ላይ መራኮት መጀመሩ ነው፡፡ አይገርምም አያሳዝንም??? አየ እኛ!!!

አሁን ምኑ ተያዘና ነው እኛ ነን መምራት ያለብን አይደለም እኛ ነን!” ለመባባል የምንበቃው??? መምራት የፈለገ ካለ ወደ ውጊያው ዐውድ ገብቶ በጀግንነት በመፋለም መሪነቱን መያዝ የሚችልበት ጊዜ ላይ ነው እንጅ ያለነው አርፎ ተቀምጦ የማይጨበጥ ነገር እየቀባጠሩ መሪና የአማራ ራስ እኛ ነን!” በማለት መሪ የሚኮንበት ጊዜ ላይ ነን እንዴ ያለነው???

አዎ በርግጥ አማራ ያጣው መሪ ነው መሪ ይፈልጋል፡፡ አውርቶ አደር መሪ ሳይሆን መሬት ላይ ወርዶ ሠርቶና ታግሎ አደር መሪ ነው ያጣውና የሚያስፈልገው፡፡ በዚህ ዘመን መሪን ትግል ይፈጥረዋል እንጅ ምኞትና ፍላጎት አይፈጥረውም፡፡ በመሆኑም ማንም መሪ ለመሆን የሚሻ ቢኖር እራሱን የአማራ መራር ትግል የሚፈልገውን ወኔና ቁርጠኝነት አስታጥቆና ለመሥዋዕትነት አዘጋጅቶ ወደ ትግሉ ይግባ፡፡ መሪነቱን እዚያው ያገኘዋል፡፡ በወሬ ወይም ቀሚስ እስኪላክለት ድረስ አልነሣ አልቀሰቀስ ብሎ ተኝቶ ከርሞ አሁን መጨረሻ ላይ የአማራ ራስ እኛ ነንና የአማራን ትግል መምራት ያለብን እኛ ነን!” በማለት አይደለም!!!

ትናንትና በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲህ እያሉ የጥፋት ኃይሎችን ተልእኮ ተቀብለው ከሚያራግቡት ቅጥረኞች አንዱ ከሆነው ጋር ተቀጣቅጠን ነበር፡፡ ግንዛቤ ታገኙበታላቹህ ብየ ስለገመትኩ የተመላለስናቸውን ቃላቶች ላስነብባቹህ ወደድኩ፡፡ ምልልሳችን ዱላ ቀረሽ ስለነበር ስድብ ስድቡን ከመሀል አውጥቸ ፍሬ ፍሬ ነገሩን ብቻ አስተካክየ ላስነብባቹህ፦

ሰውየው ከታች የምታዩዋቸውን ፎቶዎች ሜሴንጀር ላይ ሲያዘዋውር ነበር ኧረ ተዉ ኧረ ተዉ ይሄን አማራን የመነጣጠል የመከፋፈል ነገር ተዉ???” ስል የጠየኩት፡፡ እሱም የሸዋ ዘውድ ነው ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ሸዋ በዘውዳዊ ሥርዓት እና በአንበሳው አርማ ይታወቃል!” አለኝ፡፡ ጎንደርስ በዚህ አይታወቅም???” ብየ ብጠይቀው፡፡ አይታወቅም እልኩ? ወጣኝ? ጠማማ! ሸዋ ሲባል የበታችነት ስሜት ያሰቃይሀል እንዴ እንተም እንደ ሰፈርህ ልጆች?” አለኝ፡፡

እኔም አንተ እኮነህ የሸዋ መታወቂያ ነው!’ ያልከው??? ካልክ እንዲያውም ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ!’ የሚለውን ቃል የጀመሩት የዐፄ ፋሲል የልጅ ልጅ ዐፄ አዲያም ሰገድ ኢያሱ መሆናቸው ነው በታሪክ የሚነገረው!” አልኩት፡፡

እሱም አፄ ፋሲል ሸዋ ናቸው መንዝ የተወለዱ የጎንደር ዘውድ ግራኝ አህመድን ሸሸቶ ከሸዋ የሔደ ነው፡፡ ምንም የማላቅ አታስመስለኝ ሲጀመር ጎንደር የሚኖረው አማራም ከሸዋ የሔደ ነው!” አለኝ፡፡

እኔም ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ሸዋን ለቆ ጎንደር የገባው ግራኝ አሕመድን ሸሽቶ ሳይሆን ግራኝን ተከትለው ወደ ሀገራችን በገቡትና የግራኝ የ15 ዓመት ወረራ ከተቀለበሰ በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በስደት እንዳሉ በማረፋቸው በእሳቸው የተተካው ልጃቸው ዐፄ ገላውዴዎስ ወደ አባቱ መናገሻ ሸዋ ሲመለስ ሀገሩን ወረውት በተገኙት በኦሮሞዎቹ ተደጋጋሚ ጥቃት በመሰላቸቱ ነው፡፡ ዐፄ ገላውዴዎስ 19 ዓመት፣ ዐፄ ሚናስ 4 ዓመት እዚያው ሸዋ ነግሠው በኦሮሞዎቹ እየተወጉ ከቆዩ በኋላ በዐፄ ሠርፀድንግል ነው ሸዋን ለቆ ጎንደር እንፍራዝ የገባው እሽ??? ታሪክ ካወክ አማራ ከሸዋ በፊትስ የት ነው የነበረው???” ስል ጠየኩት፡፡

እሱም ታሪካዊ ግዛቴ በወርቃማው ታሪኩ መወደስ አለበት ይህ ላንተ አማራን ለመከፋፈል የመሰለህ ጎንደሬ ስለሆንክና የበታችነት ስሜት ስላሰቃየህ ነው፡፡ የሚገርምህ የጎንደር ዙፋን ጠላትን ሸሽቶ ከሸዋ የሔደ ነው ግማሹም አፄ ቲዎድሮስ ከአፄ ምኒልክን ሲወስዱ ብዙ የሸዋ ዙፋኖችን ወደ ጎንደር ወስደዋል!” አለኝ፡፡

እኔም አማራ አንድ ነው፡፡ የሸዋ፣ የጎንደር፣ የጎጃም፣ የወሎ የሚባል ነገር የለውም!!!” አልኩት፡፡

እሱም አንተ ጎንደሬ ሸዋ የሚለውን የቦታ ስማችን አክብረው፡፡ ንግሥና ሲጀመር የሸዋ ነው፡፡ ሸዋ ባትወለድም ይህን ዋጠው እሺ? ! በኦሪት ዘመን በርግጥ እነ ነብዩ ደሸት የጎጃም ዐማራ ነገሥታት እንደነበሩ የመሪ ራስ አማን የጥንቷ ኢትዮጵያ የተሰኘው መጽሐፍ ይገልፃል፡፡ በነገራችን ላይ የጎዣሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት እና ከዐፄ ሚናስ ጀምሮ እስከ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ድረስ የነገሡት በሙሉ የሸዋ ነገሥታቶች ናቸው፡፡ እነዚህ በሙሉ የዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ የሆነው ያቤቶ ያቆብ ልጅን ሐረግ ተከትለው የነገሡ ናቸው፡፡ እንደው ከጎንደር ይልቅ ጎጃሜዎች ቢያነሡ ምክንያት አላቸው፡፡ ለምን የዐፄ ልብነ ድንግል ባለቤት እቴጌ ሰብለ ወንጌል የደብረማርቆስ ጎጃም ዐማራ ተወላጅ ናቸው፡፡ አሁንም ይሔድና የዐፄ ፋሲል አባት ዐፄ ሱስንዮስ እና ንግሥት ሐመልማላዊት የጎጃም ዐማራ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ዐፄ ፋሲል የአባትቸው እናት አያታቸው የጎጃም ዐማራ ናቸው፡፡ ወደ ንግሥናው ስመጣ የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖትም ሆኑ ከዐፄ ሚናስ ጀምሮ እስከ ዳግማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ ጎንደር ላይ የነገሡት በጎንደርና የጎጃም ዐማራ ሐረጋቸው ሳይሆን በሸዋ ዐማራ ነገሥታት የዘር ሐረጋቸው ነው፡፡ ሌላውን ትታችሁ የትግራዩ አፄ ዮሐንስ የነገሰው በትግሬ እነቱ ሳይሆን ትንሽም ብትሆን ከሸዋ የነገስታት ወገን ያለውን የዘር ሐረጉን አስቆጥሮ ነው፡፡ እንዴት ለሚለው አፄ ዮሐንስ የዘር ሐረጋቸው ሲቆጠር ከአፄ ፋሲል ሴት ልጅ መና እስራኤል ይመዘዛል፡፡ እሳቸው እራሱ የነገሱት ያን ሐረግ አስቆጥረው ነው፡፡ በርግጥ በዘር ትግሬ ናቸው፡፡ ማለትም የአንድን ሰው ዘሩን የሚወስነው 75 % የሚሸፍነው ትውልዱ ነውና ነው፡፡ በንግስና ግን ያቺን ሽርፍራፊ የሸዋ ነገስታት ሐረጋቸውን አስቆጥረው ስለነገሱ በንግስና ሸዋ ናቸው፡፡ ትግሬ ሲጀመር ንግስና የለውም፡፡ ትግሬዎች የአክሱም የሸዋ ዐማራ ነገስታት የቤት አገልጋይ ነበሩ!” አለኝ ኦሮሞ በወረራ የመጣ ሳይሆን ከጎጃም የወጣ እዚሁ የተፈጠረ ነው!” የሚለውን የኦሮሞ ጽንፈኞችን ቅጥረኛንና ሙሉ ለሙሉ ከታሪክ እውነታ ጋር የሚጻረረውን የመሪ ራስ አማን በላይን ልብወለድ ድርሰት ዋቢ አድርጎ!!!

እኔም እንደኔ ጠበህ ተስተካካይ መልስ ስጥ ካልከኝማ ከዚህ ከምትለው ሁሉ በፊት የዚህ ሁሉ ታሪክ ስር የሆነው ኖኅና መቃብሩ ያለው ደግሞ ለመታሰቢያው ፋሲል ግንብ የተገነባበት ቦታ ላይ ነው እሽ??? ስለ ኖኅና መቃብሩ አንሥቸ የምነግርህ የአማራ ንግሥና መሠረቱ እሱ እንደሆነ እንድትረዳ ነው፡፡ ክብረ ነገሥት ቀዳማዊ የኢትዮጵያ የነገሥታት ታሪክ የሚጀመረው ከኖኅ መሆኑን ይናገራል፡፡ ያ ማለት ደግሞ ልክ ዛሬ ለመታሰቢያው ከኖኅ መቃብር ላይ የፋሲል ግንብ ከተገነባበት ቦታ ላይ ነው ኖኅና ልጆቹ ነግሠው ይኖሩ የነበሩት፡፡ ከጥፋት ውኃ በኋላ ማለቴ ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ነገሥታት መሠረቱ ጎንደር እንጅ አክሱምም ሸዋም አይደለም፡፡ አክሱምና ሸዋ ከጎንደር በኋላ ነው የአማራ ነገሥታት መናገሻ የሆኑት፡፡ የሰሎሞናዊ ሥርዎ መንግሥት የጀመረው ከንግሥተ ሳባ ወይም ማክዳ እና ከሰሎሞን ከተወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ ነው እንጅ ከዐፄ ይኩኖ አምላክ አይደለም እሽ???” አልኩት፡፡

እሱም ስለ ኖኅ ከሔድክ የሰው ልጅ መገኛ ከአዳም ነው እኔና አንተ ያወራነው ስለ ሰሎሞናዊ ዘውድ አገዛዝ ነው!” አለኝ፡፡

እኔም እኔ ደግሞ የማወራህ ከቀዳማዊ ምኒልክ (ከሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ጅማሮ) በፊት ስለነበረው ወይም የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረበትን ነው!!! ክብረነገሥት ቀዳማዊን እኮ ጠቀስኩልህ ምን የማይገባህ ልባውልቅ ነህ በሞቴ???” አልኩት፡፡

እሱም አማራ በተፈጥሯዊ ማንነቱ ማለትም በደሙ በአጥንቱ ከተቆጠረ ፍጹም አንድ ነው። ነገር ግን በፖለቲካና በታሪክ እይታ አካባቢዎቹ የየራሳቸው ታሪክ እና ፖለቲካዊ እሥተዳደር ልዩነት አላቸው፡፡ ይህን ማክበር ያስፈልጋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት የአማራ አንድነት በቅንነት እና በምኞት አይፈጠርም፡፡ መጀመሪያ በታሪክም ሆነ በአሥተዳደር ምክንያቶች የተፈጠሩትን ልዩነቶቻችንን ማክበር እና ዋጋ መስጠት ያስፈልጋል፡፡ ለምሳሌ አፄ ፋሲል የሸዋ ሰው ናቸው ጎንደርን ሲመሰርቱ እሳቸው ብቻቸውን አይደለም ወታደሮቻቸውን ቤተሰቤቶቻቸውን ከሸዋ ይዘው ሔደው ነው ጎንደርን የሠሯት ቤዚካሊ ጎንደር የሸዋ ሰው ጠፍጥፎ የሠራት ከተማ ነች፡፡ እዚህ ላይ ፋሲል ለምን ወደ ጎንደር ሔደ የሚለው ታሪክ እራሱን የቻለ ታሪክ ነው ከጎንደር በፊት ጣና ላይ እንደነበሩም አንዳንድ ማስረጃዎች አሉ፡፡ ወደ ጎንደርም ሲሔዱ የጎጃምም ሰው ተከትሏቸዋል የሚሉም አሉ፡፡ ዋናው ቁም ነገር የሸዋ ታሪክ እራሱን ችሎ መቆም የሚችል መሆኑን ማመን እና ማሳመን መቻሉ ላይ ነው!” አለኝ ባልጠራ የታሪክ ግንዛቤው፡፡

እኔም ስንቴ ደጋግሜ ብነግርህ ነው ግን የሚገባህ ለመሆኑ??? እላይህ ላይ ትምህርት ቤት ቢሠራብህም የሚገባህ አይመስለኝ!” አልኩት፡፡

እሱም ምንም የነገርከኝ የታሪክ ማስረጃ የለም!” አለኝ፡፡ እኔም እንግዲህ የነገሥታቱን ታሪክ በተመለከተ ብቸኛው ማስረጃ ክብረ ነገሥት ነው፡፡ ከክብረ ነገሥት በላይ ሌላ ምን ማስረጃ ልጥቀስልህ??? አንተ በምትለው ልሒድልህ ብልም እኮ የሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት ነጋሢ ዘር ያለው ጎንደር እንጅ ሸዋ አይደለም እኮ፡፡ በኦሮሞዎቹ ተገፍቶ ከሸዋ ወደጎንደር ነቅሎ ሔዷልና!” አልኩት፡፡ እሱም የቦታ ስሙን ቀየረ እንጂ ከሸዋ የሔደው የዘር ሐረግ ነው ጎንደር የነገሠው!” አለኝ፡፡ እኔም አዎ ከሸዋ ነቅሎ ጎንደር ከገባ በኋላም የነጋሢው ዘር ሸዋ ውስጥ የለም፡፡ ልቅምቃሚው ወይም የሩቅ ቁጥርጥሩ ካልሆነ በስተቀር፡፡ እሱም ቢሆን ከጋላ ጋር ተዳቅሎ ጠፍቷል!” አልኩት፡፡ እሄኔ ንዴቱን መቋቋም አልቻለም!!!

የቻለውን ያህል ከሰደበኝ በኋላ የበታችነት ስሜት ቢያሰቃይህም ቻለው የንጉሡ ቤተሰቦች የሸዋ ዘር የተመዘዙ እየተመረጡ ነው የነገሡት፡፡ ሸዋ ላንተም አንድ አካልህ ነው አይዞህ ቻለው፡፡ ደሞኮ የመጽሀፍ ስም ከመጥቀስ ውጭ አንድ እውነት አልያዝክም!” አለኝ፡፡

እኔም እንዲያው ምኑ መሐይሙ ነህ ግን??? ቅድም ማስረጃ አልጠቀስክም አልከኝ፡፡ ከክብረነገሥት በላይ ምን ልጥቀስልህ?’ ስልህ አሁን ደግሞ የመጽሐፍ ስም ከመጥቀስ ውጭ አንድ እውነት አልያዝክም!’ አልክ፡፡ ክብረ ነገሥት የሚናገረው እውነት አይደለም ወይ???” አልኩት፡፡

እሱም ስለኖኅ ሁለት ዓይነት የታሪክ አረዳድ አለ፡፡ እርሱም ምንድነው እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆች ኃጢአታቸው ስለበዛ የሰውን ልጅ ሊያጠፋው አርባ ቀንና ሌሊት ዶፍ ዝናብ አዝንቦ ምድር ተጥለቅልቃ ፍጥረት ሁላ ሲሰጥም ነገር ግን እግዜር የሰውን ልጅ ፈጽሞ ሊያጠፋው ስላልፈለገ በዘመኑ ለፈጣሪ ታዛዥ የሆኑትን ኖኅና ቤተሰቡን እንዲሁም ከየፍጥረቱ ለዘር እንዲተርፍ ይዞ ወደ መርከቢቱ እንዲገባ ስላደረገው በመጨረሻ መርከቧ ተንሳፋ አራራት ተራራ ላይ አረፈች ይላል፡፡ አራራት የሚል ተራራ አርመን አገርና ኢትዮጵያ ጣና ደሴት ላይ አለ፡፡ ስለሆነም ኖኅና ቤተሰቡ ጣና ላይ ኖረው በመጨረሻ ኖኅ የአሁኗ ጎንደር ከተማ የፋሲል ቤተመንግሥት ያለበት ስፍራ ተቀበረ፡፡ ሚስቱ አይከል ደግሞ ጭልጋ ላይ ተቀበረች ስፍራው እስካሁን አይከል በሚል ይጠራል፡፡ ኖኅ የተቀበረበት ቦታ ላይ ጸበል ፈልቆ ሰዎችን ከደዌ ይፈውስ እንደነበር ተጽፏል፡፡ በመጨረሻ በ17ኛው ክፍለ ዘመን ከሸዋ ነገሥታት ሐረግ የሚመዘዘው አፄ ፋሲል የጎንደርን ከተማ ከመሠረተ በኃላ የእግዚአብሔር ራዕይ ታይቶት ለኖኅ መታሰቢያ የጎንደርን ግንብ አሁን የፋሲል ግንብ ተብሎ የሚጠራውን በኖኅ መርከብ ቅርጽ አሠራለት ይላል ታሪኩ፡፡ አሁንም መንፈሳዊ ቁርኝቱን ስናይ የሸዋ ነገሥታት ለኖኅ ቀረቤታ አላቸው፡፡ አባታቸውን ኖኅን ለማስታወስ በኋለኛው ዘመን የሸዋ ነገሥታት ዐፄ ፋሲል ጎንደር ላይ ቤተመንግሥት አሠሩለት ፡፡ ለኖኅ በመንፈስ የሚቀርቡት የሸዋ ነገሥታት ናቸው፡፡ ወደ ቁም ነገሩ ስመለስ ንግሥናን በተመለከተ ያወራነው የሰለሞናዊ ስርዎ መንግሥትን በሚመለከት ነው፡፡ እንግዲህ ነገርን ከስሩ ውኃን ከጥሩ እንዲሉ ታሪኩን ከመነሻው ካየን የሰው ልጅ ታሪክ የሚጀምረው ከኖኅ ሳይሆን ከአዳም ነው፡፡ ስለዚህ አዳም ሲኖርበት የነበረ ሕዝብ የታሪክ ሁሉ ምንጭና ቀደምት ነው፡፡ ችግሩ የሸዋ ታሪክ ሚሥጥር ሆኖ የኖረ ስለሆነ ለመረዳት ያስቸግራል፡፡ ለአብነት ብናይ የብርሃን ጽዋው መገኛ ሸዋ መንዝ ላይ ነው፡፡ ከዚህ ሁሉ ዓለም የሸዋ ሕዝብና ምድር የብርሃን ጽዋው መቀመጫነት አምላክ የመረጠው ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሸዋ ሚሥጢራዊ የታሪክ ቋት ነው:: በዚህ ዓለም ላይ የሸዋን ምድርና ሕዝብ የሚስተካከል እንደሌለ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ እመጓ በተሰኘ መጽሐፋ ገጽ 176 አንቺ እመጓ ቆላ ሆይ ብሎ ያሰፈረውን አንብቦ ያን ሊሞግተን የሚችል ካለ ማስረጃ ይዞ ይሞግተን!” አለኝ፡፡

እኔም እስኪ ክብረ ነገሥት ቀዳማዊን ማግኘት ባትችል እንኳ የኅሩይ ወልደ ሥላሴን ዋዜማ መጽሐፍ አንብብ??? አንተ እያወራህ ያለኸው ስለ ሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት መሆኑን እኮ አውቄያለሁ፡፡ እኔ የማወራልህ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት የጀመረበትን ከሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት በፊት ስለነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ እንደሆነ በተደጋጋሚ ነገርኩህ፡፡ ይሄንን ከላይ ያስቀመጥከውን መልስ የጻፈልህ ሰውየም ቢሆን ከሰሎሞናዊው ሥርዎ መንግሥት በፊት ስለነበረው ከኖኅ ስለሚጀመረው የኢትዮጵያ መንግሥት ምንም የተናገረው ነገር የለም፡፡ አድበስብሶት ነው ያለፈው፡፡ ይመስለኛል ስለ ታሪኩም ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ለማንኛውም የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴን ዋዜማ መጽሐፍ ስታነብ የኢትዮጵያ ነገሥታት ታሪክ ከኖህና ልጆቹ እንደሚጀምር ይነግርሀል እሽ??? ሰሎሞናዊውም ቢሆን ወደ ሸዋ የፈለሰው ዮዲት ጉዲት አማራን ከአክሱም ካጠፋችው በኋላ ነው እሽ???” አልኩት፡፡

እሱም አክሱም የነገሠው የሸዋ ነግሥታት ዘር ነው!” አለኝ፡፡🤣እኔም ወቸ ጉድ እንዲያው የታሪክ ቅደም ተከተልንና የክፍለ ዘመን ልዩነትንም ጨልሶ አታውቅም ማለት ነው???” አልኩት፡፡

ከዚያ እሱም ከትግሬ ጋር መዋልኮ የበታችነት ስሜት ይጋባል፡፡ ያሰቃያል ቻለው ሸዋ ራሱን የቻለ የዘር ሐረጉ እየተመዘዘ የነገሠ ሕዝብ ነው፡፡ ሸዋ የቦታ ስም እንጂ ዘሮችህ ከሸዋ ሒደው ጎንደር የወለዱህ ዲቃላ ነህ፡፡ አየ ትግሬ! የሥራህን ይስጥህ፡፡ ጎንደሬን ሁሉ በበታችነን ስሜት በሽታ አስለክፎታል!” አለኝ፡፡ እኔም አየ አንተ ወያኔ ጭራሽ ጎንደርን የትግሬ ልታደርጋትና የጎንደርን አማራ የትግሬ ዲቃላ ልታደርገው አማረህ አህዮ? ‘ሸዋ ውስጥ የነጋሢ ዘር የለም ነቅሎ ጎንደር ገብቷል የነጋሢ ዘር አለኝ!’ የሚለው የሩቅ ቁጥርጥሩም ከጋላ ጋር ተዳቅሎ ጠፍቷል!’ ስላልኩ ተናደሽ ነው አይደል የጎንደርን ንጥር አማራ ከትግሬ ጋር የተዳቀለ የምታስመስይው??? አይምሰልሽ እሽ ከማንም ጋር ያልተዳቀለ ንጹሕ አማራ አለ ከተባለ ያለው ጎንደር ነው!!!” አልኩት፡፡ ከዚህ በኋላ ያለው ተራ መዘላለፍ ስለሆነ ትቸዋለሁ!!!

እናም እንግዲህ አገዛዙ አህያውን ፀረ አማራ የጥፋት ኃይል ብአዴንንና ካድሬዎቹን ተጠቅሞ በሰኔ 15ቱ የግፍ ግድያው አማራን ለመከፋፈል ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየው አገዛዙ አሁን ደግሞ ይሄንን ይዞላቹህ መጥቷልና ተጠንቀቅ አማራ!” ለማለት ነው!!!

የጥፋት ኃይሎች ቀጥሎ ደግሞ ወሎዎችን የለም የአማራ መሠረት እኛ ነንና እኛ ነን የአማራን ትግል መምራት ያለብን ወይም አለቃ መሆን ያለብን!” የሚል ዘመቻ አስነሥቶ ለመከፋፈል ጥረት ያደርግ ይሆናል፡፡ ዛሬ ስሙ ተቀይሮ ወሎ የሚባለው ቤተ አማራ የሸዋ ነገሥታት መሠረታችን፣ ምንጫችን ነው!” ይሉት እንደነበረ ሁሉ ሌላው የአማራ መሠረት አይደል ቤተ አማራ??? ወሎዎች ቢሉስ ጥሩ ነበር አማራነት በአካባቢው እንዲጎላ ወይም አካባቢውን በአማራነት recover ለማድረግ ያስችላልና!!!

ለማንኛውም ወገን ሆይ! እባካቹህ እንንቃ??? አሁን እስኪ አማራ በዚህ ሁሉ ፍዳ ተጠፍንጎ ተቀፍድዶ በተያዘበት በዚህ ወቅት እንዲህ እያሉ እርስበርስ መናቆር ጊዜው ነው??? አስፈላጊስ ነው??? አየ አለመታደል!!! አየ መረገም!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው