አገዛዙ ሆን ብሎ ሀገሪቱን ችግር ውስጥ እየከተታት ነው!!!
አገዛዙ አሁን አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ አሜሪካ በዓባይ ግድብና ድርድር ዙሪያ ዛሬ ያወጣችውን መግለጫ በመቃወም መግለጫ አውጥቷል!!!
ከጥቂት ቀናት በፊት እንደምታስታውሱት የግድቡ የመጀመሪያ የውኃ አሞላል እና የውሃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ ላይ ስምምነት እንደተደረሰና ለፊርማ ብቻ ቀነ ቀጠሮ እንደተያዘ እራሱ አገዛዙ በተደራዳሪ ቡድኑ በኩል በአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው መግለጫ ገልጾ እንደነበረ ታስታውሳላቹህ!!!
በዚያ መግለጫ ላይ ተደራዳሪ ቡድኑ እጅግ አሳፋሪና አስቆጪ በሆነ መልኩ “37 ቢ.ሜ.ኪ. ውኃ በየዓመቱ ከግድቡ ለመልቀቅ ተስማምተናል፣ በድርቅ ጊዜም ግድቡ ውስጥ ያለውን ውኃ ልንለቅላቸው ተስማምተናል….!” ብሎ ገልጾ ስለነበርና ይሄም ደግሞ ሀገራችንን የዓባይን ወንዝ ለመስኖ ልማት ለዘለዓለሙ እንዳትጠቀምበት የሚከለክልና ከፍተኛ የሀገር ክህደት ስምምነት በመሆኑ አገዛዙ ይሄንን ስምምነት እንዳይፈርም በተለይ እኔ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምሁራን፣ የሃይማኖት ተቋማት ወዘተረፈ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በመጋበዝና በመወትወት ጭምር ደጋግሜ ጮኼ ነበር!!!
ከዚያም ምሁራኑ በየአቅጣጫው በአገዛዙ ላይ ጫና በማሳደራቸው የፊርሚያው ቀን አገዛዙ ሳይፈርም ቀረ፡፡ አገዛዙ ፊርሚያውን አያስቀምጥም እንጅ በድርድሩ ግን ተስማምቶ ስለነበረ እንደገና ማፈግፈጉ እንኳንና ግብጽና ሱዳንን ይቅርና አሜሪካን ጨምሮ በእጅጉ አበሳጭቷል!!!
የኔ ግምት አገዛዙ የስምምነቱን ዝርዝር ውል ለማዘጋጀት ቀናት የሚጠይቅ ጉዳይ ሆኖ ፊርሚያውን በሰዓቱ አያስቀምጥም እንጅ ስምምነቱ የሀገራችንን ሉዓላዊነት በእጅጉ እንደሚዳፈር፣ ብሔራዊ ጥቅሟን ለዘለዓለሙ አሳልፎ እንደሚሰጥና የሀገር ክህደት እንደሆነም አሳምሮ እያወቀ በድርድሩ ላይ ተስማምቶ የወጣው “ሆን ብሎ ሀገራችንን ችግር ውስጥ ለመክተት አስቦ ነው!” ብየ ነው የማምነው!!!
ይሄው እንዳሰበውም አሜሪካ እጅግ አሳፋሪ በሆነ መልኩ በማያገባት ገብታ ለግብጽና ለሱዳን ጥብቅና በመቆም በቁጣ ተሞልታ መግለጫ እስከማውጣት ደርሳ የግድቡ የመጀመሪያ
ሙሌት እና የውኃ አለቃቅ መመሪያ እና ደንብ የስምምነት ፊርሚያ ሳይፈረም ግድቡ ውኃ መሙላት እና የመጀመሪያ ደረጃ ኃይል የማመንጨት ተግባር እንዳይፈጽም አስጠንቅቃ ዛሬ መግለጫ አውጥታለች!!!
አሜሪካ በዚህ ደረጃ እራሷን አዋርዳ ከግብጽና ሱዳን ጎን እንድትቆምና መግለጫም እንድታወጣ ያደረጋት ወይም ግብጽና ሱዳን አሜሪካንን የመሰለ ፈርጣማ ደጋፊ እንዲያገኙ ያስቻላቸው ወይም አሜሪካ ፍትሐዊ የወንዙን ውኃ ተጠቃሚነትን በተጻረረ መልኩና ከኢትዮጵያ ጥቅም በተጻራሪ እንድትቆም ያደረጋት ሆን ብሎ እራሱ አገዛዙ ነው!!!
“አገዛዙ ለምን ወይም ዓላማው ምንድን ነው እንዲህ ያደረገበት ምክንያት?” ተብሎ ቢጠየቅ አገዛዙ እራሱን ለአሜሪካ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሎሌ አድርጎ በማቅረብ የትራንፕ አሥተዳደር አሜሪካንን በዚህ አሳፋሪ ተግባሩ ፋውል በማሠራትና በማሳጣት ለዲሞክራቶቹ ነጥብ ማስቆጠሪያ በማመቻቸት በመጪው ምርጫቸው ሪፐብሊካኖቹ እንዲሸነፉ ለመርዳት ነው!!!
እንግዲህ ይታያቹህ ለአሜሪካ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጥቅም ሲል የገዛ ሀገሩን ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ባንዳ አገዛዝ ነው ያለን!!!
እጅግ አያሳዝንም??? እጅግ አያሳፍርም???
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው