ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ወ/ሮ እታፈራሁ ኅ/ማርያም ማን ናቸው??..

Image may contain: 1 person, selfie and closeup
Image may contain: 1 person


ማሳሰብያ፤…በፎቶው ላይ የሚታዩት ወ/ሮ እታፈራሁ ኅ/ማርያም በወጣትነት እድሜና አሁን ነው።

ብዙ የማይተረክላቸው ግን ብዙ የሰሩና ሊደነቅ የሚገባው ችሎታና ጽናት ያሳዩ ሴቶችን መዘከር ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡ በሰሞኑ የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር ለምሳሌ በሺ የሚቆጠሩ ሴቶች በዚህ ጦርነት ተሳትፈው እንደበር ማንሳትና ወንድ ጀኞችን እንደምናደንቀው ሁኡ እነሱንም ገድልካቸውንም ማክበር ይገባናል ፡፡ አጼ ምኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ብጡል ላስገኙልን ድል፤ በኋላም ከአገር በቀል አንባገነን መንግስቶች ጋር በተደረገ ትግል ሴት እናቶች ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። ከዚህ አንጻር ሰሞኑን 98 ናዓመታቸውን ያከበሩትና ታጋይ ልጆችን፤ ኢሕአፓዎችን ወልደው ያሳደጉት የነ ሳሙኤል ዓለማየሁ፤ የዳዊትና የኢያሱ ዓለመያሁ እናት ወይዘሮ እታፈራሁ ኅ/ማርያም መጠቀስ ያለባቸው ናቸው፡፡

ወ/ሮ እታፈራሁ ኅ/ማርያም ከ አባታቸው አቶ ኅ/ማርያም ተሰማና ከ እናታቸው ከ ወ/ሮ ጣይቱ ደበበ በ ደምቢዶሎ ከተማ በ የካቲት 7 ቀን 1914 ዓ/ም ተወለዱ። ወ/ሮ እታፈራሁ ለ እናት አባታቸው የመጀመርያ ሴት ልጅ ነበሩ። እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ ሀገሩና ጊዜው በፈቀደው መንገድ አባታቸው አስተማሪ ቀጥረውላቸው እስከ ዳዊት መድገም፤ መፃፍና ማንበብን ተምረዋል። ወላጅ እናታቸው በ 25 ዓመት እድሜያቸው በሞት ስለተለዩአቸው የታናሽ እህታቸውና ወንድማቸው አሳዳጊ በመሆን፤ በለጋ እድሜያቸው የቤተሰብ ሃላፊነት ልምድን አግኝተዋል። ለ አካለ መጠን በደረሱ ጊዜም ወደውና ፈቅደው ከ አቶ አለማየሁ አስፋው ጋር በጋብቻ በመጣመር የሰባት ልጆች እናት ሆነዋል። ከአመታት በኋላ ወላጅ አባታቸውን በ 55 ዓመታቸው፤ ባለቤታቸውንም በ 66 ዓመታቸው በድጋሚ በሞት ቢለዩዋቸውም ሌላ ትዳር ሳይመሰርቱ ልጆቻቸውን አሳድገዋል። የመጀመርያ ልጃቸው በሰባት አመት እድሜው በበሽታ ታሞ በሞት ሲለያቸው፤ ቀሪዎቹን ማለትም አራት ወንዶችና ሁለት ሴቶች በስነምግባር አስተምረው አሳድገዋል፡፡

ወይዘሮ እታፈራሁ ተዋህዶ ሀይማኖትናቸውን አጥብቀው የሚከተሉ፤ ሞራልና ስንመግባር የተላበሱ እናት ሲሆኑ፤ በፖለቲካውም መስክ ንቃትን የያዙ ነበርና፤ ልጆቻቸውን አኩሪና ቀና ዜጋ እንዲሆኑ፤ከአልባሌ ጠባዮች እንዲርቁ፤ አዛውንት አክባሪና ድሃንም አፍቃሪ እንዲሆኑ አስተምረዋቸዋል፡፡ የ ኢሕአፓ መስራችና እስካሁንም በትግል ላይ ያለው ልጃቸው አቶ ኢያሱ አለማየሁ ለምሳሌ ወደ ንቃትና ፖለቲካ አቅጣጫ ካስገቡኝ አንዷ እናቴ ናት ሲል ከዚህ በፊት መናገሩ ይታወሳል፡፡ አራተኛ ልጃቸው ዳዊት አለማየሁ በደርግ ዘመን በ 31 ዓመቱ በቀይ ሽብር በደሴ በግፍ ተገድሎባቸዋል። የ ኢሕአፓ አባል በመሆን በህቡዕ ሲታገል የነበረውን ትልቁን ልጃቸውን ሳሙኤል ዓለማየሁን አምጪና አስረክቢን በሚልም ከወር በላይ በሶስተኛ ጣቢያ/ማዕከላዊ ታስረው ተፈተዋል፡፡

በሀገሪቱ በተካሄደው ምስቅልቅል አገዛዝ ልጆቻቸው ለትምህርት ከሀገር ቢወጡም ተመልሰው መግባት ባለመምረጣቸው ወ/ሮ እታፈራሁ ከልጆቻቸው ጎን ለመሆን ኑሯቸውን በአሜሪካ አድርገዋል። ሁለተኛ ልጃቸው ሳሙኤል አለማየሁም በ ድንገተኛ ሞት ሲለያቸው፤ በአሁኑ ወቅት ሁለት ወንዶች ልጆቻቸው ዳንኤል አለማየሁና ኢያሱ አለማየሁ እንዲሁም ሁለት ሴቶች ልጆቻቸው ሃና አለማየሁና ሳባ አለማየሁ በህይወት ይገኛሉ።

ወ/ሮ እታፈራሁ በጣም ጠንካራ፤ መንፈሰ ፅኑ፤ ሀገራቸውንና ወገናቸውን በጣም የሚወዱ፤ እስከአሁኗ ሰአት በእድሜያቸው መፅሃፍ ማንበብ የእለት ተግባራቸው የሆነ ና መፅሃፍ ማንበብ ትልቅ ደስታ የሚሰጣቸው ተወዳጅ እናት ናቸው። በገፋ እድሜያቸው ቀቅለው የሚበሉ፤ ደረጃ የሚወጡ፤ በማንኛውም መንገድ በራሳቸው የሚተማመኑ፤ እራሳቸውን የቻሉና የሚንከባከቡ፤ በጠንካራ እምነትና ተስፋ የተሞሉ ናቸው ፡፡

ወይዘሮ እታፈራሁን ልዩ የሚያደርጋቸው አድርባይነትና ዘረኘትን መጥላታቸው ብቻ ሳይሆን የፍኖተ ዴሞክራሲ ጽኑ ተከታታይና አደናጋሪ ሹሞች ለስልጣን ሲበቁም ያልተደናገሩ የህዝብን መብትና ጥያቄ ደጋፊ እናት ሆነው መቆየታቸው ነው ፡፡ አዲስ አበባም ባሉበት የደርግ ጊዚ ሆነ ወያኔም ለስልጣን ከበቃ በኋላ፤ በተጨባጭ የ ኢሕአፓን ትግል በልዩ ልዩ መስክ አደጋን ሳይፈሩ ረድተዋል ፡፡ ለህዝብ ሲሉ ተስፋ ሳይቆርጡ የሚታገሉ ልጆችን ችግር ሳይፈታቸው በማሳደጋቸውና ለቁም ነገር በማብቃታቸው ሳይሆን ራሳቸውም የህዝብ ትግልን በአቅማቸው ደጋፊ ሆነው ጸንተው መቆየታቸውን እናደንቃለን ፡፡

ክብር ለጀግናው ትውልድ ለ ኢሕአፓ እናቶች!!

ለህግ የበላይነት፤ ለሰላም ለዴሞክራሲና ለ እኩልነት..

ሁሉንም ያካተተ የሽግግር መንግስት!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!