አንዳንድ የዋህ ሰዎች “አቶ መለስ ብዙ የሠራቸው ጥፋቶች ቢኖሩም!” ይሉና የዓባይ ግድብን ፕሮጀክት በተመለከተ ግን ሊደነቅና ሊመሰገን እንደሚገባ አበክረው ሲናገሩ ይደመጣሉ!!!
ይሄ ግን ሲበዛ ማስተዋል የተለየውና የዓባይን ግድብ ዓላማ ካለማወቅ የሚሰነዘር ያልበሰለ አስተሳሰብ ነው!!!
አቶ መለስ የፈጸማቸውን የሀገር ክህደት ተግባራትን፣ በሀገር ህልውና ላይ የጸማቸውን ደባዎችንና በሕዝብ ላይ የፈጸማቸውን ለከት የለሽ ግፎችን ዓይተን እነዚህ የዋሃን ወገኖች አቶ መለስ ጥሩ ሠርቷል የሚሉትን ካየን ሰውየው በብዙ ዕዳ የሚጠየቅ እንጅ ፈጽሞ ከወጪ ቀሪ ተሰልቶ ሊመሰገንበት የሚገባው መልካም ሥራ የሚቀረው ወይም የሚኖረው ሆኖ አይገኝም!!!
ሲጀመር አቶ መለስ ወይም ወያኔ ይሄንን ትልቅ ፕሮጀክት ማለትም የዓባይን ግድብ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት መገንባት አስቦ ያስጀመረው ለኢትዮጵያ ጥቅም ሳይሆን ኢትዮጵያን አፍርሶ ለሚገነባት ታላቋ ትግራይ ነው!!!
አቶ መለስን በዓባይ ግድብ ምክንያት ማድነቅና ማመስገን ማለት ወያኔ ለዕኩይ ዓላማው በራሳችን ወይም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የተፈጸመን ዝርፊያንና ውንብድናን ማድነቅና ማመስገን ማለት ነው!!!
የዚህ ግድብ ሥራ በዚህ ዘመን መጀመሩ ኢትዮጵያን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ እንዴት ቀፍድዶ እንዳሰራት፣ ዕድገቷን እንዴት ወደኋላ እንደጎተተውና በድምር ውጤቱም ሀገሪቱን ምን ያህል ለኪሳራ እንደዳረጋት ብዙዎቻቹህ አትገነዘቡም!!!
ሌላው ቀርቶ ሀገሪቱን ብድርና እርዳታ እንኳ እንዳታገኝ አድርጓታል፡፡ የሀገሪቱ ዓመታዊ ባጀት በእርዳታ በሚገኝ ቀጥተኛ የባጀት ድጋፍ ለሚንቀሳቀስባት ሀገር ብድርና እርዳታ አለማግኘት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በግልጽ መገንዘብ የሚቻል ይመስለኛል!!!
ምን ለማለት ፈልጌ ነው፡፡ ግድቡ በዚህ ዘመን እንዲገነባ መደረጉ ፈጽሞ ሰዓቱ አልነበረም ነው ለማለት የፈለኩት፡፡ ሀገሪቱን ለብዙ ሊጠገን ለማይችል ኪሳራ የዳረጋትም በዚህ ምክንያት ነው!!!
የግድቡ ግንባታ ቢያንስ ሦስት ዐሥርት ዓመታት መቆየት ነበረበት፡፡ በዚህ ሦስት ዐሥርት ዓመታት ሀገሪቱ ያላትን ሪሶርስ እንዲሁም የሚሰጣትን ብድርና እርዳት በአግባቡ ተጠቅማ ሥራ ላይ ብታውል በሚፈጠረው ሁሉን አቀፍ አቅም ያኔ ዓባይን ያለችግርና ያለ ግብጽ ትርጉም ያለው እንቅፋት መገንባት በተቻለ ነበረ!!!
በዚህ ጉዳይ ላይ የዛሬ ስድስት ዓመት አንድ ስፋትና ጥልቀት ያለው ረዘም ያለ ጽሑፍ ጽፌ ነበር፡፡ አገዛዙ ጽሑፉን ከብዙ ድረገጾች አስጠፍቶታል፡፡ ማንበብ ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ፦
እነ አቶ መለስ የሀገሪቱን አዝማሚያ ሲያዩት ኢትዮጵያን መግዛት የማይችሉበት ዘመን መምጣቱን ተገነዘቡና እነሱ የማይገዟት ኢትዮጵያ ከመጣች ደግሞ ከዚያ በኋላ ሀገሪቱ ለአንድም ቀን እንኳ ቢሆን ህልው ሆና እንድትቆይ አይፈልጉምና ነው እነ አቶ መለስ ግድቡን በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ኮስት በዚያ ሰዓት ለመገንባት ጥድፊያ ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው!!!
በዚያም ሆነ በዚህ አቶ መለስ በዚህ ግድብ ግንባታ የሚረገም እንጅ ፈጽሞ የሚመረቅና የሚመሰገን አይደለም!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን በዚህ ሁሉ የማይመች ሁኔታ አንዴ ወደግድብ ሥራው እንዲገባ ተደርጓልና የሚያስከፍለውን ዋጋ ሁሉ ከፍሎ ግድቡን ከማጠናቀቅ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውምና በዚህ መበርታት ይኖርበታል!!!
እርግጠኛ ሆኘ የምነግራቹህ ነገር ቢኖር ግን ይሄ ግድብ እንደተጠናቀቀ ወያኔ ሀገሪቱን አፍርሶ ይሄንን የዓባይ ግድብ ይዞ በመገንጠል ታላቋን ትግራይ ለመመሥረት ይንቀሳቀሳልና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን ፈተናህን ታሳቢ አድርገህ ተንቀሳቀስ!!!
http://www.goolgule.com/abay-blessing-or-curse/
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው