የውይይት መድረክ “ የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8” – ክፍል አንድ

March 6, 2020

Source: https://tracking.feedpress.it/link/17593/13324395
https://tracking.feedpress.it/link/17593/13324396/amharic_95d7341b-49b3-4b5d-9139-f103b8ca7032.mp3

የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 በየአመቱ በአለም ዙሪያ የሚከበር ሲሆን አላማውም የተለየ ስልጣን እና ቦታ የሌላቸው ሴቶች ለመብቶቻቸው መከበር የከፈሉትን መሰዋትነት ፤ ያሳለፉትን ትግል እና ያስመዘገቡትን ውጤት ለመዝከር ነው።

ሴቶች በትግላቸውም አንጻራዊ የሆኑ መብቶቻቸውን ለማስከበር ፤ ሰርተው ለመግባት የእድል በሮች የተከፈቱላቸው ቢሆንም በተቃራኒውም ሴቶች ዛሬም ድረስ በየትኛውም የአለማችን ክፍል ቢኖሩ የጾታ እኩልነታቸው አልተረጋገጠም።

ዘንደሮም የአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ማርች 8 ሲከበር በመርህ ደረጃ የሚያጎላው  የጾታ እኩልነትን ነው።

የዛሬውን  የውይይት መድረክ ፕሮግራማችንን ማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለመዝከር ይሆን ዘንድ ብለናል።

የውይይታችን ተሳታፌዎች :-

  ወ/ሮ ብርቱካን ሽታዬ ቢያድግልኝ  በቢሮ ኦፍ ሚቲሪዮሎጂ ክላይሜት ስፓሻል ዳታ የቡድን መሪ እንዲሁም በጂ ፒ ኤስ ሚቲሪዮሎጂ ተመራማሪ

ወ/ሮ እመቤት ታደሰ በናሽናል አውስትራሊያ ባንክ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው።

በመላው አለም ለሚገኙ ሴቶች እና ለሴቶች እኩልነት ተቆርቋሪ ወንዶች ሁሉ “ መልካም የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 ” ይሁን ::

የውይይት መድረክ “ የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8” – ክፍል ሁለት

March 6, 2020

Source: https://tracking.feedpress.it/link/17593/13324597
https://tracking.feedpress.it/link/17593/13324598/amharic_c879119b-0a60-4bfc-b1ae-ba2a5e93781e.mp3

የዛሬውን  የውይይት መድረክ ፕሮግራማችንን ማርች 8 የአለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ለመዝከር ይሆን ዘንድ ብለናል።

የተሻለች አለምን ለማምጣት የምንፈለግ ከሆነ  የጾታ እኩልነትን ማረጋገጥ የግድ ነው። ይህንን ተግባር ሴቶች ብቻ የሚወጡት ሳይሆን ወንዶችም በጋራ በቅንነት ሊሳተፉበት የሚገባ አላማ ነው።  በአጠቃላይ በማህበረሰቡ ዘንድ ስር ሰድዶ የተንሰራፋውን  ሴቶችን የማሳነስ ፤አይችሉም የማለት፤ ሳይመዘኑ መፈረጅ የመሳሰሉትን  ጎታች አስተሳሰቦች ለማስወገድ ሁሉም በጋር መስራት እንዳለበት የውይይታችን ተሳታፊዎች ያምናሉ።

የውይይታችን ተሳታፌዎች :-

 ወ/ሮ ብርቱካን ሽታዬ ቢያድግልኝ  በቢሮ ኦፍ ሚቲሪዮሎጂ ክላይሜት ስፓሻል ዳታ የቡድን መሪ እንዲሁም በጂ ፒ ኤስ ሚቲሪዮሎጂ ተመራማሪ

ወ/ሮ እመቤት ታደሰ በናሽናል አውስትራሊያ ባንክ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ አማካሪ ናቸው።

“ በመላው አለም ለሚገኙ ሴቶች እና ለሴቶች እኩልነት ተቆርቋሪ ወንዶች ሁሉ “መልካም የአለም አቀፍ ሴቶች ቀን ማርች 8 “ ይሁን ::