የተሟላ እንዲሆን
ጀግኖች መተረኩ
ትግሉን የጎዱትም
ይነገር ታሪኩ!!!

አብዩ ኤርሳማ ማን ነው?

Image may contain: 1 person, closeup

ይሄን ፎቶ አግኝቼ የተጠቀምኩት ከ ህይወት ተፈራ “ Tower IN THE SKY” መፅሃፍ ላይ ነው።

አብዩ ኤርሳማ በቀድሞ ስሙ የ ቀ/ኅይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በመባል ይታወቅ በነበረውና በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግ ፋኩሊቲ የአራተኛ አመት ተማሪ የነበረ ወጣት ሲሆን፤ በወቅቱ በኢሕአፓ ታሪክ ውስጥ ስማቸው ገኖ ከወጡት ወጣቶች አንዱ ነበር። እንደማንኛቸውም የዛ ትውልድ ወጣቶች በትምህርቱ በጣም ጎበዝ እንደነበርም የሚያውቁት ይመሰክራሉ።
አብዩ ኤርሳማ የጌታቸው ማሩ በጣም የቅርብ ጓደኛ የነበረ ሲሆን፤ “አብዮት” ይባል የነበረው ድርጅት አባልና ድርጅቱን ይዘው ከኢሕአፓ ጋር ከተቀላቀሉት ወጣቶች አንዱ ነበር። በኋላም ብርሃነ መስቀልና ጌታቸው ማሩ ድርጅቱ ከሚከተለው መርሆ ተፃራሪ በመቆምና በብዙሃን ድምፅ አንገዛም ብለው ከድርጅት ሲባረሩ አብዩ ኤርሳማ ከነሱ በመወገን በአንጀኝነት ቆሞና ከፋሺስት ደርግ ወግኖ የኢሕአፓ ወጣቶችን በማሳሰርና በማስገደል በድርጅቱ ላይ መጠነ ሰፊ አደጋ አድርሷል።

በአዲስ አበባ የ ዞን 5 ( zone 5) ተጠሪ በመሆን ፓርቲውን ከ ወጣቱ ሊግ ጋር በአገናኝነት ይንቀሳቀስ የነበረው አብዩ ኤርሳማ አንጃ በመሆን የድርጅቱን አባላት በድርጅቱ ላይ በተፃራሪ እንዲቆሙ እና የአንጃውን መስመር እንዲከተሉ ውስጥ ውስጡን በመቀስቀስ፤ ከደርግ ግድያ ለመዳን ወደ ኢሕአሠ ሰራዊት ይላኩ የነበሩትን ወጣቶች አቅጣጫ በማስቀየር አንጃው ወደነበረበት መርሐ ቤቴ እንዲሄዱ ለማድረግ በመሞከር፤ የመጠለያ ቤቶችን አድራሻ ፤ የማይታወቁ የኢሕአፓ አባላትን ስም ዝር ዝር ለፋሺስት ደርግ አሳልፎ በመስጠት፤ የድርጅቱን ሚስጥራዊ ሰነዶች ለጠላት አሳልፎ በመስጠት፤ የድርጅቱን መሳርያና ገንዘብ እምቢ አላስረክብም ብሎ ለአጃው መጠቀምያ በማድረግ ከፍተኛ ወንጀል ፈፅሟል። ለብዙ ሺህ ወጣቶች ሞት ተጠያቂ ነው።

በመጨረሻም አንጃዎቹ በተለይም አብዩ እርሳማ የሚያደርሰው አደጋ እየከፋ ሲመጣ በፓርቲው ውሳኔ እርምጃ ተወስዶበታል።

ታሪክ ሁሉንም አይረሳም!!!!!