የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ነን!” የሚሉ የአሸባሪው የጃዋር ኩሊዎች የተለያዩ የቤተክርስቲያን መጻሕፍትን በመጥቀስና አሳስቶ በመተርጎም ቤተክርስቲያን ኦሮሞን እንደምታንቋሽሽ፣ እንደምታራክስ አድርገው በየቀረቡበት መድረክ ሁሉ እየከሰሱና ስም እያጠፉ ይገኛሉ!!!

ከእነኝህ መጻሕፍት አንዱ ራዕየ ማርያም የተባለው የቤተክርስቲያን መጽሐፍ ነው፡፡ እነኝህ የጃዋር ቡችሎች ሲኖዶስ ፊት በቀረቡ ጊዜም ይሄንን መጽሐፍ ጠቅሰው ቤተክርስቲያንን ከሰው ነበር፡፡ ሲኖዶሱም መጽሐፏን ያሳተማት የግል ማተሚያ ቤት በመሆኑ መወቀስ ያለበት ማተሚያ ቤቱ መሆኑን በመግለጽ እንደመለሰላቸው ሰምተናል፡፡ ይሄ የሲኖዶሱ መልስ ግን ትክክል አልነበረም!!!

ምክንያቱም ጋላ ወይም ጋሎች የተኮነኑበትና በክፉ ሥራቸው የተወገዙበት መጽሐፍ ራዕየ ማርያም ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያን የትርጓሜ መጻሕፍት ጭምርም በመሆኑ!!!

እነኝህ ቤተክርስቲያንን ባልገባቸው ነገር ላይ የሚከሱ ወገኖች የሚጠቅሱት ራዕየ ማርያም ገጽ 36-37 ያለው ገጸ ንባብ የሚከተለውን ይላል፦

“….ከዚህም በኋላ ከሥር እስከ ጫፍ፥ ከጫፍ እስከ ሥር ድረስ በአምስት ሽህ ዓመት የማይደረስ ገደል አሳየኝ። ያንዱ ነፍስ ባንዱ ነፍስ ላይ ሲወድቅ አየሁ። እኔም ምንድን ናቸው?’ ብዬ ልጄን ጠየኩት፤ እርሱም፦ በአባታቸው፣ በወንድማቸው፣ በልጃቸው፣ በባልንጀራቸው ሚስት የሚሴስኑ ናቸው!’ አለኝ። አራስ መርገም፣ ደንቆሮን፣ እስላም፣ ጋላ፣ ሻንቅላ፣ ፈላሻ፣ የተኙ (የተገናኙ ወይም ግብረሥጋ የፈጸሙ) ፈረስ፥ አህያ የሚያደርጉ፣ ምድርን ሰንጥቀው የሚያደርጉ፣ ወንዱን ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚያደርጉ፣ ካህን ሆኖ ከሌላ ሴት፣ የካህኑ ሚስት ከሌላ ወንድ የሔዱ እነዚህ ሁሉ ኩነኔያቸው ይህ ነው!’ አለኝ!” ይላል፡፡

በቤተክርስቲያን ቋንቋ ጋላ ማለት ያላመነ ያልተጠመቀ አረማዊ ማለት ነው፡፡ የብሔረሰብ መጠሪያ ስም አይደለም፡፡ ይሄንን የማያውቁ ሰዎች ራዕየ ማርያምን ጨምሮ በሌሎች መጻሕፍት ጋላ ተብሎ የተጠቀሰውን ሁሉ ኦሮሞ ማለቱ እንደሆነ በስሕተት ተረድተውታል!!! በዚህ ጽሑፍ ይሄ ግንዛቤያቸው በእጅጉ የተሳሳተ መሆኑን እናስረዳለን፡፡ በርግጥ ይሄንን ጉዳይ ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ በተለያዩ ጽሑፎቸ በተደጋጋሚ የገለጽኩት ነገር ነው!!!

ይህ የጃዋር ቡችሎች ግንዛቤ የተሳሳተ መሆኑን ከሚያረጋግጡ የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ለምሳሌ ያህል ሁለቱን እጠቅሳለሁ፦

አንደኛው የውዳሴና ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜ ነው፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ ዛሬ ሊብያ ተብላ በምትጠራው ሀገር ስለ ነበረው ሐዋርያ ተፍጻሜተ ሠማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ሲተረክ ይሄንን ቅዱስ ሠማዕት አባት ከሀዲው አርዮስ ቆይ በጋላ ነው አንገትህን አስቆርጨ የማስገድልህ!” እያለ ሲዝትበት ቆይቶ መጨረሻ ላይ እንደዛተው አንገቱን በጋላ አስቆርጦ እንዳስገደለው ይተርካል!!!

ሁለተኛው ተአምረ ማርያም ነው፡፡ ይሄ የቤተክርስቲያን መጽሐፍም ግብጽ ሀገር የነበረችውንና ብዙ ተአምራት የተደረገባትን ደብረምጥማቅ ማርያም የተባለችውን ቤተክርስቲያን ጋላት (ጋሎች) እንዳፈረሷት ይገልጻል፡፡ ሌሎች ተመሳሳይ ተረኮችም በተለያዩ የቤተክርስቲያን መጻሕፍት አሉ!!!

እንግዲህ መረዳት እንደምትችሉት ሁሉ መጻሕፍቱ ጋላ ወይም ጋላት (ጋሎች) ሲሉ አረማውያን ወይም ኢአማንያን!” ማለታቸው ነው እንጅ ሊብያ ውስጥ አርዮስ ተፍጻሜተ ሠማዕት ቅዱስ ጴጥሮስን ሲያስገድል በኦሮሞ ነው ያስገደለው፣ ግብጽ ውስጥ ደብረ ምጥማቅን ያፈረሷት ኦሮሞዎች ናቸው፣ ኦሮሞዎች ሊብያና ግብጽ ይኖራሉ ወይም አሉ!” ማለታቸው እንዳልሆነ ማንም ሊረዳው የሚችለው ጉዳይ ነው!!!

በመሆኑም በዚህ ዐውድ ራዕየ ማርያም ላይ ከጋላ ወይም ከአረማዊ ሰዎች ጋር የተኙና ለዚህ ኃጢአታቸውም ንስሐ ያልገቡ ሰዎች ሲዖል ውስጥ እንደገቡ መገለጹ ትክክል ነው ስሕተት የለበትም!!! ምክንያቱም የሚያምን ከማያምን ጋር ኅብረት ስለሌለው፣ በክርስቶስ የተቀደሰ ሰው ካልተቀደሰ ሰው ጋር ተጋብቶ መርከስ ስለሌለበት ቤተክርስቲያን ምእመናን ከማያምኑ ሰዎች ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ የሚከለክል ቀኖና ሠርታለችና ነው!!! የማያምኑ ሲባል ከላይ ከራዕየ ማርያም ላይ እንዳነበባቹህት እስላም፣ ጋላ፣ ሻንቅላ ብቻ አይደለም ፈላሻን ማለትም አይሁድን እንኳ ሳይቀር ጨምሯል!!!

አይሁዶች በበኩላቸው ከእነሱ ወገኖች ውጭ ከሆኑ በዙሪያቸው ካሉ የአሕዛብ ወገኖች ማለትም ከፍልስጥኤማውያን፣ ከኢሎፍላውያን፣ ከኬልቄዶናውያን፣ ከከለዳውያን፣ ከከለሳውያን፣ ከሳምራውያን፣ ከሰርቂሳውያን ወዘተረፈ. እና በሌላ በየትም የዓለማችን ክፍል ካለ ከሌላ ወገን ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ ፈጽመው ከተገኙ እንደሚረክሱና እንደሚገለሉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡

በዚህም መሠረት እስራኤላውያን እኛ ኢትዮጵያውያን ያውም ከእነሱ በላቀ መልኩ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወይም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን (አሞ. 97) አያውቁ ስለነበረ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የካህኑን የዮቶርን ወይም የራጉኤልን ልጅ ኢትዮጵያዊቷን ሲፓራን ስላገባ ወገኖቹ እኛ እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የተለየን የተመረጥን ሕዝብ ስለሆንን ከሌላ ወገን ጋር እንዳንጋባ ተከልክለን እያለ ለምን ከእኛ ውጭ ከሆነ ወገን አገባ?” ብለው አጉረምርመውበት ነበረ፡፡ ባለማወቅ ያጉረመረሙትም በእግዚአብሔር ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ. 121-16በኦሪት ዘመን እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ሕዝብ ወይም ልጆች ቢሆኑም አሁን ግን ዘመኑ የሐዲስ ኪዳን ዘመን በመሆኑና መሲሑን ኢየሱስ ክርስቶስን ባለመቀበላቸውና ባለማመናቸው እኛን ክርስቲያኖችን ብንጋባቸው ከሚያረክሱን ወይም ኃጢአት ከሚሆኑብን ወገኖች ተቆጥረው ከእነሱ ጋር እንኳ እንዳንጋባ ቤተክርስቲያን ከልክላናለች!!!

እናም ጋላ ማለት የብሔረሰብ ስም ሳይሆን በቤተክርስቲያን ቋንቋ አረማዊ ወይም ኢአማኒ ማለት በመሆኑ ነው ቤተክርስቲያን ክርስቲያን የሆነ ሰው ከእነሱ ጋር እንዳይጋባ የከለከለችው፡፡ ኦሮሞዎች የግራኝ አሕመድ ወረራን ተከትለው ወደ ሀገራችን ሲገቡ ኢአማንያን ወይም አረማውያን ስለነበሩ ጋላ ይባሉ እንደነበረ የሚታወቅ ነው፡፡ ከዘመን በኋላ ግን አምነው መጠመቃቸው ይታወቃል፡፡ ምንም እንኳ እስከአሁንም ድረስ ከእነሱ መሀል ያልተጠመቁና የራሳቸውን ዋቄፈታ የሚባል ባዕድ አምልኮ የሚከተሉ ያሉ ቢኖሩም ቅሉ፡፡ የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ጋላ የሚሏቸው ዛሬ ኦሮሞ ተብለው የሚጠሩትን ብቻ ሳይሆን ሌሎች እዚህ ኢትዮጵያ ይኖሩ የነበሩ ኢአማኒ ወይም አረማዊ ጎሳዎችንም ጭምር ነው ጋላ ይሉ የነበሩት፡፡ በዚህም ምክንያት ነው ከላይ እንደተጠቀሰው ቅዱሳት መጻሕፍቱ ሊቢያና ግብጽ ያሉ ኢአማንያንን ወይም አረማውያንን ጋላ ወይም ጋላት (ጋሎች) ሲሉ የጠሯቸው!!!

በቤተክርስቲያን ቀኖና መሠረት ክርስቲያን ማለትም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኝ ካልሆነ ወይም ካልሆነች በስተቀር ከሌላ ወገን ጋር መጋባትና የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም እንደማይቻል ማለትም ክልክል ወይም ኃጢአት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ አማራም ቢሆን ኢአማኒ ከሆነ ከዚህ ሰው ጋር መጋባት ክልክል ወይም ኃጢአት ነው!!!

እናም ጉዳዩ ይሄው ነው ተጣሞ ሊተረጎምና ቤተክርስቲያን ያለ በደሏ ልትወቀስበት አይገባም!!! ጋላ ተብሎ የተጠቀሰባቸው የቤተክርስቲያን መጻሕፍትም እንደተሳሳቱ ተቆጥረው ይስተካከሉ!” በሚል ሊቆነጻጸሉ አይገባም!!! ይሄንን ለማድረግ የሚያስብ ያልበሰለ አካል ካለ ከዚህ የደንቆሮ ተግባሩ ይቆጠብ!!! ይሄንን ማድረግ ማለት አሸባሪዎቹ እንደሚሉት ቤተክርስቲያን ስሕተት ፈጽማለች ማለት ነውና!!! ቤተክርስቲያን ሳትሳሳት እንደተሳሳተች ቆጥሮ ከአሸባሪዎች ጋር ተደርቦ ባልሠራችው ስሕተት መውቀስ ታላቅ በደልና ክህደት ነው!!! ያልገባው አካል ካለ ከላይ በገለጽኩት መልኩ ማስረዳት ብቻ ነው የሚያስፈልገው!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው