ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ሶፍያ አየለ ገ/መስቀል ማን ናት??..

ማሳሰብያ ለአንባቢዎቼ፤.…ስለ ሶፍያ አየለ እታች ካሰፈርኩት ሌላ ብዙም መረጃ ስለሌለኝ የምታውቋት መረጃ በመስጠት ሌሎቻችሁም ይሄንን አጭር ፅሁፍ.. SHARE … በማድረግ ተባበሩኝ። የጀግኖቻችን ታሪክ እንዳይረሳ ታሪክን አብረን እንፃፍ።
በአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ 15 ቀበሌ 30 ነዋሪ የነበረችውና በወቅቱ ቀዳማዊ ኅ/ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመባል በሚታወቀው ተቋም ትምህርቷን ስትከታተል የነበረችው ሶፍያ አየለ ገ/መስቀል በ የካቲት ወር 1970 ዓ.ም በኢሕአፓነት ተጠርጥራ በደርግ ፋሺስቶች ተይዛ ከታሰረች በኋላ በግፍ ተገድላለች። ሶፍያ አየለ በደርግ ፋሺስቶች የሞት ፍርድ ሲፈረድባት ገና የ 22 ዓመት ወጣት ነበረች።
ክብር የህዝብን ጥያቄ አንግቦ ግንባሩን ለጥይት ለሰጠ ጀግና ትውልድ!!
ለህግ የበላይነት፤ ለሰላም ለዴሞክራሲና ለ እኩልነት..
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!