ጅሩ እነዋሪ ከተማ ውስጥ ከውጭ የመጡ መናፍቃን “የነጻ የዓይን ሕክምና እንሰጣለን!” በሚል ሽፋን ድንኳን ተክለው የሕክምና አገልግሎቱን በመደለያነት በማቅረብ እየሰበኩና መጽሐፍ እያደሉ ሊቀበላቸው ያልፈለገውን ደግሞ ሕክምና እየከለከሉ ሰነበቱ!!!
የአካባቢው ሕዝብም የወረዳው የመንግሥት አካል ይሄንን ሕገወጥ ተግባር እንዲያስቆም በማመልከቻና በሰልፍ ጭምር ጠየቀ፡፡ ነገር ግን ምንም ዓይነት የማስተካከያ እርምጃ ሊወሰድ አልቻለም!!!
መናፍቃኑ ይባስ ብለውም በዚህ በታላቁ ጾም በሬ አርደው ሕክምናቸውን ለማግኘት ሲል የውሸቱን እሽ ያለውንና እየታከመ ያለውን ሰው ሥጋ ካልበላቹህ እያሉ ፈተኑት፡፡ በዚህ የአገዛዙን ሕገመንግሥት በሚጻረረው የመናፍቃኑ ሕገወጥ ተግባር የተቆጣው ሕዝቡ እየተፈጸመ ያለው ተግባር በትዕግሥት ሊቋቋመው ከሚችለው በላይ ስለሆነበትና የሚመለከተው መንግሥት ተብየው አካልም እርምጃ ሊወስድ ስላልቻለ የራሱን እርምጃ ወሰደ፡፡ ይሄም ትክክለኛና መወሰድ ያለበት እርምጃ ነው፡፡ እንዲያውም ሲያንሳቸው ነው!!!
የአገዛዙ ሕገመንግሥት “ማንኛውም የእምነት ተቋምና አገልጋይ የሆነ ግለሰብ ለእምነት ከተፈቀደለት የአምልኮ ስፍራ ውጭ በመንገድ፣ በፌርማታ ሕዝብ በሚሰባሰብባቸው ስፍራዎች ሁሉ መስበክ፣ ጥቅምን በመደለያነት በማቅረብ እምነትን የማስቀየር ተግባር መፈጸም የተከለከለ ነው!” ይላል!!!
አገዛዙ ለይስሙላ እንዲህ የሚል ሕግ አውጥቶ ሲያበቃ ግን በዚህ 29 ዓመት መናፍቃንን በመተባበር ሲሠራ እንዳያቹህት መናፍቃን ሕግ ጥሰው መንገድ ለመንገድ ብቻ ሳይሆን ቤት ለቤት በር እያንኳኩና እያስከፈቱ በመስበክ ጭምር የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን እየጠለፉ እንዲወስዱ፣ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የቀበሌ አዳራሾችን ሳይቀር በቸርችነት እንዲጠቀሙ በማድረግ፣ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ደግሞ ጤና ጣቢያን፣ ትምህርት ቤትን፣ ወፍጮ ቤቶችንና እርዳታን በመደለያነት በማቅረብ ሕዝበ ክርስቲያኑን እንዲጠልፉ ወይም እምነቱን አስቀይረው እንዲወስዱ አደረገ!!!
አገዛዙ ለ29 ዓመታት በእንዲህ ዓይነት ሕገወጥ እንቅስቃሴ እምነታቸውን እንዲያስፋፉ ወይም ምእመናንን እየጠለፉ እንዲወስዱ ሲያደርጋቸው የቆዩ መናፍቃን በአሁኑ ሰዓት ከ30 ሚሊዮን ማለትም ከግማሽ በላይ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናንን ማርከው ወይም ጠልፈው መውሰድ ችለዋል፡፡ በተለይ በሰሜን ሸዋ አንዳንድ የገጠር አካባቢዎች ጥቂት የማይባሉ አብያተክርስቲያናት አንድ እንኳ የሚሳለማቸው ምእመናን አጥተው ወናቸውን ቀርተዋል!!!
ይሄ ሕገወጥ የመናፍቃኑ ዝርፊያ ወይም ውንብድና እንዲቀጥል የሚፈልግ የጥቅም ተጋሪ ሆዳም ቅጥረኛና መናፍቅ ካልሆነ በስተቀር ጅሩዎች የወሰዱትን ሕጋዊ እራስን የመከላከል እርምጃ ሊያወግዝ ወይም ሊቃወም አይችልም!!!
እስከዛሬም እኛ ምእመናን እንዲህ መብታችንን ለማስከበር አለመንቀሳቀሳችን፣ እረኞች ነን ባይ ምንደኛ ጳጳሳት ወይም ሲኖዶስ ተብየውም አገዛዙ ይሄንን ሕገወጥ የመናፍቃኑን የምእመናን ዝርፊያ እንዲያስቆም ባለመጠየቃቸውና ዓይተው እንዳላዩ በመሆናቸው ነው መንጋው በተኩላት ተበልቶ ሊያልቅ የቻለው!!!
አገዛዙ ቀደም ሲል በአቦይ ስብሐት በኩል “የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሰራራ አድርጌ ሰብሬዋለሁ!” ሊል የቻለውም አንዱ ከዚህ የቤተክርስቲያን ኪሳራ የተነሣ ነው!!!
ከአሁን በኋላ ግን ጅልነቱ ይብቃ!!! ይሄ ዓይነት እርምጃ መናፍቃኑ መሰል ሕገወጥ ተግባራቸውን በሚፈጽሙበት የሀገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች ሁሉ ይወሰድ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው!