ለነገሩ እነ በሪሁን አዳነን ቦርዱ ውስጥ እያያቹሃቸው ትጠራጠራላቹህ ብየ አልገምትም!!!

እነኝህ አዲስ የዐሥራት ቦርድ የተባሉት ግለሰቦች ዐሥራት ሚዲያ በጋዜጠኛ ስም በፀረ አማራው ብአዴን ካድሬዎች የተሞላ መሆኑን እያዩና እያወቁ ከእነሱ ጋር ለመሥራት በቦርድ አባልነት ተመርጠው የገቡት የፀረ አማራው ብአዴን ቅጥረኞች በመሆናቸው እንደሆነ የማይገባው ሰው ካለ በደካማ የማሰብ የማሰላሰል ችሎታው ይዘን ይፈርም!!!

ቆይ ታዩት የለ አስተዋይ ልብ ካላቹህ ዐሥራት ሚዲያ በዚህ አዲስ የተባለ የቦርድ ዘመንም የተለየ ሥራ ካለመሠራቱ፣ የፀረ አማራው ብአዴን የሥራ ክንውን መለፈፊያና የአሰልቺ ስብሰባዎቹ ማስተላለፊያ ሆኖ ከመቀጠሉ እውነቱን ትረዱታላቹህ!!!

አማራ ሆይ! የዐሥራት ሚዲያ ነገር የሞተለት ነውና እርሳው፡፡ የአማራን ብሔርተኝነት ትግል ለማሳለጥ፣ ለማነቃቃት፣ ለመምራት፣ ለማጎልበት፣ ለማጠናከር …. በሚል የሞት ሽረት ዓላማ ተቋቁሞ ሲያበቃ የፀረ አማራው ብአዴን የሥራ ክንውንና ስብሰባ ሲለፈፍበት ከሚውለው፣ ሰኔ 15 ላይ በተወሰደው የግፍ እርምጃ እንዳየኸውም ፀረ አማራው ብአዴንና አብን የአማራን ትግል ሲያስረሽኑት አማራ ያለ አንዳች ተቃውሞ በዝምታ እንዲያሳልፍ ለእነኝሁ የወያኔ/ኦሕዴድ አህዮች ወይም ቅጥረኞች ማለትም ለፀረ አማራዎቹ ብአዴንና አብን አመራሮች አሳሳችና አደንዛዥ መልእክት ማስተላለፊያ ሆኖ ካገለገለው የፀረ አማራው ብአዴን ሚዲያ ዐሥራት ሚዲያ ተብየው እራስህን አርቅና ሌላ የራስህ የሆነ፣ እራስህ የምትመራውና የምትቆጣጠረው በትክክልም የአማራ የሞት ሽረት ትግል ሚዲያ የሆነ ሚዲያ አቋቁም!!!

ይሄንን ለማድረግ ስትንቀሳቀስ አሁንም የብአዴን ካድሬዎችና ቅጥረኞች ሰርገው ገብተው ጉድ እንዳይሠሩህ ተጠንቀቅ!!! ከብአዴን ጋር ንክኪ ያላቸውንና የነበራቸውን ሰዎች አታስጠጋ!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው