አየ ጉባኤ አማራ አያiii ድንቄም!!!

በስንት መከራ ስንት ዋጋ ተከፍሎበት የተቀሰቀሰውን የአማራ ብሔርተኝነትን ትግል የአማራን ሕዝብ እጅና እግር ጠፍንገው አስረው ያስረሸኑት ፀረ አማራዎቹ የወያኔ/ኦሕዴድ አህዮች ብአዴንና አብን የተለያዩ አካላት የጋራ ግብና ራእይ እንዲኖራቸው ለማድረግ!” በሚል ዓላማ ጉባኤ አማራ የምክክር መድረክ!” በሚል ሥያሜ ባሕርዳር ላይ በጋራ ባዘጋጁት ጉባኤ ኢመደበኛ አደረጃጀት!” ሲሉ የጠሩት የፋኖ አደረጃጀት እና የአማራ ብሔርተኝነት በጥብቅ የተወገዘበትን ጉባኤ እያካሔዱ እንደሆነ ሰምታቹሃል አይደል???

የሚገርመው ፀረ አማራው ኦሕዴድ አማራን ለመምታት፣ ጥቅሙን ለመንጠቅና ጸጥ ለማሰኘት በማሰብ ለ30ኛ ጊዜ እንደ አሸን የፈላ ልዩ ኃይል ባስመረቀ ማግስት እነኝህ ፀረ አማራ የጠላት ቅጥረኞች ባሕርዳር ላይ ተሰብስበው ፋኖን ፈጽሞ ልንታገሰው የማይገባና እንዲንቀሳቀስ ሊፈቀድለት የማይገባ ኢመደበኛ አደረጃጀት!” በማለት፣ የአማራ ብሔርተኝነትን ደግሞ ጽንፈኛ የመዋቅራችን ጠላት!” እያሉ አማራን ማውገዝ ማሸማቀቃቸው ነው!!!

እነኝህ ፀረ አማራ የጠላት ቅጥረኞች አማራን ምን ያህል ቢንቁት ነው ግን የዚህን ያህል የተዳፈሩት በሞቴ??? ጭራሽ የሞተ ውሻ ያህል እንኳ ሊፈሩትና ሊያፍሩት አልቻሉምኮ!!!

አብን አሁንም ከብአዴን ጋር በዚህ ደረጃ ተቆራኝቶ ወይም ተዛምዶ እያዩት አሁንም የአማራ ድርጅት አድርገው የሚያስቡት ዘገምተኞች መኖራቸው ነው ደግሞ እጅግ በጣም የሚገርመው ነገር!!! እነኝህ ዘገምተኞች መቸም ይነቃሉ ብላቹህ እንዳታስቡ፡፡ ምክንያቱም ከሰኔ 15 ፀረ የአማራ ትግል የግፍ ዘመቻ በላይ የአብንን ማንነትና የተመሠረተበትን የባንዳነት ዓላማ ሊያሳይ ሊያጋልጥ የሚችል ሁነት ሊኖር አይችልምና!!!

ፀረ አማራው የወያኔ/ኦሕዴድ አህያ ብአዴን የአማራ ወዳጅ፣ የአማራ አለኝታ ከሆነ የአማራ ጠላት ማን ሊሆን ነው ታዲያ??? ትናንትናም፣ ዛሬም ሆነ ነገ ቀንደኛው ቁ. 1 የአማራ ጠላት ማን ሆነና??? ሰው እንዴት ለዚህ ቀንደኛ የአማራ ጠላት ቅጥረኛ ሆኖ በግልጽ ሲንቀሳቀስ እያየ መንቃት ያቅተዋል??? ይሄ የጤና ነው??? ይሄ ከዘገምተኝነትም በላይ አይደለም ወይ???

እሽ ሰዉ አብኖች ካድሬዎች መሆናቸውን አይወቅ ግድየለም፡፡ ነገር ግን ሌላው ሁሉ ቢቀር አብን እንዲህ በይፋ ከሰኔ 15ቱ የፀረ አማራ ብሔርተኝነት ትግል የግፍ እርምጃ በኋላም ለብአዴን የዚህን ያህል ታማኝ አጋር መሆኑን ካሳየና ለዚሁ ፀረ አማራ የጥፋት ኃይል ብአዴን ቀና አመለካከት ያለው መሆኑን ካሳየ እነኝህ ዘገምተኛ ደጋፊዎቹ አብን ከብአዴን ጋር ያለውን ልዩነትና አስፈላጊነት እንዴት አድርገው ነው ግን justify ሊያደርጉ የሚችሉት???

አየ ወገኔ እንዲህ የማንም ባንዳ ቅጥረኛ መቀለጃና መጫወቻ ሆነህ ትቀር??? በጣም ያሳዝናል!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው