ትናንትና “በሕዝብ ተወካዮች!” ተብየ የወያኔ/ኢሕአዴግ ሆድ አደር የጉግማንጉግ አጋሰሶች አቶ ዳንኤል ክስረት ምን ያህል እንደተዋረደ ዓይታቹሃል!!!
የገረመኝ ጉግማንጉግ አጋሰሶቹ ዳንኤልን “በሃይማኖት ዕኩልነት የማያምን፣ በዜጎች መካከል ክፍፍል እንዲፈጠር የሚሠራ…!” ብለው በመዘኑበት ሚዛን ሌሎቹንም ከእስልምና እና ከመናፍቃን የመጡ ተሿሚዎችን መመዘን አለመፈለጋቸው ጨርሶም አለማሰባቸው ነው!!!
በነገራችን ላይ ይሄ የተደረገው ሆን ተብሎ መሆኑን እንድትረዱ እፈልጋለሁ!!! አገዛዙ በዚህ አሻጥሩ ማስተላለፍ የፈለው መልእክት ምን መሰላቹህ ለኦርቶዶክሳውያን ቦታ የሌለው መሆኑንና “ቦታ እንዲኖራቹህ ከፈለጋቹህ በጥፋት መንገድ እንደፈለግን የምናሾራቹህ ፍጹም ስልብና አልጫ ሁኑ!” የሚል መልእክት ነው ማስተላለፍ የፈለገው፡፡ ዳንኤል በጥፋት መንገድ እንደፈለጉ የሚያሾሩት ፍጹም ስልብና አልጫ ሳይሆን ቀርቶ አይደለም ከዚያም በላይ ነው ዳንኤል፡፡ መልእክቱ ለዳንኤል ሳይሆን በዳንኤል ስም ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ነው!!!
ዳንኤል ክስረት ለሀገርም ለቤተክርስቲያንም ሳይሆን ለጥቅሙ ብሎ የሀገርንም የቤተክርስቲያንንም ጥቅሞች በተቻለው መጠን ሁሉ ከስር ገልብጦ ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጠላቶች ምቹ መሠረት ለመገንባት ያላደረገው ጥረት፣ ያልቆፈረው ጉድጓድ፣ ያልፈነቀለው ድንጋይ እንዳልነበረ እንደ ዳልኤል ሁሉ የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ጥቅም ለሆዱ ለጥቅሙ አሳልፎ ሰጥቶ ኑሮውን ለመኖር ከሚፈለገው ጭንጋፉ መንጋ በስተቀር አስተዋይ ልቡና ያለው ሁሉ በሚገባ የሚረዳው ሐቅ ነው!!!
በዳንኤል የጥፋት ሥራዎች ዙሪያ “የሀገርና የቤተክርስቲያን ታሪክ ጠላት ስውሩ ተኩላ ዳንኤል ክብረት!” ከሚለው ከአምስት ዓመት በፊት ከጻፍኩት ከዚህ ጽሑፍ
https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/?p=5320
ጀምሮ ለርካሽ ጥቅሙ ሲል በወሰለተ ቁጥር በተደጋጋሚ ጽፌበታለሁ!!!
ዳንኤል ክስረት የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ምሰሶ የሆኑ ጥቅሞችን በመገንደስ ከፀረ ቤተክርስቲያኑና ከፀረ ኢትዮጵያው አላዊ አገዛዝ ሞገስ ለማግኘትና ፍርፋሪ ለመለቃቀም ለማግበስበስ ሲል፦
* አገዛዙ “የኦርቶዶክስን አከርካሪ እንዳያንሠራራ አድርጌ ሰብሬያለሁ!” ብሎ አፉን ሞልቶ እስኪናገር ድረስ የእግዚአብሔር ሳይሆን የዚህ ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ ታማኝ አገልጋይ በመሆን አገዛዙ በቤተክርስቲያን ላይ ይሄንን ጉዳት ማድረስ እንዲችል ያደረጉት የሟቹ የቤተክርስቲያን ቀንደኛ ጠላት የተጋዳላይ አቦይ ጳውሎስ ዋና ጠበቃ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል!!!
* ከጠቢቡ ሰሎሞን ከሚወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ የሚጀምረውና በዚህም ምክንያት ሰሎሞናዊ የሚባለውን ታሪኩ በክብረ ነገሥትና ዜና መዋዕሎች ብቻ ሳይሆን በቤተክርስቲያኗ ጥንታዊ መጻሕፍትም በሚገባ የተሰነደውን ሥርዎ መንግሥት ታሪክ “መረጃ የሌለው ተረት ተረት ነው!” ብሎ “ስማቹህ የለም!” ብሎ ባሳተመው መጽሐፍ ሳያፍር በመጻፍ የአማራን ታሪክ ከኢትዮጵያ ታሪክ ለመፋቅና ቦታ ለማሳጣት በርትቶ ሠርቷል!!!
* በአንጻሩ ደግሞ ቅንጣትም እንኳ “ሰው ምን ይለኛል?” ሳይልና በጭራሽ ኃላፊነትና ተጠያቂነት ሳይሰማው የግራኝ አሕመድን ወረራ በመልካም አጋጣሚነት በመጠቀም የግራኝን እግር ተከትለው ወደ ሀገሪቱ የገቡትንና አሁን ያሉበትን የሀገራችንን ክፍል ከግራኝ የተረፈውን ስንት ነገር አውድመው ወረው የያዙትን ኦሮሞዎችን የቤተክርስቲያኗን መጻሕፍት እስከመቆነጻጸል በመድረስና ከታሪክ መጻሕፍት ፈጽሞ የሚጻረር ፈጠራ በመክተት ኦሮሞዎች ከግራኝ በፊትም አሁን ባሉበት የነበሩ ለማስመሰል እስደመጣር ድረስ በርትቶ ሠርቷል!!!
* የቤተክርስቲያንን እምነትና አስተምህሮ በእጅጉ በሚጻረር መልኩ “የቤተክርስቲያን መጻሕፍት ናቸው!” እያለ በሚጽፋቸው መጻሕፍት ላይ ቤተክርስቲያን የእስላሞችን ነቢይ የመሐመድን ነቢይነት የምታምንና የምትቀበል በማስመሰል ተገርጎ በማያውቅ መልኩ “ነቢዩ መሐመድ!” እያለ በመጻፍ ለእስልምና ጥቅም በርትቶ ሠርቷል!!!
* ይሄንን ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ቤተክርስቲያን አገዛዝ በታማኝነት ለማገልገልም ከዚህ በፊት በፓርላማ ተብየው ፊት ቀርቦ በፀረ ሕዝብ ፀረ ኢትዮጵያ ሕገመንግሥታቸው ምሎ ቃል በመግባት ምን ያህል ታማኝ ሆኖ ሊያገለግላቸው እንደሚፈልግ ቁርጠኝነቱን አሳይቷል!!! ወዘተረፈ.
ደንቆሮው መንጋ ግን እንዴት አድርጎ እንዳሰበው አላውቅም ዳንኤል በዚህ ደረጃ የሀገርንና የቤተክርስቲያንን ጥቅም በእጅጉ በመጻረር ለፍርፋሪ ሲል የሀገርና የቤተክርስቲያንን ጠላቶች ጥቅም ለማስጠበቅ በትጋት ሲሠራ በግላጭ እየታየ የእሱ የቤተመንግሥት አሳላፊ መሆንና መናኛ ቦታ መያዝ ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንደሚኖረው በማሰብ ለዚህ ባንዳና ነቀርሳ ጥብቅና ቆሞ ሲሟገት ይታያል!!!
ሲጀመር መንጋው ጭንቅላት ስለሌለው አያስተውልም እንጅ ዳንኤል ለግል ጥቅሙ ካልሆነ በስተቀር ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጨርሶ እንደማያስብ ከላይ የተገለጹት የባንዳ ሥራዎቹ ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ!!!
ደንቆሮው መንጋ እንደሚመስለው ዳንኤል ለቤተክርስቲያን የሚያስብ የሚቆረቆርና ለቤተክርስቲያን ለመሥራት ቤተመንግሥት የገባ ቢሆን ጳጳሳት ቤተመንግሥት ድረስ ሔደው አገዛዙ በየስፍራው ባለሥልጣናቱ ሥልጣናቸውን አለ አግባብ በመጠቀም በቤተክርስቲያን ላይ ላደረሱት መጠነ ሰፊ ጥቃት ጉዳትና ኪሳራ ይቅርታ እንዲጠይቅ፣ ካሳ እንዲከፍል፣ ወንጀለኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ ወይም ለፍርድ እንዲያቀርብ ሲጠይቁ የወያኔው ኩሊ ዐቢይ አሕመድ ይቅርታ እንደማይጠይቅ፣ ካሳ እንደማይከፍል፣ ማንንም ለፍርድ እንደማያቀርብ በመናገር አበሻቅጦና ሰድቦ ሲመልሳቸው ለቆ በወጣ ነበር!!!
እሱ ግን ዐቢይ አሕመድ አባቶችን እንዲያ እያበሻቀጠና እየሰደበ ሲያዋርዳቸው እዚያው ቆሞ በማየት ጭራሽ እንዲያውም ዐቢይ አባቶችን ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ “…እንግዲያውስ በል ዳንኤል ለእነ እከሌ እንዲህ በልና ደውል!” ሲባል ለመደወል በመጣደፍ አባቶችን እስኪገርማቸው ድረስ የዐቢይ ጨንገር ሆኖ ነበር የዋለው!!!
ደንቆሮው መንጋ ግን ይሄንን አያስብም አያስተውልም!!! የእሱ እዚያ መሆን ቤተክርስቲያንን ከምንም እንዳላዳነ ጭራሽ እንዲያውም ፈተናዋ ተባብሶ ቤተክርስቲያን ለከፋ ፈተና ጉዳትና ኪሳራ ተዳርጋ በየስፍራው እየተደፈረች ስትዋረድና ፍዳ ሲጸናባት በዓይኑ እያየ በጆሮው እየሰማ ይሄው ደንቆሮ መንጋ የራሱን የቤትሥራ ወይም የሚጠበቅበትን ክርስቲያናዊ ግዴታ በመወጣት ቤተክርስቲያንን ከጥፋት እንደመታደግ ዳንኤልን ተስፋ አድርጎ ተኝቷል!!!
አገዛዙም ዳንኤልን ያስጠጋበት ሸፍጠኛ ምክንያት ለዚህ ነው፡፡ ደንቆሮው ዘገምተኛው መንጋ ምንም የማይፈይደውን ዳንኤልን ተስፋ በማድረግ ተንከርፍፎ በመጠበቅ ጊዜውን በከንቱ እንዲገፋ ለማድረግ፡፡ ይሄው ያሰበውም ተሳክቶለት ደንቆሮው መንጋ እጅ እግሩን አጣጥፎ ተቀምጦ “ዳንኤል ዳንኤል!” እያለ በከንቱ ሲቃዥ ይውላል!!!
ማሰብ የሚችል ጭንቅላት ያለው ሰው ከዚህ ከደንቆሮው መንጋ ውጭ ያለ የተዋሕዶ ልጅ ካለ አጥብቄ ላሳስበው የምፈልገው ነገር አለኝ፡፡ ዳንኤል ከፈጸማቸው የታሪክ ቅሰጣዎች እንደምንረዳው ምንም እንኳ ዳንኤል አገዛዙን ጠጋ ጠጋ የሚለው ለሀገርና ለቤተክርስቲያን ጥቅም ባይሆንም ዳንኤል በሔደበት መንገድ ተሒዶ የአገዛዙ ሎሌ በመሆን የሀገርንም ሆነ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ለማስጠበቅ ፈጽሞ እንደማይቻል የዚህን ያህል እራሱን አዋርዶ፣ ከእውነትና ከታሪክ ጋር ክፉኛ ተጣልቶ በፍጹም ታማኝነት ሲፈጋላቸው ከኖረው ከዳንኤል ክስረት ውርደት ተምራቹህ መንገዱ ወያኔ/ኢሕአዴግን ተቀላቅሎ ለውጥ ለማምጣት መሞከር ሳይሆን የዘርና የእምነት ልዩነት ሳያደርግ ለሀገር አንድነትና ህልውና የሚሠራ ተፎካካሪ ፓሪቲ በማቋቋም ወያኔ/ኢሕአዴግን ተፎካክሮ በማሸነፍ ሥልጣን መያዝ መሆኑን አውቃቹህ ለዚህ እንድትተጉ ነው!!!
ዳሩ ለቀጣዩ ምርጫ ካልሆነ በስተቀር ከፊታችን ላለው ምርጫ አትደርሱም፡፡ ምርጫው ካልተራዘመ በስተቀር፡፡ ይሄንን በማሰብ ከዓመታት በፊት ጀምሬ ደጋግሜ ብመክር ባስጠነቅቅ አልሰማ ብላቹህ፣ መንቃት ተስኗቹህ ይሄው ዕድሉን አስመለጣቹህን፡፡ እያንዳንድሽ ዛሬ ዕድሉ ካመለጠ በኋላ “ነቃሁ!” ብለሽ በየሚዲያው እየቀረብሽ መፍትሔው ይሄ መሆኑን ትናገሪያለሽ፡፡ አየ የእናንተ ነገር፡፡ ብቻ እግዚአብሔር ይፋረዳቹህ ነው ሌላም የምለው ነገር የለኝ!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው