የታፈኑ ወይም የተጠለፉ ወገኖቻችንን በሚገባ ጉዳየ ብሎ የሚጮህላቸው አቋጣሪ፣ ተሟጋች፣ አሳቢ ቁርጠኛ የሆነ ድርጅት፣ ፓሪቲ ወይም ተቋም ያጡ ተጠላፊ ወገኖቻችን ከታፈኑ ወይም ከተጠለፉ መቶ ቀናት አለፋቸው!!!
እነኝህን የግፍና የጭካኔ ሰለባ ተማሪዎች ማን ያስፈታቸው ትላላቹህ??? በሕይዎት ካሉ ማለቴ ነው፡፡ ብአዴን? አብን? የአማራ ሕዝብ? ወይስ ሌላ ማን ያስፈታቸዋል ብላቹህ ታስባላቹህ???
ፀረ አማራው ብአዴን ተማሪዎችን ለፖለቲካ ቁማር ያሳፈናቸው የግፍ አገዛዙ አካል በመሆኑ የችግሩ አካል ነውና የመፍትሔ አካል ሊሆን አይችልም፡፡ አብንም ጉዳየ ሊላቸው እንዳልቻለና እንደማይችልም እያያቹህት ነው፡፡ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በዝርዝር እናየዋለን፡፡ የአማራ ሕዝብ ደግሞ በአገዛዙ ላይም ሆነ በሌላ ፀረ አማራ የጥፋት ኃይል ላይ ጫናና ተጽዕኖ ማሳደር በሚችልበት አቋም ደረጃ የሚያታግለው አካል ባለማግኘቱ እንደምታዩት አቅም እያለው አቅመቢስ ሆኖ መጫወቻ ሆኗል፡፡ ታዲያ ልጆቹን ማን ያስፈታቸው??? ማን ይድረስላቸው??? ባጠቃላይ በአማራ ላይ ሆን ተብሎ የሚፈጸሙ ግፍ፣ ሰቆቃና ጥቃቶችን ማን ያስቁማቸው???
እነኝህ የታፈኑ ተማሪዎች እንዲህ አቋጣሪ፣ ተሟጋች፣ አሳቢ አካል ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያጡበት ምክንያትስ ምን ይመስላቹሃል??? ሌላ ምንም ሳይሆን አማራ መሆናቸው ነው!!! ይሄኔ ትግሬ ወይም ኦሮሞ ቢሆኑ ሌላ ተአምር በተፈጠረ ነበረ!!!
እጅግ የሚገርመኝ ነገር “ለአማራ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብትና ጥቅም በቁርጠኝነት እንታገላለን!” የሚሉ በአማራ ስም የሚንቀሳቀሱ ቅጥረኛ፣ አስመሳይና ነጋዴ ድርጅቶች “ለአማራ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብትና ጥቅም በቁርጠኝነት እንታገላለን!” እንደማለታቸው ጥግ ድረስ የደረሰ አይደለም እዚህ ግባ የሚባል ጥረት፣ ጫናና ተጽእኖ አለማድረጋቸው እየታየ ዘገምተኛው መንጋ ለአማራ የቆሙ ድርጅቶች አድርጎ ሲመለከታቸው መታየቱ ነው ትንግርቱ!!!
“ለአማራ ሕዝብ ቆመናል!” የሚሉ እነኝህ አስመሳይና ቅጥረኛ ድርጅቶች ወሬና ማስመሰል ላይ እንጅ ተግባር ላይ ጨርሶ የሌሉ በመሆናቸው ለአማራ በጭንቁ ጊዜ ሊደርሱ አልቻሉም አይችሉምም!!! ይሄኔ የትግሬና የኦሮሞ ፓርቲዎች ቢሆኑ ሀገሪቱን ቀውጢ ባደረጓት ነበር!!!
ለእንዲህ ዓይነቱ የአማራ ጥቃት፣ መደፈርና መዋረድ የማይደርስ፣ የማይቆም፣ ከፊት ተሰልፎ የማይታገልና የአማራን ሕዝብ የማያታግል “የአማራ ፓርቲ ነኝ!” ባይ ድርጅት መቸና የት ለአማራ ሊደርስ፣ ሊቆምና ሊታገል እንደሚችልና እንዴትስ የአማራ ድርጅት ተደርጎ ሊታሰብ እንደሚችል ይሄ ዘገምተኛው መንጋ እንዲነግረኝ እወዳለሁ!!!
ለምሳሌ አብንን ብንወስድ አብን “በአማራ ላይ የሚፈጸሙ ግፍና ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የታሰሩት በአስቸኳይ እንዲፈቱ ለማድረግ ለየካቲት 22 አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቻለሁ!” ብሎ ነበር፡፡ በኋላ ቀኑ ሲደርስ ደግሞ “አባላቶቸ ተፈትተዋልና ሰልፉ ተሰርዟል!” ብሎ መሰረዙ ይታወሳል!!!
በዚህ እጅግ አሳፋሪና አስገራሚ ተግባሩም “እታገልለታለሁ!” ከሚለው የአማራ ሕዝብ ደኅንነት፣ ህልውና፣ መብት፣ ነጻነትና ጥቅም ይልቅ የአባላቱ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ጥቅም፣ ነጻነትና መብት እንደሚበልጥበትና አማራን በስሙ የሚጠቀምበት አሻንጉሊቱ ወይም ደግሞ እንዳያስቸግር አታሎ አስሮ እንዲይዘው የጠሰጠው መንጋ እንጅ የምር እንደሚያወራው ለአማራ መብት፣ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ ጥቅም እስከ ሞት ድረስ ታምኖ የሚታገልለት ሕዝብ አለመሆኑን በይፋ አሳየ አረጋገጠ!!!
የአንድ እውነተኛ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችና አባላት “እንታገልለታለን!” ለሚሉት ሕዝብ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብትና ጥቅም ይኖራሉ፣ ይታገላሉ፣ ይፋለማሉ፣ ይዋደቃሉ፣ ይሠዋሉ እንጅ በግልባጩ ፈጽሞ “እንታገልለታለን!” የሚሉት ሕዝብ ለእነርሱ ጥቅም፣ መብት፣ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ነጻነት … እንዲኖር፣ እንዲታገል፣ እንዲፋለም፣ እንዲዋደቅ፣ እንዲሠዋ አያደርጉም አይፈልጉምም!!!
እውነተኛ የሕዝብ ታጋዮች ጥቅማቸው፣ መብታቸው፣ ህልውናቸው፣ ደኅንነታቸውና ነጻነታቸው እንዲጠበቅላቸው፣ እንዲከበርላቸው፣ እንዲያገኙ የሚፈልጉት የሚታገሉለት ሕዝብ መብት፣ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነትና ጥቅም ከመጠበቁ፣ ከመከበሩ፣ ከማግኘቱ ብቻ ነው!!!
አብኖች አማራን መጠቀሚያ ማድረግ እንጅ ለአማራ ማለፍና መሠዋት ስለማይፈልጉ ሕዝቡ ለእነሱ እንዲያልፍላቸው እንዲሠዋላቸው እንጅ እነሱ ለሕዝብ ማለፍ መሠዋት አይፈልጉም!!! ለዚህም ነው አማራ ተማሪ ልጆቹ መጠለፋቸውና የአዋራጅ ቅስም ሰባሪ ግፍና ጥቃት ሰለባ በመሆናቸው አጥንት ሰባሪ አንገት አስደፊ ውርደት ደርሶበት እያለ ይሄ ሳይታያቸው የአባላቶቻቸው ጉዳይ ብቻ የታያቸውና “አባላትቶቻችን ተፈትተዋልና ሰልፉን ሰርዘነዋል!” ሊሉ የቻሉት!!!
አንድ ለሕዝብ የሚታገል ታማኝ ድርጅት ግን እንዴት ነው የሚያስበው መሰላቹህ ትግል ውስጥ እስከገባ ጊዜ ድረስ የአመራሮቹና አባላቱ መታሰር መሠዋት የሚጠበቅ በመሆኑ ይህ በሚደርስ ጊዜ ለሕዝብ ህልውና፣ ደኅንነት፣ ነጻነት፣ መብትና ጥቅም ሲባል የተከፈለና የግድም የሚከፈል ዋጋ እንደሆነ ይቆጠራል እንጅ እንደ አብኖች ሕዝቡ ላይ ግፍ ሰቆቃና ፍዳ እየተፈጸመ እያለ ይሄንን ወደጎን ትቶ “ታሰሩብኝ!” በሚላቸው አባላቱ ላይ አተኩሮ ወይም ቅድሚያ ሰጥቶ አይንቀሳቀስም!!! ቀድሞውኑ ወደ ትግሉ የገቡት ለሕዝብ ሲሉ ሊታሰሩና ሊሠው አይደለም ወይ???
አንድ ድርጅት “እታገልለታለሁ!” ከሚለው ሕዝብ ይልቅ ለአባላቱ የላቀ ትኩረትና ቅድሚያ ሰጥቶ ከተገኘ “ለሕዝብ እታገላለሁ!” ማለቱ የውሸት ወይም የሽፋን ነው፡፡ ዓላማውም ሕዝብን መረማመጃ፣ መጠቀሚያ ወይም ሽፋን አድርጎ ለሥልጣን በመብቃት ወይም የቀጠረውን አካል በማገልገል የየግል ጥቅምን ማስጠበቅ ነው ማለት ነው!!!
አብን ላይ እየታየ ያለው ጉዳይም በትክክል ይሄው ነው፡፡ አብኖች ለሕዝብ ብለው ዋጋ መክፈል ወይም መሠዋት አይደለም መጋፈጥ እንኳ ፈጽሞ አይፈልጉም፡፡ ይሄንን ጉዳቸውን በተለይ በሰኔ 15 እና ከዚያ በኋላ በነበረው ጊዜ በሚገባ ተጋልጦ ታይቷል፡፡ ሰኔ 15ን በተመለከተ ዝም ቢሉ እንኳ በተሻለ ነበር፡፡ እነሱ ግን ከጀግኖቻችንና ከትግላችን ገዳዮች ጎን ቆመው ነው ለግፈኛው አገዛዝና ለግፍ እርምጃው ድጋፋቸውን ሲሰጡ የነበሩት!!!
በዚያ ፀረ የአማራ ብሔርተኝነት ትግል ዘመቻ ሕዝቡ በቁጣ ተነሣሥቶ የአጸፋ እርምጃ እንዳይወስድ ሕዝቡን በማረጋጋትና ከዚያም አልፈው በተወሰደው የፀረ አማራ ብሔርተኝነት ትግል ዘመቻ ወይም የግፍ እርምጃው ላይ ሕዝቡ አገዛዙን እንዲተባበር ለማድረግ ዋነኛውን ሚና የተጫወተው አብን ነበር!!! በዚያ ወቅት ብአዴን ለእንዲህ ዓይነት የጭንቅ ቀን እንዲሆኑት በስውር ያቋቋማቸው አብንና ዐሥራት ሚዲያ ባይኖሩ ኖሮ አገዛዙ ጉዱ ፈልቶበት ነበር፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ብአዴኖችንና የብአዴንን ሚዲያ አይሰማም አይቀበልም ነበርና!!!
አሁን ታዲያ አብን የአማራ ጠላት ነው ወይስ አለኝታ ነው??? አብኖች የአማራን ሕዝብ ለመደለል ለማጃጃል ሲነፉት እንደከረሙት ፕሮፖጋንዳ ቢሆን ኖሮ ሰኔ 15 ላይ “ዘራፍ ወንዱ!” እያሉ በመፋለም አንድ ሞያ ሠርተው በመገኘት የሚቀድማቸው ባልተገኘ ነበር፡፡ ማስመሰልና ተግባር፣ ቅጥረኝነት ወይም ባንዳነትና ታጋይነት ለየቅል ሆነው እንዲህ ዓይነት ሞያ ላይ ሊገኙ ሳይችሉ ቀሩ እንጅ!!!
አብንን ለአማራ ሕዝብ የቆመና የሚታገል አስመስሎ በማቅረብ በብአዴን ካድሬዎች እንዲመሠረት የተደረገበት ዓላማም ይሄው ነው፡፡ የአማራን ትግል እንዲጠልፍና በእንዲህ ዓይነቱ የአገዛዙ ፀረ አማራ ዘመቻ ወቅትም ሕዝብን በማዘናጋት፣ በማረጋጋትና በመያዝ ሊከሰት የሚችልን ሕዝባዊ ቁጣን ወይም ዐመፅን እንዲያስቀር እንዲያከሽፍ ታስቦ ነው!!! ይሄው በታሰበው መሠረትም ተልእኮውን በሚገባ እየተወጣ ይገኛል!!! እጅግ የሚገርመው ነገር ዘገምተኛው መንጋ ይሄ ሁሉና ሌላ ብዙ ነገር ሲሆን እያየ አለመንቃቱ ነው!!!
አሁንማ ጭራሽ “አማራ የህልውና አደጋ የለበትም!” እያሉ የአማራን ትግል ወደኋላ ለመመለስ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ትግል መጥለፍ ይሉሃል ይሄ ነው፡፡ ጠላፊ የሚያደርገው ምንድን ነው??? መሀል ላይ ተቀላቅሎ እስከተወሰነ እርቀት ድረስ ተመሳስሎ አብሮ ይጓዝና የሆነ ቦታ ላይ አቅጣጫ አስቶ መውሰድ ነው፡፡ አብኖች በፊት የእኛን ጩኸት በመንጠቅ አማራ የህልውና አደጋ ላይ ያለና በጠላት የተከበበ እንደሆነ እየሰበኩ የአማራን ትግል ከእኛ እጅ ነጥቀው በቁጥጥራቸው ስር ካደረጉ በኋላ ዛሬ አማራ በአማራነቱ ብቻ የትም በማንም እየተደፋ፣ እየተገደለ፣ እየተጨፈጨፈና በዙሪያው ባሉ የጥፋት ኃይሎች እየተዛተበት እያዩ “አማራ የህልውና አደጋ የለበትም፣ አማራ በጠላት የተከበበ እንደሆነ የሚነገረው ነገር ስሕተት ነው…!” እያሉ በአማራ ፍዳ መከራና አሳር ላይ አሿፊ ሆነው ቁጭ ብለዋል!!!
እናም አማራ እንደ ትግሬና ኦሮሞ የመሳሰሉት የሚሟገትለት የሚቀድምለት የሚታገልለት የሚፈራ አካል ባለመኖሩ ይሄው በምናየው መልኩ ዛሬም እንደትናንቱ ሁሉ እንዲያውም ከዚያም በከፋ መልኩ እየተጠቃ፣ እየተዋረደ፣ እየተደፈረ፣ እየተፈጀ ይገኛል!!!
እናንተ የተጠለፉት ተማሪዎች መቶ ቀናት በማስቆጠራቸው ይገርማቹሃል አይደል??? ገና ለዓመታት የት እንዳደረሳቸው ሳያሳውቅ ቤተሰብንና ዘመድ አዝማድን በሰቀቀን ይገላቸዋል፡፡ ማንን ፈርቶ??? እነ መርጌታ እንደሥራቸው አግማሴንና በተለያየ ዘመን እያፈነ የወሰዳቸውን ወገኖቻችንን ያደረጋቸውን አልሰማቹህም እንዴ??? አፍኖ ወስዶ ደብዛ ማጥፋት ለዚህ አረመኔ አገዛዝ አዲስ አይደለም!!!
የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ጭራሽ “ጠፉብን!” እያሉ በየስፍራው የሚያለቅሱ የቤተሰብ አባላትን “ለቤተሰብ አባሎቻቹህ ለምን ትጮሁላቹሃላቹህ!” ብሎ በግፍ በማሰር ወላጆቻቸውን ለተጨማሪ ሐዘንና ጭንቀት የሚዳርግ እጅግ ጉደኛ፣ ነውረኛ፣ ወራዳ፣ ቆሻሻ፣ አረመኔ፣ ወንበዴ አገዛዝ ነው አገዛዙ!!!
ታዲያ እንግዲህ ለእነኝህ የግፍ ሰለባ ወገኖቻችን ማን ይድረስላቸው??? ማን ይጩህላቸው??? ሕዝቡ በየከተማው ሰልፍ ወጥቶ ጮኸ ግን ምን ለውጥ አመጣ??? ምንም!!! ለምን ይመስላቹሃል??? አገዛዙ ወይም ወያኔ/ኢሕአዴግ በእነ አብንና “የአማራ ወጣቶች ማኅበር በምንንትስ!” እያለ ባቋቋማቸው ቅጥረኛ ወጣት ማኅበራቱ ከመተማመኑ በተጨማሪ አማራ ከዚህ የዘለለ ምንም ነገር ሊያደርግ እንደማይችል ልቡን ሰልሎ ስላወቀው ነው!!!
በሰኔ 15ቱ ፀረ የአማራ ብሔርተኝነት ትግል የግፍ ዘመቻ አማራ ሆ ብሎ ተነሥቶ የቻለውን ያህል ቢዋደቅ ኖሮ ሙሉ ነጻነቱን መቀዳጀት ባይችል እንኳ ሌላው ሁሉ ቢቀር ከዚያ በኋላ አገዛዙም ሆነ ማንም እንዲህ እንደፈለጉ መጫወቻ ከማድረግ ይቆጠቡና ይፈሩት ነበር፡፡ አማራም እራሱን አስከብሮ ተፈርቶ መኖር ይችል ነበር!!!
እብድ እንኳ የሚፈራው ለምን ይመስላቹሃል??? አማራ ይሄንን መረዳት ይኖርበታል!!! ካልሆነ በየተራ እየለቀሙ ይጨርሱሃል እንጅ መቸም ቢሆን ሊፈሩህና ሊያከብሩህ አይችሉም!!! እስክታልቅ ድረስ ዛሬም ሆነ ነገ እንደትናንትናው ሁሉ ውርደትህን እንደተከናነብክና አንገትህን እንደሰበርክ ትቀጥላለህ!!!
አሁን ጥያቄው ወገኖቻችንን ማን ያስለቅቃቸው??? እንዴት ይለቀቁ??? ይሄንን ጥያቄ እያንዳንዱ አማራ ለየራሱ በሚገባ ካልመለሰ ተማሪዎቹ እንደእነ መርጌታ እንደሥራቸው አግማሴ ደብዛቸው ጠፍቶ መቅረቱ አይቀርም፡፡ እነሱ ብቻ ሳይሆኑ ሌላም ባለተራ አማራ ደብዛው እየጠፋ መቅረቱና የትም መደፋቱ አይቀርም!!!
አማራ ሆይ ይሄንን ጥያቄ ነገ ሳይሆን ዛሬ በአግባቡ መልስ!!!
መልሱ ከወያኔ/ኦሕዴድ አህዮችና ባንዶች ከፀረ አማራዎቹ ብአዴንና አብን ነጻ ሆነህ ተደራጅና በቁርጠኝነት መታገል መፋለም ብቻ ነው!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው