ግብጽ ዝናብና ፈጣሪ!!!
በግብጽ ሀገር እንደብዙ ሀገራት ዝናብ በየዓመቱ አይዘንብም፡፡ ከስንት ዓመታት አንድ ጊዜ ነው የሚዘንበው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እንዲያውም የዝናብን ምንነትና ተፈጥሮ ጨርሶ ሳያይ የሚያልፍ ትፍልድ አለ፡፡ አንዳንዴም እስከ አምስት መቶ ዓመት ድረስ ላይዘንብ ይችላል!!!
እንዲህ ዓይነት የዝናብ ሽፋን ያላት ግብጽ በቀደምለት ውሽንፍር የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ዘንቦ ነበር፡፡ በዝናቡ ምክንያት የአምስት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን ከአምስት ያላነሱ ሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታውቀው ነበር!!!
ፈጣሪ በዚህ ግብጾች “ዓባይ የእኛ ብቻ ነው አትነኩብንም!” በሚለው ለዘመናት የጸና ኢፍትሐዊ አቋማቸው ምክንያት ከእኛ ጋር የተካረረ ውዝግብ ውስጥ በገባንበት ሰዓት የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የባቡር አገልግሎቶችን፣ የመርከብ እና የአውሮፕላን ማረፊያ እና ዋና የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ለመዝጋት እስኪገደዱ፣ በአገሪቱ የመብራት አገልግሎት እስኪቋረጥ ድረስ ውሽንፍር የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ማዝነቡ መልእክቱ ምን ይሆን???
እኔ ለበጎ አይመስለኝም!!!
ምክንያቱም ፈጣሪ ግብጾች ዓባይን ለብቻቸው ለመጠቀም “ወንዙን የኛ ነው!” በማለታቸው ምክንያት ተቆጥቶ ከግብጽ ምድር በሚያጠፋቸውና በስደት በዓለም በሚበትናቸው መዓቱ እንደሚቀጣቸውና ግብጽን የሚደግፉም እንደሚወድቁ የእግዚአብሔር ቃል በትን. ሕዝ. 29፤1-21 እና 30፤1-9 ተናግሯልና ነው!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው!