*************
ሀብታሙ ግርማ ደምሴ
(Habtamu Girma Demiessie)፣
መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም
ድሬዳዋ፣ኢትዮጵያ
**************
የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ማድረግ ብንችል መልካም ነበር። ነገር ግን አለም የመንደር ያህል በጠበበችበት ዛሬ (አየር መንገድን መውቀስ አይቻልም!) ይህ የሚቻል አይደለምና በአገራችን የመጀመሪያው የቫይረሱ ተጠቂ ተገኝቷል።
ከዚህ በኋላ እንዴት የዚህን በሽታ መስፋፋት መግታት ይቻላል የሚለው ላይ ማተኮር ነው የሚያሻው፤ ለዚህ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማድረግ ስላለበት ነገር ጥቂት ልበል፦
***** በቅድሚያ ራሳችንን በጦርነት ላይ እንዳለን ማሳመን፣
***** የውጊያው ስንቅ የሚሆነው የውጊያ መንፈስ ነው፤ እናም ለዘመቻው መዘጋጀት፤ ይህም ሲባል ከመደንገጥ እና ከመረበሽ ይልቅ በወኔ እና በአገር ፍቅር ስሜት ለውጊያው ራስን ማዘጋጀት
****** የውጊያው ዋነኛ ትጥቅ ስለበሽታው አጠቃላይ ግንዛቤ መጨበጥ፣ ማስጨበጥ እና ማስረጽ ነው
******* የውጊያው መሪ ሁሉም ነብስ ያወቀ ኢትዮጵያዊ ይሆናል፤
****** የውጊያው ስልት የአልሸነፍ ባይነት ወኔ እና እምነት ናቸው። ከታሪካችን ማህደር እንደምናገኘው አባቶቻችን በአውደ ውጊያዎቻቸው እንዳደረጉት በእጃቸው ጦር እና ጋሻ፣ በልቦናቸው ደግሞ የፈጣሪን ተራዳኢነት ይዘው ነበር። ኮሮናን ለመግጠም ስንዘጋጅ እኛም ተመሳሳይ ስልት መከተል አለብን።
****** ስለሆነም፣ ዝቅ ሲል ራስን እየተከላከሉ የበሽታውን መስፋፋት መከላከል፣ከፍ ሲል ስርጭቱን ለመግታት ማጥቃት ነው፤ ኢትዮጵያዊያን ጦርነት ላይ እጅ መስጠት ታሪካችን አይደለምና ኮሮናን በመዋጋት ሂደት የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀት ያሻል፤ ሞቶ ሌሎችን ለማዳን የመንፈስ ዝግጁነት ይጠይቃል
***** ከዚህ በመለስ ሁሉን ለፈጣሪ መተው፣ መልካም ማሰብ፣ መልካም ማድረግ መፍትሄ ነው!
**********
ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአገር ፍቅር እና ህዝባዊ መንፈስ ኮሮናን ለመግጠም ወደፊት!