ዋነኛው የአማራ ጠላት ብአዴን የሚሉት የወያኔ/ኦህዴድ አህያና ባንዳ የጥፋት ኃይል ቀደም ባለው ጊዜ አገዛዙ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ግፍ ተቃውሞ ከጓዶቹ ጋር በረሃ በመግባት አገዛዙን ሲፋለም የኖረውን የአማራ ሕዝብ ባለውለታ አርበኛ መሳፍንትንና ጓዶቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ዛሬ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በመሞከሩ ዳባት ላይ ከፍተኛ ውጊያ ተከፍቷል!!!

ከዚህ ጋር በተያያዘ ጎንደር ላይ ሦስት ሰዎች በጥይት ተመትተዋል!!!

ብአዴን ባለፈው ሳምንት ባሕርዳር ላይ ከአብንና ከአማራ ምሁራን ማኅበር ተብየው ጋር የተለያዩ አካላት የጋራ ግብና ራእይ እንዲኖራቸው ለማድረግ!” በሚል ዓላማ ጉባኤ አማራ የምክክር መድረክ!” በሚል ሥያሜ በጋራ ባዘጋጁት ጉባኤ ላይ አቶ ገዱ በንግግሩ ኢመደበኛ አደረጃጀት!” ሲል የፈረጀውን ፋኖን ማስወገድ እንደሚገባ መዛቱ ይታወሳል!!! ጉባኤው ሲጠናቀቅም እነኝሁ ብአዴን አብንና የአማራ ምሁራን ማኅበር የተባሉ የጠላት ቅጥረኞች የጋራ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል!!!

በተለይ ከጉባኤው በኋላ ዛሬ መውሰድ የጀመሩትን የኃይል እርምጃ ለመውሰድ እንዲመቻቸው ታጣቂ ኃይላቸውን በየስፍራው አሰማርተው በፋኖ ስም ወንጀሎችን በመፈጸም ፋኖን በሕዝብ ለማስጠላት ሰፊ ሴረኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ መሰንበታቸው ይታወቃል!!!

ይሄው ዛሬ ደግሞ በተገመተው መሠረት ፋኖን በመመንጠር የአማራን ትግል ዘሩን በማጥፋት ጨርሶ እንዳያንሰራራ አድርጎ ለመምታት ለማክሰምና ለማምከን የመጨረሻውን እርምጃ በመውሰድ ላይ ናቸው!!!

ወገን ይታያቹህ ይሰማቹህ! ጠላቶቻችን ቀረጣጥፈው ሊበሉን ዙሪያችን ከበው ዝግጅታቸውን ያጧጡፉታል ብአዴን አብንና የአማራ ምሁራን ማኅበር የተባሉ የወያኔ/ኦሕዴድ ባንዶችና ቅጥረኞች ደግሞ ባለፈው ሳምንት በመከሩትና በተስማሙት መሠረት አማራ አንድም መካችና ተከላካይ እንዳይኖረው ፋኖዎቻችንንና አርበኞቻችንን አጽድተው ለመቆየት ይሄው በአርበኞችህና በፋኖዎችህ ላይ ዘምተዋል!!!

ኧረ እባክህ ወገን ተው ንቃና ተነሥ ተው??? ጀግኖችህን በሙሉ አስፈጅተህ ምን ለመሆን ነው ዝም ብለህ የምትመለከተው??? ለምንስ ይመስልሃል ጀግኖችህን፣ መከታዎችህን፣ ጋሻዎችህን ከያሉበት መንጥረው ማጥፋት የፈለጉት??? እንዴት ይሄንን መረዳት ይሳንሃል??? ነው ወይስ ጀግኖችህን አስፈጅተህ አንተንም ጨርሰው እስኪያጠፉህ ድረስ እንደፈለጉት የሚያደርጉህ ባሪያቸው ሆነህ መኖርን መረጥክ???

ኧረ ምንድን ነው ጉዱ??? ምን ዓይነት አዚም ነው ግን ያደረጉብህ???

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው