የፀረ አማራው ቅጥረኛ የጥፋት ኃይል ብአዴን ባለሥልጣናትና አንዳንድ ያገዛዙ ቅጥረኞች በሀገሪቱ ከመንግሥት ውጭ የታጠቀ ኃይል ሊኖር አይችልም አይገባምና ጎንደር በፋኖና አርበኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ትክክል ነው!” ሲሉ ተደምጠዋል!!!

ሲጀመር ከጥንት ጀምሮ እስከ አሁንም ፋኖም ሆነ አርበኛ ሕገወጥም ኢመደበኛም የሆነ ታጣቂ ኃይልና አደረጃጀት አይደለም!!!

አገዛዙ ፋኖንም ሆነ አርበኞችን በእኔ ቁጥጥር ስር ካልሆናቹህ!” ካላለ በስተቀር ፋኖም ሆነ አርበኛ ፈረንጆቹ ሚሊሺያ (militia) የሚሉት አደረጃጀት ነው እንጅ ሕገወጥም ኢመደበኛም አደረጃጀት አይደለም!!!

የፋኖ/አርበኛ አደረጃጀት በአገዛዙ ቁጥጥር ስር ይሁን!” እንዳይባል ደግሞ በፋኖ/አርበኛ እና በአገዛዙ መሀከል ከፍተኛና በግልጽ የሚታይ ሊታረቅም የማይችል የዓላማና የጥቅም ግጭትና ልዩነት ስላለ ፈጽሞ ሊሆን አይችልም!!!

ይሄ የፋኖ/አርበኛ አደረጃጀት ሀገሪቱ በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ዘመናዊ ውትድርና እስከጀመረችበት ጊዜ ድረስ ከጥንት ጀምሮ ሀገሪቱን ከጠላትና ከወራሪ ጠብቆ ነጻነቷን፣ ሉዓላዊነቷን፣ ክብሯን፣ ደኅንነቷን፣ ህልውናዋን ወዘተረፈ. አስጠብቆ የኖረ የጀርባ አጥንት አደረጃጀት ነው!!! ጠላት ካልሆነ በስተቀር ይሄንን የሀገር ባለውለታ አደረጃጀት ሕገወጥና ኢመደበኛ አደረጃጀት!” ብሎ ሊፈርጅና ሊያስወግድ አይችልም!!! የፋኖ/አርበኛን ኃይል እንደ ኦነግ ካሉ ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ ሕዝብ የጥፋት ኃይሎች ጋር አንድ አድርጎ ማየት ድንቁርና ብቻ ሳይሆን ቅጥረኝነትና የሀገር ጠላትነትም ነው!!!

አማራ በዚህ ባሕላዊ አደረጃጀት ለሽዎች ዘመናት የሀገርን ዳር ድንበር፣ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ነጻነት፣ መብትና ጥቅም ሲጠብቅ የኖረ እንደመሆኑ ፋኖነትና አርበኝነት ከደሙ የተዋሐደው ባሕሉ ነው!!!

እውነቱ ይሄ ሆኖ እያለ ፋኖንና አርበኛን ሕገወጥና ኢመደበኛ!” በማለት በቁጥጥር ስር ለማዋል፣ ትጥቅ ለማስፈታት፣ ካልሆነም ለማጥፋት የሚደረገው ጥረት አማራን የማጥፋት ዘመቻ አካል ካልሆነ በስተቀር ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም!!!

አማራ የሀገር ዘብ ሆኖ እንደመኖሩና የዚህች ሀገር ባለአደራ እንደመሆኑ ፋኖነትና አርበኝነት በደሙ የተዋሐደው ባሕሉ መሆኑ ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ለማንም ሥጋት ሆኖም አይደለም፡፡ ስለሆነም በገዛ ሕገመንግሥታቸው ሕገወጥ የሆነውን የልዩ ኃይል አደረጃጀት ሕጋዊ አድርገው ፋኖንና አርበኛን ሕገወጥና ኢመደበኛ!” ሊሉ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ መሠረት የላቸውም!!!

በተለይም ደግሞ አማራ በዚህ ወቅት ከፋኖነትና አርበኝነት ሊለይ ሊነጠል የማይችልበት ሌላ ወቅታዊና አንገብጋቢ ምክንያት አለ፡፡ እሱም እንደምታውቁት ዙሪያውን የከበቡትና ጠላት አድርገው ጥርሳቸውን የነከሱበት የጥፋት ኃይሎች በግልጽ በአደባባይ እንደሚያጠፉት እየዛቱበትና ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉበት ያሉ መሆናቸው ነው!!!

አማራ እንዲህ ዓይነት ግልጽና ወቅታዊ አደጋ ተጋርጦበት እያለ ፋኖንና አርበኛን ሕገወጥና ኢመደበኛ አደረጃጀት!” በሚል ሐሰተኛ ፍረጃ ፈርጆ ለማጥፋት መነሣት ዓለማው ምን እንደሆነ የሚጠፋው ሰው የሚኖር አይመስለኝም!!!

ፋኖና አርበኛ ከዚህ ትውፊታዊ አመጣጡና አቋሙ በተጨማሪም አገዛዙ ሕጋዊ አደረጃጀት!” የሚለው በአገዛዙ መዋቅር የተካተተ ማለቱ ከሆነ ጀግናው ጄኔራል አሳምነው ጽጌ ነፍሱን ይማረውና ፋኖ/አርበኛን የአማራ ክልል በሚሉት የጸጥታ መዋቅር አደረጃጀት አዋቅሮ በካምፕ እንዲከትና እንዲሠለጥን አድርጎት አካባቢያቸውን ከፀረ ሰላም የጥፋት ኃይሎች እንዲጠብቁ አድርጎት የነበረ የሰላምና ደኅንነት ዋስትና ሆኖ እየሠራ የነበረ ሕጋዊ ኃይል ነው!!!

አሁን ያለውን የብአዴንንና የፋኖ/አርበኞችን አለመግባባት የፈጠረው ፋኖ/አርበኛ የሀገርንና የተገፋውን አማራን ሕዝብ መብት፣ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ነጻነት፣ ጥቅም ለማስጠበቅ ሲፈልግ ፀረ አማራው የወያኔ/ኦሕዴድ ቀኝ እጅ ብአዴን ደግሞ የአማራን ጠላቶች መብት፣ ደኅንነት፣ ህልውና፣ ነጻነትና ጥቅም ለማስጠበቅ የሚፈልግና እየተንቀሳቀሰም መሆኑ ነው ልዩነቱን፣ አለመግባባቱን፣ የዓላማ መጣረሱንና የጥቅም ግጭቱን የፈጠረው!!!

ፋኖ በያለበት አካባቢ የየአካባቢው ሰላም ዋስትና መሆኑ ነው ፀረ አማራ የጥፋት ኃይሎች ፋኖ/አርበኛን ሕገወጥ ኢመደበኛ አደረጃጀት!” በሚል ፈርጀው ሊያጠፉትና አማራን በግላጭ ለማግኘት የፈለጉት!!!

ለአማራ ኢመደበኛ አደረጃጀት ተብሎ የተፈረጀው አደረጃጀት ለትግሬ ሲሆን ግን መደበኛና ሕጋዊ ነው፡፡ ወያኔ የትግሬን ገበሬ አስታጥቆ ጨርሶ ከዚያም አልፎ ለአቅመ አዳም ያልደረሱ ሕፃናትንና ሴቶችን ሳይቀር ሲያስታጥቅ አስታጥቆም በግልጽ በአደባባይ ፀረ አማራ የሆነ መርዘኛ ስብከት እየጋተ ጦር በአማራ ላይ ሲያሰልፍ ሕጋዊና መደበኛ ነው!!!

ኦሕዴድ የአገዛዙ ሕገመንግሥት የማይፈቅደውን ከሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊትና ከከተማ ፖሊስ ውጭ ጦር የማደራጀትን ተግባር ከሀገሪቱ ጦር ባልተናነሰ ቁጥር በ30 ዙር የልዩ ኃይል ጦር አሠልጥኖ አመራሮቹ ነፍጠኛን ሰብረነዋል፣ ከፊንፊኔ እናባረዋለን….!” እያሉ በግልጽ በአደባባይ በሚዝቱበት አማራ ላይ ያሰቡትን ጥቃት ለመፈጸም ሲያዘጋጅና ሲያደራጅ ፋኖን መጥፋት ያለበት ኢመደበኛ አደረጃጀት!” የሚሉት አህዮቹ የብአዴን ባለሥልጣናት የዚህ የኦሕዴድ ጦር ኢመደበኛና ኢሕገመንግሥታዊ አደረጃጀትነት አይታያቸውም!!! ሌሎች አማራን ከበው ጦር እያደራጁ ያሉ ክልል ተብየዎችም እንደዚያው!!!

ስለሆነም ጉዳዩ ፈጽሞ ሕግን የማስከበር ጉዳይ አይደለም!!! አማራ ላይ ብቻ ተለይቶ የሚሠራ ሕግ ሊኖር አይችልምና!!! ሕግ ከተባለ ሁሉም ላይ መሥራት አለበት!!! ትግሬ ውጫጩ ሳይቀር አማራን ትወጋለህ!” እየተባለ እስከ አፍንጫው ታጥቆ፡፡ ኦሮሞ ነፍጠኛን ትሰብራለህ ታባራለህ!” እየተባለ ከሀገሪቱ ሠራዊት በላይ ሠራዊት አስታጥቆ፡፡ ሌላውም እንደዚያው በአማራ ላይ ታጥቆ፡፡ አማራ ብቻ ትጥቅ ካልፈታህ!” የሚባል ሕጋዊ አሠራር ፈጽሞ ሊኖር አይችልም!!!

አህዮቹ የብአዴን ባለሥልጣናት ይሄ ጠፍቷቸው አይደለም፡፡ ፀረ አማራ የወያኔ/ኦሕዴድ ቅጥረኞች ስለሆኑና አማራን እናጠፋለን!” እያሉ ዙሪያውን ከበው እየዛቱበት ያሉት ጠላቶቹ እስኪዘምቱበት ድረስ አማራን መከታና ትጥቅ አልባ አድርገው እንዲቆዩ ስለታዘዙ እንጅ!!!

አማራ ሆይ! የተጠነሰሰብህ ሴራ ይሄ መሆኑን ተረድተህ ለማይቀርልህ የሞት ሽረት ትግል እራስህን አዘጋጅ!!!

ትግሬና ኦሮሞ እንዲሁም ሌሎች በሕገወጥ የጦር አደረጃጀት ያለ የሌላቸውን አስታጥቀው ቀረጣጥፈው ሊበሉህ አሰፍስፈው ባሉበትና በግልጽ እየዛቱ እየፎከሩ ባሉበት በዚህ ሰዓት የአንተ አደረጃጀት ብቻ ሕገወጥና ኢመደበኛ!” እየተባለ ሊዘመትበት የሚችልበት አንድም ሕጋዊ አሠራር የለም!!!

ሚሊሻ ሕገወጥ አደረጃጀት ነው!” ከተባለ አስቀድሞ ትግሬ ውጫጩን ሳይቀር ያስታጠቀውን ገበሬ ትጥቅ ያስፈታ፣ ገበሬውን ብቻ ሳይሆን ኢሕገመንግሥታዊ ልዩ ኃይሉንም ያስፈታ!!! ኦሮሞም ሌሎቹም እንደዚያው!!! ይሄንን ሳያደርጉ አንተን ብቻ ለማስፈታት ከተንቀሳቀሱ ግን ዓላማው ሌላ ነውና በለው!!!

ድል ለአማራ!!! ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው