መጋቢት 10/2012 .

ክብር ረፍት ለጓድ መኮንን ደጀኔ (መኩሪያ

(1941-2012 .)

የኢሕአፓ ድርጅታዊ የሀዘን መግለጫ!

አቶ መኮንን ደጀኔ ወልደሰንበት (በኢሕአፓ ድርጅታዊ ስማቸው “መኩሪያ”) በሸዋ ክፍለ ሀገር፣ በየረርና ከረዩ አውራጃ በ1941 .ም ተወለዱ፡፡ የ1ኛ ደረጃና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት አጼ ገላውዴዮስ ሁ///ቤት ከተከታተሉ በኋላ ባህርዳር በሚገኘው ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ገብተው ሞያዊ ስልጠና ወስደዋል፡፡ እስከ 1966 .ም ድረስ በሲዳሞ ክ/ሀገር በ1ኛና 2ኛ ደረጃ መምህርነት ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ በ66ቱን አብዮታዊ ለውጥ በግንባር ቀደምትነት ለማስቀጠል ከተሰለፉትና ኢሕአፓን ተቀላቅለው ከፍተኛ ትግል ካደረጉት ምርጥ ኢትዮጵያዊያን መካከል አንዱ ናቸው፡፡

ድርጅታችን በወታደራዊ ደርግ አስተዳደር ከፍተኛ አመቃ እስከተፈጸመበት ድረስ፣ በሲደሞና አካባቢው የኢህአፓን ፕሮግራምና ዓላማዎች ለመምህራንና ለልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በማስተዋወቅና በማደራጀት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በ1968 .ም የኢሕአፓ ሰራዊት (ኢሕአሠ)ን ለመቀላቀል ወደ ትግራይ በረሃዎች በመጓዝ ወታደራዊ ስልጠና ወስደዋል፡፡ በአጭር ጊዜም ውስጥ የኃይል ኮሚሳር በመሆን ታግለውና አታግለው በወልቃይት፣ በጠለምት፣ በበየዳና በበለሳ ለበርካታ ዓመታት ያህል በትጋት የኢህአፓን ሰራዊት መርተዋል፡፡

በበለሳና አካባቢው (ሪጅን 3) ለሚንቀሳቀሰው ሰራዊት አመራር ሆነው ተመድበው ድርጅቱንም በወኔና በብቃት አገልግለዋል፡፡ በ1970ዎቹ አጋማሽ ላይ በሰራዊቱ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የሠራዊት አመራርነቱን ለቀው ሱዳን ገብተዋል፡፡ ከዚያም ወደ አሜሪካን ሄደው በአትላንታ ጆርጂያና በካሊፎርኒያ ግዛት በሎስ አንጀለስ አካባቢ መኖር ከጀመሩ በኋላ በአሜሪካን የድርጅቱ አመራር በመሆን ከሪጅን እስከ አህጉር አመራርነት በታላቅ ጽናት ሰርተዋል፡፡ 

አቶ መኮንን ደጀኔ (ጓድ መኩሪያ) እጅግ አገር ወዳድና ከራሳቸውም ሆነ ከማንም በላይ ብሔራዊ ስሜት ያላቸው ጓድ እንደነበሩ በሲቪልም ሆነ በወታደራዊ መስክ አብረዋቸው ሲያገለግሉ የነበሩ ሁሉ አረጋግጠዋል፡፡ የድርጅቱ ጓዶችና ደጋፊዎች ሁሉም ስለ ጓድ መኮንን (መኩሪያ) ድርጅታዊ ብቃትና ጽናት አረጋግጠዋል፡፡ 

በድንገተኛ ህምም ተይዘው ለቀናት በሆስፒታል ሲረዱ ከቆዩ በኋላ መጋቢት 6 ቀን 2012 .ም በተወለዱ በ71 ዓመታቸው ከአፀደ ሕይወት ተለይተዋል፡፡ ድርጅታችን ኢሕአፓ በጓድ መኩሪያ ዜና ረፍት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ለድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በሙሉ ለመግለጽ ይወዳል፡፡ 

ለጓድ መኮንን ነብስ ሔር እያልን፤ ለቤተሰቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው/ወዳጆቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን!!

የኢሕአፓ ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ፡፡ 

Phone : 251944223216