የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ዕሁድ [ዛሬ] አመሻሽ ላይ እንዳስታወቁት ቀን ላይ ከተገለጹት በሽታው ከተገኘባቸው 3 ሰዎች በተጨማሪ ሁለት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ሁለቱ ግለሰቦች የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ ወንዱ 38 ሴቷ ደግሞ የ35 ዓመት ዕድሜ እንደላቸው የተገለጸ ሲሆን ግለሰቦቹ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተጉዘው እንደነበር ተጠቅሷል።

ሁለቱ ግለሰቦች ላይ የበሽታው ምልክቶች ስለታዩባቸው በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባው መረጋገጡ ተገልጿል።

በዚህም በዚትዮጵያ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 21 ደርሷል።

BBC