- 30 ማርች 2020

የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍ ላይቤሪያን ለአስራ ሁለት ዓመታት መርተዋል። በእነዚህ ዓመታትም ውስጥ በአገሪቷ ታሪክ ፈታኝ የሚባለውና ለአምስት ሺህ ሰዎች ህይወት መቀጠፍ ምክንያት የሆነው የኢቦላ ወርርሽኝ ወቅትም በአመራር ላይ ነበሩ።
ቢቢሲ የኖቤል አሸናፊ የሆኑትን የቀድሞ የላይቤሪያ መሪ በኮሮናቫይረስ ላይ ያላቸውን አስተያት ጠይቋቸዋል። የቀድሞዋ ፕሬዚዳንትም ለዓለም ሕዝብ ያላቸውን መልዕክትም አስተላልፈዋል።
እንደ ጎርጎሳውያኑ 2014 የኢቦላ ወረርሽኝ 2ሺህ የሚሆኑ ዜጎቻችን የቀጠፈበት ወቅት ሲሆን፤ ወረርሽኙም ባልተጠበቀ መጠን በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተም ነበር።
በዚያ ወቅት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ባለሙያዎችን እንዲሁም ቁሳቁሶችን በማስተባበር እንዲልኩልን በመማፀን ደብዳቤ ፃፍኩላቸው።
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሲተባበር የምንፈራውን ወረርሽኝም ሊቀንስ እንደሚችል አስረዳሁ። አሁንም ቢሆን ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም መናገር የምፈልገው መተባበር እንደሚያስፈልግ ነው።
• የኮሮናቫይረስ መነሻ የነበረችው ዉሃን ከተማ በከፊል ለእንቅስቃሴ ክፍት ሆነች
በሁለት ዓመታት ውስጥ 11 ሺህ 325 ሰዎች በምዕራብ አፍሪካ ላይቤሪያን ጨምሮ፣ በሴራሊዮን፣ በጊኒ በበሽታው ሞተዋል።
ከስድስት ዓመታት በፊት በጦርነት ተዳክማ የነበረችው የላይቤሪያ ኢኮኖሚ የበሽታውን መዛመት መሸከም እንደማይችል፣ ያለው የጤና ሥርዓትም ያሽቆለቆለ ከመሆኑ አንፃር ለበሽታው እንድንጋለጥና እንዲዛመትም ምክንያት ሆኗል።
ዓለም አቀፍፍ ማኅበረሰብም ለምዕራብ አፍሪካ ያሳየው ምላሽም አጠቃላይ ያለንን የጋራ የጤና ደህንነት የሚያሳይ ነው።
ይህንንም ተላላፊ በሽታ በዚሁ መግታት ካልቻልን የትኛውም አገርም ሆነ ቦታ ላለ ማንኛውም የሰው ዘር ጠንቅ ነው በማለት ተከራከርኩ። ይህንም ተከትሎ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በጎ ምላሽ ሰጠ፤ ምላሹም ጥሩ ነበር።
በተባበሩት መንግሥታትና በአለም አቀፉ የጤና ድርጅት አስተባባሪነትም የተለያዩ እርዳታዎችም ተሰባሰቡ። አሜሪካም ቀጥላ ይህንኑ መንገድ ተከተለች።
አብረንም ይህንን እልህ አስጨራሽ ትግል ተወጣነው። የዚያን ወቅት በተሰራው አመርቂ ሥራ ምክንያት ውጤታማ የሆኑ ክትባቶች እንዲሁም ሌሎች መድሃኒቶች በዓለም ላይ ምጡቅ በሚባሉ ሳይንቲስቶች አማካኝነት ተሰራ።

- ስለ ኮሮናቫይረስ ሊያውቋቸው የሚገቡ ወሳኝ ነጥቦች
- ተመራማሪዎች ሰውነታችን የኮሮናቫይረስን የሚከላከልበትን መንገድ መለየት ቻሉ
- የኮሮናቫይረስ ህመም ምልክቶችና እንዳይዘን ማድረግ ያለብን ጥንቃቄ
- ራስዎን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል እጅዎን ታጥበዋል? ስልክዎንስ?
- ኮሮናቫይረስ የአእምሮ መረበሽን እያስከተለ ነው ተባለ
- የኪነጥበብ ባለሙያዎች መልዕክት ስለ ኮሮናቫይረስ
አሁንም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት የምናገረው ቢኖር ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተመሳሳይ የሆነ ትብብር እንዲያደርግ ነው። ምንም እንኳን አፍሪካ እንደ አህጉር ቫይረሱ ሲመጣ ቢዘገይም፤ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መዛመቱን ለመታገል ምንም ዝግጅት ያላደረገችውን አህጉር ክፉኛ እንደሚመታት ሳይታለም የተፈታ ነው።
መዛመቱን ለመቀነስ አብረን፣ ተደጋግፈን ልንሰራ ይገባል።
ለቫይረሱ መዛመት የተሰጠው ምላሽ ከእስያ ወደ አውሮፓ እንዲሁም ወደ አሜሪካ ስህተቶች ተፈፅመዋል።
ጊዜ ባክኗል፣ መረጃ ተደብቋል እንዲሁም በማይሆን መንገድ ተላልፏል። እምነትም ተሰብሯል።
“እኔም ተመሳሳይ ስህተት ሰርቻለሁ”
ፍራቻ፣ መደበቅ፣ መረጃዎችንም አለመግለፅ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመደበቅ መሯሯጥ ነበር፤ እናም መፍትሄው ከማኅበረሰቡ ውስጥ ነበር።
እኔም አውቃለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ስህተቶች ከስድስት ዓመታት በፊት ፈፅሜያቸዋለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ዓለም አቀፍ ድጋፍ የሚሰጡትም ይህንኑ ሰርተዋል። ስህተታችንም አስተካክለናል፤ ከማኅበረሰቡም ጋር አብረን እየሰራን ነው።
የመዛመቱን ሁኔታ ለመቀነስ ብዙዎች ድንበሮቻቸውን እየዘጉ ነው። ይህ ማለት ግን ብቻችንን ነን ማለት አይደለም፤ እያንዳንዱ አገርም በራሱ ተነጥሎ ቆሟል ማለት አይደለም። በተቃራኒው ይሄ የማኅበረሰቡ የጋራ ምላሽ ነው፤ ድንበሮችን መዝጋት ልዩነት ያመጣል።
• የህክምና ባለሙያዎቻቸውን ለመከላከል የሚተጉት ቱኒዚያውያን
ሁሉም ዜጎች፣ ሁሉም አገራት የራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል።
“አሸናፊ ሆነን ወጥተናል”
በላይቤሪያ ኢቦላ ወረርሽኝ አሸናፊ ሆነን መውጣታችን እንደ ማኅበረሰብ ጠንካራ አድርጎናል። በኢቦላ ወረርሸኝ ወቅት የተዘረጉ የጤና ሥርዓቶች ኮቪድ-19ን ለመከላከል ረድቶናል።
ዋናው የማምንበት ነገር በግለሰቦች መንፈስ አምናለሁ፣ በጋራ መፀለይ እንዲሁም በአምላክ ያለን ተስፋ ትልቅ ነገር ነው።
በዓለም ላለው ማኅበረሰብ ደህንነትም እፀልያለሁ።