April 3, 2020DW Amharic

የዓለም ባንክ  የኮሮና ተህዋሲ በኢትዮጵያ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚረዳ የ82.6 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እና ብድር ትናንት አጸደቀ።የባንኩ «ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር» ከመደበዉ ከዚህ ገንዘብ 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ እርዳታ፣ ቀሪው 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ብድር መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።…► ሙሉውን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ

የዓለም ባንክ  የኮሮና ተህዋሲ በኢትዮጵያ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚረዳ የ82.6 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እና ብድር ትናንት አጸደቀ።የባንኩ «ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር» ከመደበዉ ከዚህ ገንዘብ 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ እርዳታ፣ ቀሪው 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ብድር መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።

USA Wirtschaft Washington DC Zentrale der Weltbank Gebäude Logo (ullstein bild - Fotoagentur imo)

የዓለም ባንክ  የኮሮና ተህዋሲ በኢትዮጵያ የሚያስከትለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚረዳ የ82.6 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ እና ብድር ትናንት አጸደቀ።የባንኩ «ዓለም አቀፍ የልማት ማህበር» ከመደበዉ ከዚህ ገንዘብ 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ እርዳታ፣ ቀሪው 41.3 ሚሊዮን ዶላሩ ደግሞ ብድር መሆኑን ባንኩ አስታውቋል።በኢትዮጵያና አጎራባቾችዋ የባንኩ ተጠሪ ካሮሊን ተርክ፣ ኢትዮጵያ የጤና ስርዓቷን በማሻሻል ረገድ በጎ ውጤቶች ብታስመዘግብም  የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ስርዓት ተግዳሮት ይሆናል ተብሎ እንደሚጠበቅ እንዲሁም በምጣኔ ሃብትዋም ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ማሳደሩ እንደማይቀር መግለጻቸውን ባንኩ ዘግቧል። የባንኩ አዲሱ የኮቪድ 19 አስቸኳይ ምላሽና የጤና ስርዓት ዝግጁነት ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ የኮቪድ 19 መከላከያ ዝግጅነት እና ምላሽ ፣ለህክምና አቅርቦቶች እና መሣሪያዎች ለህክምና አቅም ግንባታ እና ለስልጠና ከውጭ የሚገቡ ሰዎችን ለመመርመር እና ለይቶ ማቆያ እና ማከሚያ ማዕከላትን ለማቋቋም የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ለኬንያ የ50 ሚሊዮን ዶላር፣ለኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ደግሞ የ47 ሚሊዮን ዶላር ብድር እና እርዳታ ሰጥቷል።
 

ኂሩት መለሰ 

አዜብ ታደሰ