April 13, 2020 |
ሚያዚያ 13, 2020
Source: https://amharic.voanews.com/a/wolqait-committee-arrest-4-13-2020/5370444.html
https://gdb.voanews.com/A0B34EB6-FDEB-47C1-A3EF-9BEC2160F931_cx0_cy8_cw0_w800_h450.jpg

የኢትዮጵያ ካርታ
ባህር ዳር — የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰሞኑን አባሎቻችን ያለ ምንም ምክንያት ታሰረውብናል ሲል ቅሬታ አቀረበ።
የወልቃይት አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አታላይ ዛፌ አቶ መብራቱ ጌታሁንን ጨምሮ ወደ 4 የሚጠጉ አባሎቻችን ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጎንደር ከተማ ውስጥ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረውብናል ብለዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ መብራቱ ልጅ ደግሞ አባቴ የታሰረው ፋኖ ነህ ተብሎ ነው ትላለች
በጉዳዮ ዙሪያ የመንግሥትን አካል ለማናገር የተደረገው ጥረት አልተሳካም።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት እስር
by ቪኦኤ