April 15, 2020 – Konjit Sitotaw

በሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ሚሲዮን ቆንስል ጄነራል ዶክተር ብርሃነመስቀል አበበ ከኃላፊነት ተነሱ።በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የኢትዮጵያ ሚሲዮን ቆንስል ጄነራል ዶክተር ብርሃነመስቀል አበበ ሰኚ ከኃላፊነት መነሳታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቊል።ይሁንና ሚኒስቴሩ ቆንስላ ጄኔራሉ በምን ምክንያት ከኃላፊነት እንደተነሱ ያለው ነገር የለም፡፡ዶክተር ብርሀነመስቀል አበበ ህዳር 2011 ዓ.ም ኢትዮጵያን በዲፕሎማሲው መስክ እንዲያገለግሉ በፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መሾማቸው ይታወሳል። – ETHIO FM 107.8