
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሲኒማ ቤት፣በአፍሪካም የተወላጆች የመጀመሪያ ሲኒማ፣“ሰይጣን ቤት”አይፈርስም!!በጥሩ ሁኔታ ታድሶ ከሚሰራው የመስቀል አደባባይ-ማዘጋጃ ቤት ፕሮጀክት ጋር ተካቶ አሁን ካለበት አሳዛኝ ሁኔታ ይላቀቃል።ይኸን ከክቡር ከንቲባው ጠይቄ ተረድቻለሁታሪካዊ ቤቱን እንዲህ በሚያሳዝን እና በሚያስጠይቅ ሁኔታ ላለፉት 25 አመታት በላይ ያለጥገና አሁን ደግሞ በአደገኛ ሁኔታ የዕቃ ማከማቻ ያደረገው ድርጅት ከዚያ እንዲወጣ መደረጉ ግድ ነው።
ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ እንደጻፉት
ዋፋ ሲኒማ ተብሎ የሚጠራው ቦታ ሊፈርስ ነው በሚል የወጣው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።ቦታው በኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ ታሪካዊ እንደመሆኑ መጠን ታሪካዊ ይዞታውን በጠበቀ መልኩ የመስቀል አደባባይ እስከ ማዘጋጃ ቤት የሚገነባው የአረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት አካል ሆኖ በአዲስ መልክ ይገነባል ተብሏል።አሁን ላይ ያለበት ይዞታም ቦታውን በማይመጥን መልኩ በእቃ ማስቀመጫነት እያገለገለ እንደሚገኝ ተገልጿል።ስለሆነም የከተማ አስተዳደሩ ይህን ቦታ ታሪካዊ ይዞታውን እንደጠበቀ በዘመናዊ መልኩ ተመልሶ ለአገልግሎት እንዲውል እንደሚሰራ ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።Source – አዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር