ለቻይና ብቻ የመጣ መቅሰፍት እስኪመሰል ኮሮናን “የቻይና ቫይረስ” እያሉ ያፌዙት ዶናልድ ቻይና ዋጋዋን አገኘች ያሉ በሚመስል ውስጣዊ እርካታ ወረርሽኙን ሲበዛ ችላ አሉት።

አጅሪት ቻይናም አፈር ልሳ ድንጋይ ተንተርሳ የመጣባትን መዓት አሽቀንጥራ ጣለች።

የነጩ ቤተመንግስት አለቃ ድንገት ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ያ “የቻይናው ቫይረስ” በመላከ-ሞት ተመስሎ በእርሳቸው አይዟቹ አትፍሩ ንግግር የተዘናጋውን ህዝብ አሰልፎ ሲወስደው አዩት።

ትራምፕ ሁሌም ቢሆን ከአጣብቅኞች ለመውጣት ሰዎች ላይ ጣት መቀሰርን ይመርጣሉ። ኮሮና በአሜሪካዊያን ላይ እያደረሰ በሚገኘው እልቂት ሀላፊነት እንዲወስዱ የተጠየቁት ትራምፕ ከዝያ ይልቅ ባራክ ኦባማ፣ ቻይና፣ ጆ ባይደን፣ ዴሞክራቶች እና የዓለም ጤና ድርጅትን ተጠያቂ ማድረግን መርጠዋል። ተጨማሪውን ይመልከቱ!

Subscribe to gmn ethiopia: https://www.youtube.com/channel/UCeGVb33cWmh-41lXoknj7Ig