April 20, 2020

Posted by: ዘ-ሐበሻ

ሚያዝያ 2012

ፖሊቲካ ነው ወይስ መንፈሳዊ? ሀሳቡን አገላበጥሁት! በዚህም በዚያም አየሁት፤ ውጤቱ ዜሮ ሆነብኝ፤ አንድ ሰው ዘመዴን ቢገድል፤ ሆነ፤ በእኔ በኩል አለቀ፤ በቃ፤ ብዬ ለእግዚአብሔር ሰጥቼ ይቅር ማለት እችላለሁ፤ አንድ ሰው ዘመዴን ቢያሰቃይ አሁንም እግዚአብሔር ፍዳውን ይክፈለው ብዬ ይቅር ለእግዚአብሔር ማለት እችላለሁ፤ አንድ ባለሥልጣን የዘመዴን ንብረት ዘርፎ እየተምነሸነሸ ሲኖርና የኔ ዘመድ በደሀነት፣ በችግርና በችጋር ሲቆላ በየቀኑ እያየሁት ይቅር ማለት የምችለው እንዴት ነው? አንድ በሉ፤ ሌሎች ባለሥልጣኖችስ ብንዘርፍ ይቅርታ ይደረግልናል ብለው ዘረፋን መስፋፋት አይችሉም ወይ? ሁለት በሉ! እንደሚመስለኝ ሙስናና ዘረፋ ይከርማሉ!